ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


በዚህ ቻናሌ ላይ የኦርዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣መዝሙሮች፣እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ። ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




🔴👉 እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡፡ ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡፡ ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትም እንዴት አብልጣ አታማልድ?

❗ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን❗

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 12 /2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16


❗#ጥር 12 #ቃና #ዘገሊላ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት (ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡

🔷👉 ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡

🔵👉 ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡

🔴👉 በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡

🔵👉 የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ_ ወደ ወዳጃ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡

🔴👉 እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡

🔷👉 ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡

🔴👉 ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡

🔷👉 ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡- የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› ትወልጃለሽ ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡

🔴👉 በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ ጌታችን ቀርቦ ‹‹የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡፡ ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ (ሉቃ 8÷28-29)

🔴👉 ስለሆነም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡ ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡፡

🔴👉 ‹‹ጊዜዬ አልደረሰም›› ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡- እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡ ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡

🔵👉 ይሁዳ ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡ እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል፡፡ የድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡፡

🔷👉 ነገር ግን የእናቱን የድንግል ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❗የሆለታው ቅዱስ ገብርኤል❗
🔷 በሠላም ገብቷል
ሆለታ 2017 ዓ.ም

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16




❗ጥር 11 በዓለ ኤዺፋንያ | በዓለ ጥምቀት❗
🔷👉 ጌታችን ለምን ተጠመቀ ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ጥር አስራ አንድ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሀንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም እለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም "መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው።

🔴👉 ' ኤዺፋንያ' የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን
የተወሰደ ሲሆን በቁሙ 'አስተርእዮ: መገለጥ' ተብሎ
ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤዺፋንያ ማለት 'የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት' እንደ ማለት ነው::

🔷👉 አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ
የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ 441ኤዺፋንያ
ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ33 ዓመታት ተመላልሷል::

🔴👉 ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር 10 ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::

🔷👉 10 ሰዓት መሆኑም ርግብ (መንፈስ ቅዱስ) ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::

🔵👉 መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: (ሉቃ. ማቴ. ) ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::

🔴👉 ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው:: ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ :: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ እያልክ አጥምቀኝ" አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::

🔷👉 ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ
ደነገጠች: ሸሸችም:: (መዝ) ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ
ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውሃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና:: ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::

🔴👉 አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::

🔷👉 ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::

❗ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተጠመቀ?❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ጌታችን እርሱ ባወቀ ለብዙ ምክንያቶች ተጠመቀ ጥቂቶቹን እንይ

❗👉 ትህትናን ሊያስተምረን -

🔵👉 ጌታችን በደቀመዝሙሩ በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ ባህረ ዮርዳኖስ በሰላሳ ዘመኑ ተጠምቋል፡፡ ይህን ምስጢር የፈጸመው በደቀ መዘመሩ እጅ ለመጠመቅ ወደ ነበረበት ስፍራ በመሄድ ነውና መምህረ ትህትና ያሰኘዋል፡፡

❗👉 ሥርአትን ሊመሰርትልን-

🔵👉 ጌታችን ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን፤ አድርጎ አድርጉ እንደሚል ደገኛ መምህር ተጠምቆ ተጠመቁ አለን፡፡

❗👉 ምስጢር ሊገልጥልን-

🔴👉 በጌታችን ጥምቀት ሰማያት ተከፍተዋል ፤የአብ ምስክርነት መንፈስቅዱስ ስምረት በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ለዚህም የሥላሴ የአካል፣ የስም የግብር ሦስትነት ተገልጧል፡፡

❗👉 የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ-

🔴👉 በዲያብሎስ ሥራ ተሸሽጎ የኖረውን የዕዳ ደብዳቤ እንደ ሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ሊደመስስልን ጌታ ተጠመቀ፡፡

🔵👉 በመሆኑም በልደቱ ያገኘነውን ጸጋ በጥምቀት ልጅነት አጽንተን በመጠበቅ የመንግስቱ ወራሽ የክቡር ስሙ ቀዳሽ እንሆን ዘንድ የጌታችን ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን፡፡አሜን

❗እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ❗
🔷👉 መልካም በዓል

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 11 /2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❗ታቦታቱ በሠላም ገብተዋል❗
    🔷 ከተራ በሆለታ ከተማ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16




❗#ከተራ_ምን_ማለት_ነው?❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ከተራ "ከበበ" ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

🔵👉 የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡

🔴👉 በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የምእመናኑ አብዛኛው ሥራ ውኃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

🔴👉 ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው፡፡ በየሰበካው ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦታቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድሩበት፣ የተለያዩ የውኃ አካላት ተጠርገው የሚከተሩበት ወይም ሰው ሠራሽ የግድብ ውኃ የሚበጅበት ስፍራ ‹‹ባሕረ ጥምቀት››፣ ‹‹የታቦት ማደርያ›› እየተባለ ይጠራል።

