መዝሙረ ዳዊት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረቦችን ትምህርቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
@mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@Estifo_17 ላይ ያገኙናል

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

◉ መና አውርዶ ◉

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
💚@mezmurochh💚
💛@mezmurochh💛
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ መና አውርዶ

መና አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ

ነፀብራቃዊዉ ሚካኤል
አምደ ብርሃን ሚካኤል
ነፃ ያወጣ ሚካኤል
ህዝበ እስራኤልን ሚካኤል

ሌሊቱን ብርሃን እያደረክ
ምራን እኛንም ወደ አምላክ

አዝ________________

እሩሩ መላዕክ ሚካኤል
ያፎምያ አባት ሚካኤል
ፈጥነህ የምደርስ ሚካኤል
በጭንቀት ላሉ ሚካኤል

ጠላት ዳቢሎስ እንዳይጥለን
ቅዱስ ሚካኤል አትለየን

አዝ________________

የሚቃወሙን ሚካኤል
በእሱ እራቁልን ሚካኤል
ጠላቶቻችን ሚካኤል
ተሸነፉልን ሚካኤል

የማንችለውን እያስቻለን
ለዚህ አበቃን እየረዳን

አዝ________________

ወደ ሞት ሲሄድ ሚካኤል
ደብዳቤ ይዞ ሚካኤል
ደጉ ባህራን ሚካኤል
ከንጉስ ታዞ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል በረድሄት
ሞቱን በህይወት ለወጠለት

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ 💚 @mezmurochh 💚 ✥
✥ 💛 @mezmurochh 💛 ✥
✥ ❤ @mezmurochh ❤ ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


➣ አንተኑ ሚካኤል ዘአውረድከ መና ➢

    ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤል ነጻነት ያወጣበትን ዕለት አደረሰነ 🙏

✤ ኅዳር ፲፪(12) ሚካኤል ወአስተርእዮተ ዮሐንስ መጥምቅ ውስተ ደብረ ማኀው ወፊላታዎስ ሊቀ ጳጳስት ወበእደ ማርያም ንጉሥ ዘኢትዮጵያ ✤

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ

✤ ትርጉም ✤

አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል
በማዳንህ እጅግ ሐሤትንና ያደርጋል
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው

            መዝ ፳-፩
                 20   1

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፲፱ ቁ ፲፩-፳፰
           19    11  28

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ሮሜ ም ፱ ቁ ፲፯-፳፬
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፱-፲፬
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኀኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር

🙏 ትርጉም 🙏

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸውማል
እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም

              መዝ ፴፫-፯
                     33   7

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፲፭-፳፩
            18     15  21

❖ ቅዳሴ

ያዕቆብ ዘሥሩግ አው ባስልዮስ

" አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ ተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም፤የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ደጅም እንጠናለን እንጂ "
     ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
              ም ፩ ቁ ፹፯
                  1      87

✝ በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ በረከት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከሊቀ መላዕክቱ ከቅዱስ ሚካኤል በረከት ይክፈልን በቅዱሳኑ ፀሎት ሁላችንም ይማረን ለቅዱሳኑ ሁሉ የተለመነች እመቤታችን ማርያም ለሁላችንም በረከት በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ለህዝባችን ስላም ይስጥልን ደም ሰማዕታት ቅዳሴ መላዕክት ዝማሬ ዳዊት የተቀበለ አምላክ ቅዱሳን የኛንም ፆም ፀሎት ምሕላ ምስጋና ይቀበልልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ✝️

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

5k 0 23 5 16

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

በዓለ ደብረ ቁስቁዋም

የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ [ማቴ.፪፥፩-፲፰] እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ፪ ዓመቱ የጥበብ ሰዎች [ሰብአ ሰገል] ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ [144,000] ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፩ አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::

ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

- የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
- ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
- የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
- የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
- የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
- እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::

ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::

"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"

፩. ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና [ኢሳ.፲፱፥፩, ዕን.፫፥፯]

፪. ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ [እሥራኤል] : ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

፫. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: [ኢሳ.፲፱፥፩]

፬. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

፭. ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: [ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::]

፮. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

፯. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ፫ ዓመታት ከ፮ ወራት [ወይም ለ፵፪ ወራት] በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር [ደብረ ሊባኖስ] ነው::

በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: [እሴብሕ ጸጋኪ]

ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ [አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው] ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ፻ ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::

ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::

እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች [ከሰብአ ኦፌር] የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ፭ ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::

ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት ፬፻ ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ፫፻፺ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::

የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::

ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው :-

"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: [ሰቆቃወ ድንግል]
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::

ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

9k 0 34 4 10

➢ ተማኀፀንኩ በዘባንኪ ዘአግመረ ርስነ መለኮታዌ እሙነ ሐውጽኒ ድንግል ወናዝዝኒ ፍጡነ ➢

  ሰቆቃወ ድንግል ዘደረሰ አባ ገብረኢየሱስ ዘደብረ መጓዬና

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️

➢ እንኳን ከ፴፫ቱ ከእመቤታችን በዓላት አንዱ ከስደት ያረፈችበት በዓለ ቊስቋም ማርያም በዓል በሰላም አደረሳችሁ ➢

👉  ኀዳር ፮ ቦአ እግዚእነ ውስተ ደብረ ቊስቋም ወፊልክስ ሊቀ ጳጳሳት ወተዝካሩ ለአባ ፍሞስ ወለንዲዎስ ወይላጥስ ወማርትሮስ ወኢላስዎስ ወቆርናልዮስ ወሱኪሮስ ወናውኔኖስ ወሊባዲቆ ወሲላስዮስ ወ፪ቱ ፻ወ፸ወ፪ቱ ማኀበረ ኤስድሮስ ሰማዕት 👉

➢ ዘነግህ ምስባክ ➢

ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ
ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር እጐሊሃ
ምሥዋዒከ እግዚአ ኃይላን ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ

ርግብ ለርስዋ ቤት አገኘች
ዋልያም ጫጩቶችዋን የምትኖርበት ቤት አገኘች
የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬ ሆይ እርሱም መሠዊያህ ነው

       መዝ ፹፫ - ፫

➣ ወንጌል ➣

ሉቃ ም ፳፪ ቁ ፲፬ - ፳፬

✝️ የቅዳሴ ምንባባት ✝️

፪ ቆሮ ም ፰ ቁ ፩ - ፲፮
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፱ - ፍፃሜው
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪ - ፲፭

👉 ምስባክ 👈

ርኢክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዘ ሊባኖስ
ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ
ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ

➢ ትርጉም ➢

ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ልምልሞ አየሁት
ስመለስ አንዱም ብመለስ ግን አጣሁት
ፈለግሁትን ቦታውን አላገኘሁም

     መዝ ፴፮ - ፴፭

➣ ወንጌል ➣

ማቴ ም ፪ ቁ ፲፪ - ፍፃሜው

👉 ቅዳሴ 👈

ዘእግዚእነ

" ዓለሙን የምታሳረፈው ሆይ በመስቀል ላይ የተሠወረ ምሥጢርን ያሳየህ አንተ ነህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይና ቅዱስ ማነው

    ቅዳሴ እግዚእነ

✝️ በዓሉን በዓለ በረከት በዓለ ሐሴት ያድርግልን ቸሩ መድኀኔ ዓለም በቸርነቱ ይማረን ከበዓለ ሚጠታ በረከት ትክፈለን በዕፅ መስቀሉ ይጠብቅን ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ለቅድስት ሰሎሜ ለቅዱስ ጊጋር መስፍነ ሶርያዊ ለአባ ጽጌ ድንግል ለአባ ገብረኢየሱስ ለአባ ጊዮርጊስ ለቅዱስ ያሬድ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለእቴጌ ምንትዋብ የተለመነች ለኛም ትለመነን ቸሪቱ እመ አምላክ ፍቅሯ ይደርብን ለሃገራቸው ፍፁም ሰላም ይስጥልን ሰናይ የበረከት በዓል ያድርግልን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱስ ዮሴፍ ይሰውረን ✝️

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

ስምሽን ቢጠሩ

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            💚@mezmurochh💚   
            💛@mezmurochh💛   
            ❤@mezmurochh❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ስምሽን ቢጠሩ

ስምሽን ቢጠሩ የማትጠገቢ
የመንገድስንቄ ነሽ የነብሴ መጋቢ
ምስጋናሽ ይብዛልኝ ወደቤቴ ጊቢ

ጻድቃን የወረሱሽ የእግዚእብሔር ከተማ
የምንዱባን ሰፈር የሞላብሽ ግርማ
ቡራኬሽ ይድረሰኝ እናትዬፍቅርሽ
ነብሴን ለምስጋና ላንቺ ላፍስልሽ

አዝ----------------

የአለም አርነት ጽህፈት ያለብሽ
የሂወት ፊደሌ ጽድቅ የተማርኩብሽ
ቢያነቡሽ አታልቂ ሚስጥርሽ የሰፋ
ስምሽ ማራኪነው ከልብ የማይጠፋ

