Репост из: أبو هشام📡 አቡ ሂሻም 📡
🌹ጥቂት ምክር ለሚስቶች🌹
የተከበርሽው እህቴ በጆሮሽ የምነግርሽ
ሚስጥር አለኝ ከልብሽ አድምጪኝ...
አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ለሚስቶቻቸው ላቅ ያለ ክብር ከመስጠታቸው በላይ ርህራሄን፤
አዘኔታን ፍቅርን በንጹሁ አንደበት
እንደሚያጎናጽፋቸው የታወቀ ነው!!
♒ ይሁንና ወንዶች በሴቶች ላይ እንዲንጸባረቁ የማይፈሉጓቸውና የሚጠሏቸው ባህሪያት አሉ፡፡
ለመሆኑ እንዚህን ባህሪያት ለይተሸ ታውቂያቸዋለሽ??
ካወቅሽ ምን ያህል እየተጠነቀቅሻቸው ነው??
አላውቅም ከሆነ መልስሽ በጆሮሽ ሹክ
የምልሽ ነገር ስላለ በደንብ አድምጪኝ፤ የምፈልገው ነገር ቢኖር ይህንን ሚስጥር ሰምተሸ ተግባር ላይ እንድታውይው ነውና፤ ለመተግበር ቃል ግቢልኝ!!
① ፈላጭ ቆራጭ እኔ ልሁን አትበይ፡-
እንዲህ አይነት ባህሪ ያላት ሚስት ባሏ ከአጠገቧ እያለ የምትዘነጋውና ከነአካቴው የምትረሳ፣ እንቅስቃሴዋ ሁሉ በሃይል የተሞላ፣ ሰለቤተሰባዊ
ጉዳያቸው ከባሏ ጋር ምክክርን የማትፈልግ፣ ባሏን እንደምትፈልገው ልትመራውና ልታሽከረክር የምትሞክር ናት፡፡
እሱ እንደሚስት እሷ ደግሞ እንደአባወራ!!
ባሏ በዚህ ባህሪዋ የተነሳ ባል
ከሷ የሚለይበትን (የሚላቀቅበትን)
መንገድ ማሰብ ይጀምራል፡፡
ቤታቸው ሰላም ያጣል፤
ባሏ ከእሷ ያጣቸውን ነገሮች ከሌላ ሴት ማግኘት እንደሚችል እራሱን በቀላሉ አሳምኖ በተፈጠረው አጋጣሚ ድንገት ከእጅ ወድቆ እንደሚሰበር ብርጭቆ
እሱም ከእጅሽ ያመልጥሻልና ልብ በይ!!
🍁 እህቴ ሆይ በዚህ ጉዳይ ዙርያ እራስሽን መርምረሽ በጣም ጥንቃቄ ልታደርጊ ይገባል፡፡
② ውሸታም ሚስት አትሁኚ፡-
እውነት መናገር አንድን የትዳር ህይወት ስኬታማና ደስተኛ ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለዚህ
አንድ ባል ከሚስቱ የሚጠላው ክህደትና መዋሸትን ሲሆን ሁሌ በትዳርሽ ውስጥ ውሸት የምትቀላቂይ ከሆነ ምናልባት አንድ ቀን ከደረሰበት ከዚያ በኃላ አንቺን የሚያየው በንቀት ይሆንል፡፡
🍁 ስለዚህ በባልሽ ከመናቅሽ በፊት ጥንቃቄ አድርጊ!!
③ ተናዳጅና ብስጩ፣ አማራሪ ሚስት አትሁኚ፡-
እንዲህ አይነቷ ሚስት ማለት ስለራሷ ጉዳይ እንጂ ስለሌላው የማትጨነቅ በትንሽ በትልቁ የምትበሳጭ፤ የምታማርር፤የምትናደድ ሴት።
በዚህ የተነሳ ባሏን በራሷ እጅሽ ታርቂዋለሽ!!
ከብስጭት የተነሳ ክብሩን መንካትሽ አላህ ዘንድ ያለሽን ቦታም ያሳጣሻል፣ መነጫነጭሽ፣ ድምፅሽን ከፍ ማድረግሽ፣ እርሱ እንዳያከብርሽ ያደርጋል። ብሎም፤ መጥፎ ቃላትን መወራወራችሁ፤ ለፍቺ ና መጎዳዳት ሊያበቃችሁ ይችላል።
ከሁሉም የሚብሰው፤ ሁልጊዜ በማማረርሽ ምክንያት ላንቺ መልካም አድርጎ አንቺን ማስደሰት እንደማይችል ካመነ፤ በመካከላችሁ ያለውን ፍቅር የሚንከባከበው ሀዲያ ይቀንሳል።
🍁 ስለዚህ፤ ከማማረር፣ ከመነጫነጭ እና ከብስጭት ተቆጠቢ!!
