የ13 ዓመት ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ሰጥሞ ህይወቱ አለፈ።
በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሽሮሜዳ ታቦት ማደርያ አካባቢ የ13 ዓመት ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት፤ የተቋሙ ሰራተኞች በፍጥነት በስፍራው ቢደርሱም የታዳጊውን ህይወት ማዳን አልተቻለም፡፡
በቂ የሆነ የዋና ችሎታ ሳይኖር ዋና ውስጥ መግባት ለህይወት ያለውን አደጋ በመረዳት ወላጆች ልጆቻቸውን ሊቆጣጠሩ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተቆፍረው ክፍት የሚተው ጉድጓዶች አገልግሎት ካልሰጡ የመድፈን ተግባራትን መከወን አስፈላጊ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
#ኢፕድ
@ThiqahEth