🔵👉 ከዚህም በተጨማሪ በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡

🔵👉 በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

🔴👉 ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል፡፡ የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ፡፡

🔴👉 ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡

🔵👉 ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።

🔵👉 ታቦታተ ሕጉ በወጡበት ቦታ የማይመለሱበት ምክንያት ብዙ ምስጢር አለው፤ ይኸውም ‹‹ወተቀደሰት ምድር በኪደተ እግሩ ምድር በኪደተ እግሩ ተቀደሰች›› እንዳለ ሊቁ ያልተባረከ መሬት እንዲባረክ ነው፤ ዳግመኛም ያላየው እያየ ያልሰማው እየሰማ ሥርዓቱን አይቶ እንዲያምን ሃይማኖት እንዲሰፋ ነው። ነቢያት በመጡበት እንዳይመለሱ ሥርዓት ነበረና የዚያም ምሳሌ ነው፡፡ ሰብአ ሰገል ጌታን ካገኙ በኋላ በመጡበት ቦታ አልተመለሱምና የዚያም ምሳሌ ነው፡፡

🔴👉 የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዞ አክብሮ ወደ ወንዝ መውረድ በብሉይ ኪዳን የነበረ ሥርዓት ነው ኢያሱ በሙሴ ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን ሲመራ ታቦቱን አሸክሞ ሲሔድና ከዮርዳስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከኹለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም እንደነበረ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል።

🔷👉 እስራኤል ወደ ምድረ ርስት ሲገቡ ታላቁን የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሻገሩ ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳን ታቦት ድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ ዙሪያውን፣ ካህናቱ በውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንደተሻገሩ መፅሐፍ ይናገራል ዛሬም እንደ ዮርዳኖስ ከድህነት ወደ ብልጽግና፣ ከደዌ ወደ ጤና፣ ከከህደት ወደ ሃይማኖት ከድንቁርና ወደ ዕውቀት አላሻግር ያለን ባሕረ ኀጢአት በቃል ኪዳኑ አማካኝነት በጥምቀቱ በረከት ያደርቅልናል። ኢያሱ ፩ ፥ ፲፫ ፣ ኢያሱ ፫ ፥ ፰

🔴👉 በዓለ ከተራ የምን ምሳሌ ታቦታቱ ለምን ወደ ጥምቀተ ባሕር ሔደው እዛው ያድራሉ ቢባል :- ሐዋርያው ፊልጶስ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባውን ሊያጠምቀው ወደ ጋዛ ወንዝ የመውረዱ ምሳሌ ነው። ሐዋ ሥራ ፰ ፥ ፴፬

🔷👉 ዋናው ምሥጢሩ ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐንስን አስከትሎ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱና ለመጠመቅ ተራ ሲጠብቅ እዛው የማደሩ ምሳሌ ነው። ጌታችን ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመጣው ጥር 10 አመማቴ ፫ ፥ ፲ በዚህ መሠረት ከጥንት ጀምሮ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘን ወደ ወንዝ ወርደን በዓለ ጥምቀትን የምናከብረው ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው።

🔴👉 ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ጥር ፲ ቀን ተቀራራቢ የሆኑትን ታቦታትን በየአቅራቢያቸው ወደሚገኘው ወንዝ በአንድነት እያወረደች ከከተራ ዕለት ጀምሮ የጥምቀትን በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብራለች። ሌሊቱን ከሚያነጋው ሕዝበ ክርስቲያን ጋር በመሆን ያሬዳዊ ማሕሌትና የወንጌል ጉባኤ ተዘርግቶ በመምህራን ወቅታዊ ትምህርት ሲሰጥ ይታደራል ይዋላል።

🔵👉 በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀት መዘጋጀት የሚከተለው ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው። ታቦቱ የጌታችን፤ ታቦቱን አክብሮ /ይዞ/ የሚሄደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሄዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።

❗እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ❗
🔷👉 መልካም በዓል

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 10 /2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16










❗🔴ጥር 7 #በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ
🔵👉 ለምን ይከበራል ?
..........................................................
🔴👉 ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

❗#ሕንጻ_ሰናዖር
🔵👉 ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

🔴👉 ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

🔵👉 ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

🔴👉 መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

🔴👉 ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

🔵👉 ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

❗#ቅዳሴ_ቤት
🔴👉 ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

🔴👉 ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

🙏 ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 7/2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16








❗ጥር 6 በዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ❗
🔵👉ለምን ይከበራል ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ጌታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዕለት ሰይማ የምታከብር ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጥር 6 ቀንን በየዓመቱ በልዩ ሁኔታ ታከብረዋለች!

