የፋሲል ከነማ የቡድን አባላት በህመም ላይ ለሚገኙት የመቐለ 70 እንደርታው ምክትል አሰልጣኝ ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ ድጋፍ አድርገዋል
በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት በኢትዮጵያ እግርኳስ የራሱን አሻራ ያሰፈረው የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያና ዋልታ ፖሊስ ትግራይ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ የነበረው ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ በአሁኑ ወቅት በካንሰር በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ታሞ ይገኛል።በመሆኑም ህክምናው በሀገር ውስጥ የማይሰጥ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ወጥቶ እንዲታከም የህክምና ባለሙያዎች ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በመሆኑንም ለህክምናው ውጭ ሀገር በመሄድ እንዲታከም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ የቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች እና የአሠልጣኝ ቡድን አባላት መዋጮ በማድረግ የ50 ሺ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል።
የክለቡ አባላትም ሌሎች ክለቦች ይህንን መልካም አርዓያ ያለውን ተግባር ተቀላቅለው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ድጋፍ ለማድረግ 👇
ወ/ሮ ትብለፅ ገብረመስቀል
👉 የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ | 1000184557375
👉 ወጋገን ባንክ | 0952411530101