የእመቤታችን መከራዋን ማሰብ
✝መስቀል ተሸክሞ ወደሞት ሲሄድ ያየችው ጊዜ✝
በፍጡራን መካከል ካለ ፍቅር በጥልቅ የምትወድ እንደ እናት ማንም የለም። እጅጉን የጠበቀ ነው የሚባለው የባልና ሚስት ፍቅር እንኳ እናት ለልጇ ካላት ፍቅር አይተካከልም ለምን ቢሉ ባል ከሚስቱ የሚፈልገው የሚስት ፍቅር ስላለ ነው የወደዳት ሚስትም ከባሏ የምትሻው ፍቅር ስላለ ነው የወደደችው። እናት ግን የምትወደው ልጇ ስለሆነ ብቻ ነው። ማንም ሰው እናቴ የምትወደኝ ከዚህ ተነስታ (on account of this....) ብሎ መናገር አይችልም።
እናት ደስታዋ ከልጇ በምታገኘው ነገር ሳይሆን ለልጇ በምትሰጠው ነገር ነው። ደስታዋም የልጇ መሆንና አለመሆን ነው። እናት ልጇ ራሷ ለእናትነት ደርሳም ቢሆን ዛሬም እንደታናሽነቷ ታስብላታለች። እናት የምትኖረው ለልጇ ነው። ደስታዋም ልጇ ነው። የልጇ ስብራት የእርሷን ያህል እኩል ይሰማታል። የእናት ምጥ የወለደች ልት ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ልጆቿ በተጎዱ ቁጥር ልቧ በኀዘን ሰይፍ ይወጋል። አንድ ደራሲ እናት ስለልጇ የምታዝነውን ኀዘን "All mother feel the suffering of their children as their own. ሁሉም እናቶች የልጆቻቸውን መከራ እንደራሳቸው ይሰማቸዋል" ሲል የገለጸው እርግጥ ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ አንዲት ሴት ልጇን ጋኔን አሞብባት ነበርና ወደ ጌታ መጥታ እየጮኸች "ልጄን አሞብኛልና እባክህ እርዳኝ" ብላ ነበር የለመነችው። ማቴ15÷22
ልብ በሉ ይህች ሰው ጌታን "እባክህ ልጄን እርዳት" አላለችም ይልቁንም የልጇን ኀዘን እንደራስዋ ቆጥራ ይሰማት ነበርና "እባክህ እርዳኝ" አለችው እንጂ። እናስተውል ይህች ሴት ልጇ ታማለች እንጂ የሚደበድባት የለም፣ እናቷም የማስታመም እድል አላት፣ የሞት ፍርድ አልተፈረደባትም ግን የታመመች ብቻ እናቷ እስክትጮህ ድረስ አለቀሰች እንጂ።
እስኪ የእመቤታችንን ኀዘን እናስብ
ጌታ ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ጎልጎታ አስራ አራት ምዕራፎች ያሉት የመስቀል ጉዞ አድርጓል። አራተኛው ከእናቱ ጋር የተያዩበት ቦታ ነው። ወዮ ያቺ ሰአት ምን ያህል አስጨናቂ ናት። እናት ልጇ ሲነግስላት፣ ዘውዱ ሲደፋላት ደስ ይላታል ድንግል ግን አንዱን የድንግልናዋን ፍሬ ራሱን የሚበሱ የእሾህ ጉንጉኖች በራሱ ላይ ደፍቶ አየችው። ከእነዚያ አንዱን እሾህ እንኳን ለልጇ መንቀል አለመቻሏ ለድንግሊቱ እናት ምን ያህል መራራ ነው።
እሾሁን ልትነቅልለት ይቅርና እየወደቀ እየተነሳ ሲገረፍ ሲዳፋ ያደረ በደም የተሸፈነ ፊቱን ለማየትስ እንኳን እድል አላገኘችም። የልጇን ደስታ ለምትሻ እናት የመከራ ፊቱን አቅፋ እንዳታለቅስ እንኳን ስትከለከል እንደምን ያለ የተሳለ የኀዘን ሰይፍ ወግቷት ይሆን። ወየው እመቤቴ አዕላፈ እስራኤል በልጅሽ ላይ እየደነፉ ላንቺ አንድስ እንኳን የሚያረጋጋ አልነበረሽም። ስቃዩ ገርፈው ይለቁታል እንዳይባል ደግሞ እንደዚያ እያደረጉ የሚወስዱት ሊገድሉት መሆኑ ሰይፉ ይበልጡን ልብዋን እንደምን ይወጋው።
የእናት ሀዘን ለታመመች ልጅ የሚያስጨንቅ ከሆነ አጥንቱ እስኪቆጠር ተገርፎ ሊሞት የሚወስደን ልጇን ለምታይ ድንግልማ ምን ያህል የሀዘን ሰይፍ ይሆን? ነብዩ ኤርምያስ የሚያጽናናኝ የነፍሴን የሚያበረታታት ከእኔ ርቋልና ስለዚህ አለቅሳለሁ። አይኔ ውሃ ያፈሳል ፣ ጠላት በርትቷል ፣ ልጄም ጠፍቷል ብሎ እተናገረው ያላጽናኝ እየተገፋፋሽ ባለቀሰሰሽ በድንግል ተፈጸመ። ሰቆ 1÷15 እመቤታችንን የምንወዳት ይህንን የመሰለው መከራዋ ሲረዳን ነው።
አሐቲ ድንግል ገጽ 553 - 554
በአባ ገብረ ኪዳን ግርማ
https://t.me/abagebrekidan