Фильтр публикаций


በአዲስ አበባ ለስድስት ቀናት ያህል የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ተከልክሏል

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ መከልከሉን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ከዛሬ የካቲት 04/2017 ዓ.ም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ድረስ በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የማይቻል መሆኑን ቢሮው ከወዲሁ አሳውቃለሁ ብሏል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ዩክሬን የሆነ ቀን የሩሲያ ልትሆን ትችላለች - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “የሆነ ቀን ዩክሬን የሩሲያ ልትሆን ትችላለች” ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ዋሺንግተን ተኩስ አቁም እንዲደረስ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

በሰጡት አስተያየትም “ሀገራቱ ሥምምነት ላይ ሊደርሱም ላይደርሱም ይችላሉ፤ ዩክሬንም የሆነ ቀን የሩሲያ ልትሆነም ላትሆንም ትችላለች” ብለዋል።

ከተኩስ አቁሙ ጋር በተያያዘ በሩሲያ በኩል ዝግጁነት እንደሌለ ከፎክስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ዩክሬንም ከሥምምነቱ ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ ጋር በቅርበት የመስራት ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች።

ትራምፕም አሜሪካ ለዩክሬን ለምትሰጠው ድጋፍ በማዕድን መልክ ካሳ እንደምትፈልግ አስገንዝበዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ዴንማርካውያን የአሜሪካዋን ካሊፎርኒያ ለመግዛት ዘመቻ ጀመሩ

ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች እስካሁን ፊርማቸውን ያኖሩበት ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን እያንዳንዱ ዴንማርካዊ 18 ሺህ ዶላር እንዲያዋጣ ተጠይቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዴንማርክ ግዛት ስር ያለችውን ግሪንላንድ ለመግዛት ያቀረቡት ሃሳብን ተከትሎ ነው ዘመቻው የተጀመረው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሁለት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለማልማት ጨረታ ማዉጣቱን አስታወቀ!

ተቋሙ በሶማሌ ክልል ጋድ እና በአፋር ክልል ወራንሶ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመንግስት እና በግል አጋርነት ለማልማት ነዉ ጨረታ ማዉጣቱን የገለፀው።

ከአሁን ቀደም በመንግሥት እና በግል አጋርነት ማዕቀፍ ከንፋስ ኃይል 300 ሜጋ ዋት ለማመንጨት አሜአ ፓወር ከተሰኘ የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ኩባንያ ስምምነት በመፍጠር ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል፡፡

እነዚህ ሁለቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች 225 ሜጋ ዋት ኃይል በማመንጨት የኃይል ስብጥሩን ለማስፋት እንደሚያስችል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በኦሮሚያ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።አደጋው ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡

በደረሰው አደጋም የ26 ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 42 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዞኑ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር አስናቀ መስፍን ተናግረዋል፡፡በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ግብፅና ዮርዳኖስ የጋዛ ተፈናቃዮችን የማይቀበሉ ከሆነ የሚያገኙትን እርዳታ አቆማለሁ - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይት ኃውስ እንደገቡ የጋዛ ፍርስራሽ እስኪጸዳ ድረስ ፍልስጤማውያን እንደ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ባሉ ሀገራት እንዲጠለሉ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለማፈናቀል በያዙት እቅድ ላይ መጽናታቸውን በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን፤ ለመቀበል ፍቃደኛ ያልሆኑ ሀገራትን ማስፈራታቸውን ቀጥለዋል።

ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ፍልስጤማውያን ከጋዛ በቋሚነት ይወገዳሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

ፍሊስጤማውያን መቼ ወደ ጋዛ ይመለሳሉ ተብለው የተጠየቁት ትራምፕ፤ “አይ አይመለሱም፣ ምክንያቱም የተሻለ መኖሪያ ቤት ያገኛሉ፣ በሌላ አነጋገር እኔ የማወራው ለእነሱ ቋሚ መኖሪያ ቤት ስለመገንባት ነው” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አክለውም “በርካታ ፍሊስጤማውያንን አነጋግረናል፤ ሌላ የሚኖሩበትነን ስፍራ ካገኙ ጋዛን መልቀቅ እንደሚፈልጉ ነግረውናል” ሲሉም ገልጸዋል።

የጋዛ ተፈናቃይ ፍሊስጤማውያንን ለመቀበል ፍቃደኛ ያልሆኑ ሀገራትን በተመለከተም ዶናልድ ትራምፕ “እኛም ለእነሱ የምንሰጠውን እርዳታ እናቆማለን” ሲሉ ዝተዋል።