④ አንደበት ደረቅ ሚስት አትሁኚ፡-
ይህችኛዋ ሚስት ደግሞ ማነኛውንም አይነት ስራ የቤቱምንም ሆነ ከቤት ውጪ ያሉትን ሃላፊነቶችና ስራዎች ባሏ ብቻ እንዲወጣቸውና እንዲያከናውናቸው የምትፈልግ ናት። ባሎች ከምንም ነግር በበለጠ ምልካም ንግግር እና ትህትና ይገዛቸዋል፤ ስለሴቶች በተፈጥሮ ለስለስ ያለ ተፈጥሮን ስለሚያስቡ፤ ደረቅ አገላለፅና ምላሽ አይወዱም።
እራስሽን በማስተናነስ፤ እንደአገልጋይ የባልን ልብ የሚስቡ የትህትና ቃላትን ብትወረውሪ ክብርሽ ዝቅ አይልም።
እንደውም ትመጥቂያለሽ!!
መልካም ንግግር፤ ምን ያክልየጠለሸን እና ቂም ያረገዘን ልብ እንደሚቀይር ሱረቱል ፉሲለት መጨረሻ ላይ አንብቢ!!
🍁 እህቴ ሆይ! አሽሙርን እና ስሜትን የሚጎዱ መጥፎ ቃላትን ከመጠቀም ተጠንቀቂ!! በቀላል መስእዋትነት የባልሽን ቀልብ ግዢ!!
5. አቋመ ግትር ሚስት አትሁኚ፡-
ይህች ደግሞ አንድ አመለካከት ካላት በዚያ አመለካከቷ ላይ የማይቀየር ግትር አቋም የመያዝ ባህሪ ያላት ናት፡፡ ጥፋት አጥፍታ አልፈጸምኩም አላደረኩም ብላ በፈጣጣነት የምትክድ፤ ተሳስቻለሁ ወይም አጥፍቻለሁ ብላ የመናገር ፍላጎት የሌላት የራሷ ብቻ ትክክል እንደሆነ የምታምን ሚስት ናት።
እንዲህ አይነተቷ ሚስት ቤቷን ታፈርሳለች፤ ለውይይትና ለመግባባት ክፍት ስላልሆነች፤ ከተወያየችም የባሏን ጥፋት የማጉላት ሂደትን ስለምትከተል ችግሮችን የመፍታት አቅም የላትም።
🍁 እህቴ ሆይ! አደራሽን ጥፋትን በመቀበልና በመተራረም እነጂ በድርቅና ሰላም አይገኝም!!
6. ነገረኛ ሚስት እንዳትሆኚ፡-
ይህችኛዋ ሚስት ደግሞ ምንም ጊዜ በጠብና በጭቅጭቅ መኖርን የምትወድ ናት። ባህሪዋ ስላደረገችው፤ ጠብ ወይም ጭቅጭቁ የህይወት ስታይሏ ሆኗል፡፡ ሁሌ የምትጋጭበትንና የምትግባባበትን ምክንያቶች የምትፈልግ፣ ድርጊቷ ሁሉ በነገር የተሞላ ናት። እንዲህ አይነቷ ሴት ፈፅሞ ትዳርንም ሌላ የጋራ ፕሮጀክት ማሳካት አትችልም። በባሏ ልቦና ውስጥ ጥላቻን በመፍጠር ቤቷ ውስጥ ሰላም እንዳይኖረው ታደርጋለች።
🍁 ነገረኝነት ትዳርን ብቻ ሳይሆን አኼራን ያሳጣሻልና ተጠንቀቂ፤ እራስሽን ገምግሚ፣ አርሚም!!
🌷 እህቴ ሆይ!
እነዚህን የነገርኩሽን ሚስጥሮች በጥሞና አድምጠሸ ከዚህ ሰአት ጀምረሽ "እኔስ ላይ የትኘው ባህሪ ሊኖር ይችላል?" ብለሽ እራስሽን ፈትሺ።
ከነዚህ ባህሪያት እንድትቆጠቢም አዳራ እልሻለሁ።
💐💐💐