በስድስት ወራት ውስጥ በወሊድ 620 እናቶች እንዲሁም በረሃብ 352 ህጻናት ህይወታቸው አለፈ
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ ከወሊድ ጋር በተያያዘ 620 እናቶች እና በረሃብ 352 ህጻናት መሞታቸውን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
በቀረበው ሪፖርት 620 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፣ ነገር ግን የሞታቸው ምክንያት በዝርዝር አለመብራራቱን የገለጸው ዘገባው ይህም በቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ በማስነሳት የሪፖርቱን ተዓማኒነት አጠራጣሪ እንደሚያደርገው ተመላክቷል ብሏል፡፡
አቶ ተስፋሁን ቦጋለ የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል ከቀረበው ሪፖርት በመነሳት ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ እናቶች የሞት ምክንያት ለምን በዝርዝር ማቅረብ እንዳልተቻለ ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት ስድስት ወራት በአገር ደረጃ ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱ በሪፖርቱ የተመለከተ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት 352 ሕፃናት ሲሞቱ 232‚389 ሕፃናት ደግሞ ለሕመም መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የወባ ወረርሽኝ ከ2016 ዓ.ም. ተመሳሳይ ዕቅድ አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር፣ በሁለት እጥፍ በመጨመሩ ለበርካታ ዜጎች ሕመምና ሞት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
https://t.me/voa_amharic1