☄️ሰሌክታ ግሩፕ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከኢትዮጵያ ወጣ
በስዊዘርላንድ ዋና መስሪያ ቤቱን ያደረገው ሰሌክታ ግሩፕ በሰሜን ኢትዮጵያ ኩንዚላ የሚገኘውን የምርት ማዕከሉን በፖለቲካ አለመረጋጋት እና በወታደራዊ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ ኬንያ እና ኡጋንዳ ማዛወሩን አስታዉቋል።
ኩባንያው የዚህ ውሳኔ ምክንያት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ለሰራተኞች ደህንነት ስጋት መፍጠሩ እና የሎጂስቲክስ ችግሮች መከሰታቸው እንደሆነ ገልጿል።
የኩባንያዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንስጋር ክሌም ይህን ውሳኔ "አሳማሚ እርምጃ" ብለው የገለፁት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እና ጥረት ከንቱ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ውሳኔ በኩንዚላ አካባቢ ከ1,000 በላይ የስራ እድሎችን የሚያሳጣ ሲሆን፣ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ወደ 10,000 የሚሆኑ ሰዎችን ይጎዳል። ኩባንያው ለአካባቢው ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ህይወት መስመር እንደነበር እና መውጣቱ ትልቅ ጉዳት እንደሚያስከትል ገልጿል።
ካፒታል ያገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሰሌክታ ግሩፕ በኬንያ እና ኡጋንዳ ያሉትን የምርት ማዕከላት በማጠናከር ለደንበኞች የምርት አቅርቦት እንዳይቋረጥ ማረጋገጡን ገልጿል። ወደፊት ሁኔታዎች ሲሻሻሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተስፋ እንዳለውም አስታውቋል።
ሰሌክታ ግሩፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የሆነ የአበባ እና የጌጣጌጥ እፅዋት አምራች ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል።
@seledadotio@seledadotio