የጋና ፕሬዝዳንት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዋና ዳኛን አገዱ
የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ የሀገሪቱን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ ከስራ አግደዋል፡፡ ይህ እርምጃ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ ነው።
ዳኛዋ ገርትሩድ ቶርኮርኖ ለመታገድ ያበቃቸው በዝርዝር ያልተነገሩ ሶስት ክሱች ቀርበው ምርመራ መጀመሩን ተከትሉ ነው፡፡
በጋና ውስጥ ያሉ ዋና ዳኞች የስልጣን ዋስትናን ያገኛሉ ፡፡ ከስራቸው ሊያሳግዳቸው የሚችለው ጥቂት ምክንያቶች ብቻ ሲሆኑ እነሱም የብቃት ማነስ እና የባህሪ ችግር ናቸው ይላል የቢቢሲ ዘገባ ።
የአቤቱታዎቹ ይዘት ለህዝብ ይፋ አልተደረገም፡፡ ዳኛዋም እስካሁም ምንም አስተያየት አልሰጠችም ፡፡ ይሆን እንጂ የጋና የቀድሞ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እገዳው የፍትህ ስርዓቱን ለማዳከም የተደረገ ሙከራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
"በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ በፍትህ አካላት ፣ በዚህች ሀገር ህገ-መንግስታዊ ስርዓት በዳኝነት ነፃነት ላይ የተደረገ ትልቁ ጥቃት ነው።"ብለዋል የቀድሞው ጠቅላይ አቃቤ ህግ፡፡
@seledadotio