ግብፅ እና ዮርዳኖስ ፍሊስጤማውያንን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆኑ ከአሜሪካ የሚያገኙት እርዳታን ሙሉ በሙሉ እንደሚያቋርጡም ነው ትራምፕ ያስታወቁት።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ከነገ የካቲት 05/2017 ዓ.ም ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰሩ አሸከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ መቁም አይቻልም ተብሏል

በኮሪደር ልማት በለሙና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት ተሽከርካሪ በመንገድ ዳር ማቆም እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ፥ ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከተለያዩ የአፍሪካ ብሎም የዓለም ሀገራት እንግዶች አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን አንስቷል።

ስለሆነም ከዛሬ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ማታ 12:00 ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር ማቆም እንደማይቻል አስታውቋል።

በኤሌክትሮኒክ ክፍያ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ፣ የሜትር ታክሲ፣ የላዳ፣ የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች መልዕክቱን እንዲተገብሩም ቢሮው አሳስቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በትግራይ ወቅታዊ ጉዳይ ለመወያየት የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን መቀለ መግባታቸው ተገለጸ!

የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም መቀለ መግባታቸው ተገለጸ።ልዑካኑ መቀለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር፣ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ እና በክልሉ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከሳለፍነው አመት መገባደጃ ጀምሮ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የሆኑት ኤርቪን ማሲንጋን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ተወካዮች ወደ ትግራይ በማቅናት በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ትኩረት ያደረገ ጉብኝቶች ሲያደርጉ እንደነበር ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


"ወደ ሀገሬ እንዳልገባ ተከልክያለሁ" ያሉት አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ ሀገር አየር መንገድ አማካኝነት ወደ #ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ገለጹ!

በ #አሜሪካ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው "ወደ ሀገሬ እንዳልገባ ተከልክያለሁ" ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።ነገር ግን ይህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል እንደጣለባቸው የተገለጸላቸው የጉዞ ዕገዳ ቢኖርም፣ በሌላ ሀገር አየር መንገድ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ለየካቲት 3/2017 ዓ.ም. የአውሮፕላን ቲኬት ቆርጠው በአትላንታ አየር ማረፊያ ቢገኙም መሳፈር እንዳልቻሉ አስታውቀዋል።"ቲኬቱ የተረጋገጠ ነው።ፖስፖርቴም ለሚቀጥሉት 11 ወራት የሚያገለግል ነው" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት አቶ ልደቱ፤ ነገር ግን አየር ማረፊያ ሲደርሱ "በአሜሪካ የኢትዮጵያን ኤምባሲን" አነጋግረው ልዩ ፈቃድ ካላገኙ መጓዝ እንደማይችሉ እንደተናገራቸው ገልፀዋል።

አክለው ከሥራ አስኪያጁ [የአየር መንገድ] የተሰጣቸው ምላሽ "እገዳ ስተለጣለብህ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም" የሚል እንደሆነ ጠቁመው "አሜሪካ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመልክተህ በእነሱ በኩል እገዳው ካልተነሳልህ መብረር አትችልም" መባላቸውን አስታውቀዋል።"በሌላ አየር መንገድ ቲኬት ለመቁረጥ እየተዘጋጀሁ ነው። አዲስ አበባ ስደርስ ደግሞ የሚሆነው አያለሁ።ወደ ሀገር እንዳልገባ ለመከልከል የሚያስችል ምንም ዓይነት ሕግ የለም" ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ሐማስ ታጋቾችን እንደማይለቅ አስታወቀ።

በቀጣዩ ቅዳሜ ይለቀቃሉ ተብሎ ሲጠበቁ የነበሩ ሦስት እሥራኤላዊያን ታጋቾችን እንደማይለቅ ሐማስ አስታውቋል።ሐማስ ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረሱ እንደ ምክንያትነት የጠቀሰው እሥራኤል የተኩስ አቁም ሥምምነቱን ጥሳለች ብሎ ማመኑ ነው ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐማስ በመጪው ቅዳሜ ሁሉንም ታጋቾች የማይለቅ ከሆነ የተኩስ አቁም ሥምምነቱ ሊሰረዝ እንደሚገባ ጠቅሰው ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን "እሥራኤል የፈቀደችውን ማድረግ ትችላለች" ብለዋል።የእሥራኤል የመከላከያ ሚኒስትር እሥራኤል ካትዝ ይህንን የሐማስ ውሳኔ "የተኩስ አቁም ሥምምነቱን ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስ ነው" ብለውታል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የቦንብ ጥቃት

