👂 #ምን_ተሰማ⁉️ 👂
🤱 በቦሎኛ ከተማ የሚወለዱ ሁሉም ህፃናት ነፃ የማሊያ ስጦታ እንደሚሰጣቸው ተገለፀ 🧑🍼በጣሊያን ታሪካዊ ከሆኑ ከተሞች መካከል አንዱዋ ቦሎኛ ናት። ስፖርት በስፋት ከሚወደድባቸው የጣሊያን ግዛቶች መካከል አንዱዋ የሆነችው ቦሎኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነና በሴሪያ ምስረታ ወቅት ትልቅ አበርክቶ የነበረው በውቧ ከተማ ስም የሚጠራ ታላቅ የእግርኳስ ክለብ አላት።
ታዲያ ይህ የከተማው ብቸኛ ፕሮፌሽናል ክለብ ከከተማው አስተዳደር እና ከክለቡ የትጥቅ አጋር ተቋም ጋር በጋራ በመሆን በከተማው ለሚወለዱ ህፃናት የማሊያ ስጦታ እንዲሰጣቸው መወሰኑ ተሰምቷል።
የክለቡን እና የማኅበረሰቡን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የወደፊቶቹን የቦሎኛ ታማኝ ደጋፊዎች ለማፍራት ታስቦ የተወሰነው ውሳኔ ከሰሞኑን ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
ከውሳኔው በኋላም በሆስፒታሎች የሚወለዱ ህፃናት ወደ ቤታቸው ከማምራታቸው በፊት እዛው ሆስፒታል በልካቸው የተሰራውን ማሊያ እያገኙ እንደሆነ ተገልጿል።
@goferesportswear