❗#ጥር 15 #ቅዱስ_ቂርቆስ_ወኢየሉጣ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 የሰማዕትነት ታላቅ ክብር ያገኘው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በነበረበት ጊዜ የነበረው መኰንን ክርስቶስን በመካድ በክርስቲያኖች ላይ መከራ ያጸናባቸው ነበር፤ ሕፃኑ ቂርቆስንም ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ይኽ ሕፃን ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው በማለት መለሰለት፡፡
🔷👉 መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡
🔴👉 መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
🔴👉 መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡
🔵👉 ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡
🔷👉 የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡
🔷👉 በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት "ምን ላድርግልኽ?" አለው፤ ሕፃን ቂርቆስም ለጌታ "ሥጋዬ በምድር ላይ አይቀበር፤ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ ፍላጎታቸውን ስጣቸው፤ ስሜ በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ፤ በሰውም ላይ ተላላፊ በሽታ በእኽልም ላይ ድርቅ የውሃም ማነስ አይኹን" አለው።
🔴👉 መድኀኔ ዓለምም ሕፃኑ ቂርቆስን "የለመንከኝን ኹሉ እሰጥኻለሁ ሥጋኽንም ኤልያስ ባረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖርልኻለኊ" አለው፤ ይኽነን ቅዱስ ቂርቆስ በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር 15 በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገታቸው ተቈረጠ፤ መድኃኒታችን ክርስቶስም በማይጠፋ አክሊል ጋረዳቸው፤ ነፍሶቻቸውም በታላቅ ክብር ዐረጉ የሰማዕትነትንም ክብር ተቀዳጁ።
ምንጭ :- ስንክሳር ዘወርኃ ጥር
❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 15/2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube
🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16