በትግራይ ክልልጰሽሬ ከተማ በተወረወረ ቦንብ ንፁሃን ላይ ጉዳት ደረሰ

ትናንት ምሽት በሽሬ ከተማ በተለምዶ ሀረግ ፓርክ በተባለ ሰፈር ቦንብ ተወርውሮ ንፁሃን ላይ ጉዳት ደርሷል። በተወረወረው የቦንቦ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸው የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በተጨማሪ መረጃ በዚሁ አካባቢ በጥር ወር ተመሳሳይ ቦምብ ተጥሎ ሳይፈንዳና ጉዳት ሳያደርስ እንደቀረ ታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በቤንሻንጉል ጉምዝ ከ200 በላይ የጤና ኬላዎች በጸጥታ ችግር ወድመዋል

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ200 በላይ የጤና ኬላዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት መውደማቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል። በአጠቃላይ 426 የጤና ኬላዎች ከሚገኙበት በክልሉ፣ 211 የሚሆኑት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ወድመዋል።

የክልሉ የሕጻናት፣ እናቶች እና ወጣቶች ጤና ቢሮ ዳይሬክተር አብደል ፈታህ በርሄ እንደገለጹት፣ ግጭቶች በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። በተለይም እናቶችና ህጻናት ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል በዚህም በግማሽ ዓመቱ ብቻ 140 ሰዎች በቂ የህክምና አገልግሎት ባለማግኘታቸው ህይወታቸው አልፏል።

በተጨማሪም በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭት እና የኮሌራ ወረርሽኝ ስጋት ተደቅኗል። በኮሌራ ወረርሽኝ ብቻ በግማሽ ዓመቱ 900 የሚጠጉ ሰዎች የተያዙ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም 3% ደርሷል።

ይህ ዜና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለውን የጸጥታ ሁኔታ እና በጤናው ዘርፍ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ ያሳያል። ግጭቶች የጤና አገልግሎት አቅርቦትን በማስተጓጎል እና በህዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የግብርና የምርምር ማእከላት አመታዊ ግብር እንዲከፍሉ ተጠየቁ።

በሀገሪቱ የሚገኙ የግብርና ምርምር ተቋማት ግብርናን በምርምር ለመደገፍ የተቋቋሙ ቢሆንም ትኩረት እንዳልተሰጣቸዉ ይነሳል።

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኘሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ፤ በአንዳንድ የምርምር ማእከላት ለትርፍ እንደተቋቋመ ተቋሙ ታይተዉ ግብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዉ እንደነበር አንስተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በምሳሌነትም በሰበታ የአሳ ምርምር ማእከል 1.3 ሚሊየን ብር ለአመታዊ ግብር ክፈሉ መባሉን ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ በተባሉ የምርምር ማእከላት ላይ የዚህ የግብር ክፈሉ አዝማሚያዎች መታየታቸውን ተናግረዋል።

የግብር ክፈሉ ጥያቄዎቹ ከህገመንግስታዊ ድንጋጌ ዉጪ ነዉ የሚሉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የግብርና ምርምር ማእከላቱ ላይ የተጣለባቸዉን አመታዊ ግብር አግባብነት የማይኖረዉ ነዉ ብለዋል።

ይህንን ለማስቆም ከክልል መስተዳድሮች ጋር ንግግሮች መደረጋቸዉን አንስተዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በፖሊስ SWAT ውድድር የተሳተፈው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 101ኛ ወጣ

ላለፉት ጥቂት ቀናት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ዱባይ ከተማ በተካሄደው እና የ103 ሀገራት የSWAT ፖሊስ ቡድን አባላት በተሳተፉበት ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 101ኛ መውጣቱ ታውቋል።

ይህ Special Weapons And Tactics (የልዩ መሳርያዎች እና ታክቲኮች) የቡድን ውድድር ላይ የቻይና B ቡድን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፣ የካዛክስታኑ ሱንካር ፖሊስ ሁለተኛ እንዲሁም የቻይና C ቡድን ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በ SWAT ውድድሩ ላይ ሲወዳደር የቆየው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቡድን ከሁለት ቀን በፊት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስትራቴጂክ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ እንደ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ የፖሊስ ተቋም በተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች SWAT ውድድር ላይ መሳተፉ ለሀገራችን ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ ከማስገኘቱም ባሻገር ዓለም አቀፍ የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትን ለማዳበር ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የፖሊስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ውድድር ላይ መሳተፍ መቻላችን ልምድና ተሞክሮ እንድናገኝ ያስቻለን ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም እ.ኤ.አ 2026 በሚካሄደው ውድድር ላይ አስፈላጊውን ስልጠና በመውሰድ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት እንሠራለን ሲሉም ገልፀዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ግዴታ ሆኗል‼️