አዝ----------------

በሰው ሀገር ስኖር ሰው ጠፍቶ ከጎኔ
ባልንጃራ ሆነሽ የለሊት ብራኔ
ተስፋዬን አብዝተሽ ጥሜን አስታገሽው
በብዙ በረከት ጎጆዬን ሞላሽው

አዝ----------------

ፍፁም ሩሩነሽ ስምሽ ጣእም ያለው
ሀዘኔ ሲበዛ ባንቺ እፅናናለው
የአለም እርጋታ የሰላም ውጥን ነሽ
ጊዜ ለጣለው ሰው አይጨክንም ልብሽ

መዝሙር
ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ 💚 @mezmurochh 💚 ✥
✥ 💛 @mezmurochh 💛 ✥
✥ ❤ @mezmurochh ❤ ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔


ዘማሪ ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

መድኃኒዓለም የለም የሚሳነው

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            💚@mezmurochh💚   
            💛@mezmurochh💛   
            ❤@mezmurochh❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


መድኃኔ_ዓለም

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው

አላስብም ነበር አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ

አዝ----------------

የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ

አዝ----------------

ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ

አዝ----------------

እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ

ዘማሪ
ሲስተር ሕይወት ተፈሪ


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
       ✥     💚 @mezmurochh 💚   ✥
       ✥     💛 @mezmurochh 💛   ✥
       ✥     ❤ @mezmurochh ❤   ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ 
@teksochina_meslochi
 ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

🔊    ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ 

          ◦ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ◦

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          💚 @mezmurochh 💚   
          💛 @mezmurochh 💛   
          ❤ @mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ በሰማያት ላይ

በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል
ክብርህም በምድር ይነገራል
ዘመን የሚዋጅ አለን ምስጋና
መድኃኔዓለም ስምህ ገናና (×2)

እልፋ አላፍ መላእክት
ቢቆሙ ካንተ ፊት
አያርፉም ይተጋሉ
ስሉስ ቅዱስ እያሉ

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

አዝ----------------

ሊቃናት ይጮሀሉ
በጉ ድል ነሳ እያሉ
የወርቅ ፅና የያዙ
ምስጋናህን አበዙ

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

አዝ----------------

በደምህ የታተሙ
ኃይልህን ተሸክሙ
የቅኔ ዑደት ሆነ
ክብርህ በአለም ገነነ

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

አዝ----------------

በዙፋኑ ስር ካሉት
ከሰባቱ መናፍስት
ከታመነው ምስክር
አዲስ ውዳሴ መዝሙር

«ያለና የሚኖር»(×2)
አንተ ነህ እግዚአብሄር

                 ዘማሪ
     ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥     💚 @mezmurochh 💚   ✥
    ✥     💛 @mezmurochh 💛   ✥
    ✥     ❤ @mezmurochh ❤   ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ 
@teksochina_meslochi
 ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
✧ ድንግል መከራሽን ✧

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
💚 @mezmurochh 💚
💛 @mezmurochh 💛
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ​​ድንግል መከራሽን

ድንግል መከራሽን ጥቂት ላስታውሰው
በሄሮድስ ዘመን ፍጥረት ያለቀሰው
አንቺ የአምላክ አናት ደግሞም እመቤት
እንደ ችግረኛ ተነሳሽ ስደት 

ኧረ ለመሆኑ እንዴት አለቀልሽ
ስትንከራተቺ በረሃን አቋርጠሽ
ይገሉታል ብለሽ ለልጅሽ አስበሽ
በሄሮደስ ዘመን መከራሽን አየሽ
መከራሽን መከራሽን አየሽ

አዝ____

አዛኝቷ ማርያም በጠራሁሽ ጊዜ
እንድትደርሽልኝ በመከራ ጊዜ
መከራን ያየ ሰው መቼም አይጨክንም
አትጨክኝብኝ አደራሽን ድንግል
አደራሽን አደራሽን ድንግል

አዝ____

አቤት የዚያን ጊዜ ያየሽው መከራ 
ያለቀሽው ልቅሶ ጭራሽ አይወራ 
የአማኑኤል እናት አንቺ መከረኛ 
እድሜሽን ጨረስሽው ሆነሽ ኀዘንተኛ 
ኀዘንተኛ ሆነሽ ኀዘንተኛ

              
        ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥ 💚 @mezmurochh 💚   ✥
   ✥ 💛 @mezmurochh 💛   ✥
   ✥ ❤ @mezmurochh ❤   ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

Показано 20 последних публикаций.