❗ክብር ምስጋና ይድረሰውና የጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት በየዓመቱ ጥር 6 ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ጥር ፮ ቀን በሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ የሚገኘውን የጌታችንን የግዝረት ታሪክም በሉቃስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ ከተቀመጠው ትምህርት ጋር በማጣቀስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል !

🔵👉 ልሳነ ዕፍረት ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፡፡ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ፤›› በማለት እንደ ተናገረው /ሮሜ.፲፭፥፰/፣ የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጽሟል፡፡ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡

🔴👉 ስሙም ገና በሥጋ ሳይፀነስ የእግዚአብሔር መልአክ ባወጣለት ስም ‹‹ኢየሱስ›› ተብሎ ተጠራ /ሉቃ.፪፥፳፩-፳፬/፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ /ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ/፡፡

🔵👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አረጋዊው ዮሴፍን ‹‹እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የኾነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ፤›› አለችው፡፡

🔴👉 ጻድቁ ዮሴፍም እንዳዘዘችው የሚገርዝ ባለሙያ ይዞ መጣ፡፡ ባለሙያውም በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ባየው ጊዜ ‹‹እንድገርዘው በጥንቃቄ ያዙት›› አላቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ‹‹ባለሙያ ገራዥ ሆይ! ደሜ ሳይፈስ ልትገርዘኝ ትችላለህን? በዕለተ ዓርብ በመስቀል ስሰቀል ካልኾነ በስተቀር ደሜ አይፈስምና፡፡ ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኀና ደም ይፈሳል፡፡ ይኸውም ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኀኒት ይኾናል፤›› አለው፡፡

🔵👉 የክብር ባለቤት ጌታችን የተናገረውን ይህን ቃል ባለሙያው በሰማ ጊዜም አደነቀ፡፡ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሣና ከጌታችን እግር በታች ወድቆ ሰገደ፡፡ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጁ ላይ እንዳሉ እንደ ውኀ ቀለጡ፡፡ ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም ‹‹ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ ይህ ልጅሽ ስለ እርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው፤›› አላት፡፡

🔷👉 ጌታችንም ባለሙያውን ‹‹እኔ ነኝ! ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ? ወይስ የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ ላድርግ?›› አለው፡፡ ባለሙያውም መልሶ ‹‹የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ጌታችንም አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የሕዝቡ ዅሉ አባት እንደ ኾኑ ካስገነዘበው በኋላ ‹‹ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው›› በማለት የግዝረትን ሕግ አስረዳው፡፡

🔴👉 ባለሙያውም ይህን ምሥጢር ሲሰማ ‹‹እኔ ከአንተ ጋር እነጋገር ዘንድ አልችልም፡፡ በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና፤›› ብሎ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት መሰከረ፡፡

🔴👉 በዚህ ጊዜ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹‹አባት ሆይ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው፤ ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ›› አለ፡፡ ያንጊዜም ያለ ሰው እጅ በጌታችን ላይ ግዝረት ተገለጠ (የግዝረት ምልክት ታየ)፡፡

🔵👉 ከዚህ ላይ ጌታችን ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አብ ልመና ማድረሱ የለበሰው ሥጋ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ መኾኑንና ጸሎት ማቅረብ የሚስማማው ሥጋን መልበሱን ለማጠየቅ ነው እንጂ በእርሱና በአብ መካከል ልዩነት ኖሮ አይደለም፡፡

🔵 ጌታችን ድንግልናዋን ሳያጠፋ ከድንግል ማኅፀን እንደ መውጣቱ ግዝረቱም አይመረመርም፡፡ በተዘጋ ቤት ወደ ሐዋርያት እንደ ገባና እንደ ወጣ ዅሉ እርሱ በሚያውቀው ረቂቅ ጥበብ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቈረጥ፣ ምንም ደም ሳይፈሰው መገረዙ ተገለጠ፡፡

🔴👉 ገራዡም የጌታችንን ቃል ከመስማቱ ባሻገር በሥጋው ላይ የተደረገውን ተአምር ባየ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ከክብር ባለቤት ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ወድቆም ሦስት ጊዜ ሰገደና ‹‹በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ!›› በማለት በክርስቶስ አምላክነት አመነ፡፡ ከዚህ በኋላ ያየውንና የሰማውን ዅሉ እየመሰከረ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

❗የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ኅብረት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ያለ ጥርጥር በፍጹም ልባችን ከምናምን ምእመናን ጋር ይኹን! /፪ኛቆሮ.፲፫፥፲፬/፡፡❗

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 6/2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

Показано 20 последних публикаций.