በአካል ኢትዮጵያ ውስጥ የማይገኙ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደ ዩናይት ዶት ኢቲ ያሉ አማራጮችን ተጠቅመው ፋይዳን ሳይዙ የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ ተገልጿል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደ ቅደመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ብሔራዊ ባንክ አቅጣጫ ማስቀመጡን ያስታወሰው መረጃው ይህው አሰራርም በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን እንዲያካትት መደረጉን ነው የተናገረው።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የውጪ ሀገር ዜጎችንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያጠቃልል መሆኑ ጭምር የተገለፀ ሲሆን መመሪያው በብሔራዊ ባንክ መውጣቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ መሥሪያ ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በአማራ ክልል የዳኞች ያለመከሰስ መብት እንዲጠበቅ ባለመደረጉ ዳኞች ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጡ ነው ተባለ።

የዳኞች ያለመከሰስ መብት በአማራ ክልል ምክር ቤት ቢቀርብም የዳኞችን መብት የሚያስጠብቅ ሕግ አለመውጣቱ ተገልጿል፡፡

ጉዳዩ ሁለት ጊዜ ያህል ለክልሉ ምክር ቤት ቢቀርብም በአዋጅ እስካሁን አለመጽደቁም ተነስቷል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው የህግ ባለሞያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ፤ ክልሎች የፌድራሉን ህገ መንግስትን ተከትለው ህግ እንዲያወጡ በማንሳት አንዱ ክልል ፀድቆ ሌላው ጋር አለመፅደቁ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብለዋል።

የህግ ባለሞያው አቶ ጥጋቡ ይህ ችግር እንዲስተካከል የዳኞች ማህበር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተለይም ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በስፋት መጠየቅ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

አቶ ጥጋቡ ጠንካራ የዳኝነት ተቋም እንዲኖርና ሕዝቡ በፍርድ ቤቶችና በዳኞች ላይ እምነት እንዲኖረው፣ በአንድ አገር ውስጥ የዳኝነት ነፃነት መስፈንና መረጋገጥ አለበትም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር የዳኞች እስር ችግሩ ሲንከባለል የመጣ ቢሆንም በ2017 ዓ.ም ግን የከፋ ሆኗል ማለቱ ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


“የጋዛ ነዋሪዎችን ከዘላለማዊ የትውልድ ሀገራቸው ማስወጣት አይታሰብም”- ኤርዶጋን

ቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “የትኛውም ኃይል ፍልስጤማውያንን ከትውልድ ሀገራቸው ማስወጣት አይችልም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ትራምፕ ጋዛን ለመቆጣጠር የያዙትን እቅድ ውድቅ በማድረግ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በመግለጫቸውም “የትኛውም አይነት ኃይል የጋዛ ነዋሪዎችን ከዘላለማዊ የትውልድ ሀገራቸው ማስወጣት አይችልም” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ጋዛ፣ ዌስት ባንክ እና ምስራቅ እየሩሳሌም የፍልስጤማውያን ናቸው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ትናንት ምሽት በኢስታቡል በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ትራምፕ ፍሊስጠየማውያንን ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር ጋዛን ለመቆጣጠር የያዙትን እቅድ ያነሱ ሲሆን፤ የአሜሪካ አስተዳር በጺዮናዊ አስተዳር ተገፋፍቶ ያወጣው እቅድ መሆኑን እና ለውይይት የማይበቃ እርባና ቢስ መሆኑንም አስታውቀዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


ኢትዮጵያ ያለባትን ዕዳ የምትከፍልበትን መንገድ ለማመቻቸት ከአበዳሪዎች ጋር የምታደርገው ድርድር «የመጨረሻ ደረጃ» ላይ መድረሱን የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ ተናገሩ።

አህመድ ሺዴ ይህን ያሉት ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክሪስቲና ጆርጂዬቫ ጋር አዲስ አበባ ውስጥ ከተነጋገሩ በኋላ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ነው።ኢትዮጵያ በኤኮኖሚ የበለጸጉ ሃገራት ጥምረት በቡድን 20 አነሳሽነት ዕዳዋ መልሶ እንዲዋቀር ለረዥም ጊዜ ብርቱ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ሮይተርስ ዘግቧል።

ጥረቱ ዉጤት ሳያስገኝ አዝጋሚ ሆኖ መቀጠሉን የጠቀሰው ዘገባው በጎርጎርሳዊው 2023 ከአበዳሪ ሃገራት በቦንድ ሽያጭ የተበደረችውን (ዩሮ ቦንድ) እና መክፈል የሚጠበቅባትን ወለድ መክፈል ባለመቻሏ የውጭ ዕዳ ወለድ መክፈል ከተሳናቸው ሦስት የአፍሪቃ ሃገራት አንዷ ተብላ ተሰይማለች።ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ በጋራ የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት ``ዕዳውን መልሶ ለማዋቀር የሚደረገው ድርድር የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሷል።``

ኢትዮጵያ ባለፈው የሰኔ ወር መጨረሻ ያለባት የውጭ ዕዳ 28.9 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ አይ ኤም ኤፍ፣ የዓለም ባንክ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ያሉ የባለ ብዙ ወገን አበዳሪዎች ዕዳ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክርሲቲና ጆርጂዮቫ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የኢትዮጵያን ዕዳ መልሶ ማዋቀር ጉዳይ በቀዳሚነት ከያዟቸው ጉዳዮቻቸው አንዱ መሆኑን አንስተዋል።ኢትዮጵያ ባለፈው የሀምሌ ወር ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ጋር የ3.4 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የመዋዕለ ነዋይ መርኃ ግብር ስምምነት ደርሳለች።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


በስድስት ወራት ውስጥ በወሊድ 620 እናቶች እንዲሁም በረሃብ 352 ህጻናት ህይወታቸው አለፈ

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ ከወሊድ ጋር በተያያዘ 620 እናቶች እና በረሃብ 352 ህጻናት መሞታቸውን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በቀረበው ሪፖርት 620 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፣ ነገር ግን የሞታቸው ምክንያት በዝርዝር አለመብራራቱን የገለጸው ዘገባው ይህም በቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ በማስነሳት የሪፖርቱን ተዓማኒነት አጠራጣሪ እንደሚያደርገው ተመላክቷል ብሏል፡፡

አቶ ተስፋሁን ቦጋለ የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል ከቀረበው ሪፖርት በመነሳት ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ እናቶች የሞት ምክንያት ለምን በዝርዝር ማቅረብ እንዳልተቻለ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ባለፉት ስድስት ወራት በአገር ደረጃ ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱ በሪፖርቱ የተመለከተ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት 352 ሕፃናት ሲሞቱ 232‚389 ሕፃናት ደግሞ ለሕመም መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የወባ ወረርሽኝ ከ2016 ዓ.ም. ተመሳሳይ ዕቅድ አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር፣ በሁለት እጥፍ በመጨመሩ ለበርካታ ዜጎች ሕመምና ሞት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1


የኢትዮጵያ “ፈታኝ” የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ “አስደናቂ ውጤቶች” ይዞ የሚመጣ ነው ሲሉ የአይኤምኤፍ ኃላፊ ተናገሩ!

የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ፣ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በተግዳሮቶች የተሞላ መሆኑን አስታውቀው፣ የኢኮኖሚ ማሻያው “ፈታኝ” ሲሉ በመግለጽ “ጊዜ የሚወስድ” መሆኑንም ጠቁመዋል።

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ጉብኝት አካሂደዋል፤ በጉብኝታቸውም ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

የማሻሻያ እርምጃዎቹ መካከል “አንዳንዶች ቀድሞውኑ ግልጽ እየሆኑ ነው” ያሉት ዳይሬክተሯ “ህብረተሰቡም በኢኮኖሚ ማሻሻያው ላይ አንድ በመሆን ሊደግፍ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል።

ባለፈው አመት 2024 ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የ8 ነጥብ አንድ በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ተቋማቸው ተንብዮት ከነበረው የስድስት ነጥብ አንድ በመቶ እድገት ብልጫ ያለው መሆኑን በመጥቀስ "ኢትዮጵያ የምትኮራበት ብዙ ነገር አለ" ሲሉ አስታውቀዋል።

የኢኮኖሚ መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ ለቀጣይ የኢኮኖሚ እድገትና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት በማሳየት ለሌሎች የአህጉሪቱ ሀገራት ተምሳሌት እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል።

በተለይም የፊስካል ፖሊሲዉን በማሳደግ፣ የኢኮኖሚዉን መዋቅራዊ ችግሮችን በመፍታት እና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት የዜጎችን የኑሮ ደረጃን የሚያሻሻሽል መሆኑን ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Показано 20 последних публикаций.