የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ የፍቅር ቴሌግራም™ ❤
💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ
💜ድርሰቶች
💚የፍቅር ግጥሞች
💛ጣፋጭ ታሪኮች
❤️ምክሮች ...
አልፎ አልፎ ቀልዶች ይለቀቁበታል 😂

Since 2016 e.c
❤️ከናተ ሚጠበቀው 𝐉𝐨𝐢𝐧 to request በማረግ ብቻ መከታተል ነው ❤️
👇👇👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: EXO DISK ቤት
🇬🇧 🇬🇧 🥇 🏆 🏆 🏆

ከእነዚህ ዉስጥ የማን ደጋፊ ኖት??

የምትደግፉትን ክለብ ስም በመጫን ተቀላቀሉ⬇️


Репост из: EXO DISK ቤት
🎬🍿 ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN አርጋቸው እነዚህ ቻናሎች ምርጥ ምርጥ የጦርነት እና የጫካ የአክሽን ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያሉ መርጣችሁ ተቀላቀሉ ⬇️

https://t.me/+qEB5fouDhl9kZmQ8
https://t.me/+qEB5fouDhl9kZmQ8


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል 
9️⃣


ሱቅ ገብቼ ፊቴ አይፈታ እንዲሁ እንደደበረኝ ገብቼ ሰወጣ ሀና ደጋግማ የሆንኩት ነገር ካለ ጠየቀችኝ የማወራው ሰው ፈልጌ ነበር በቃ ቁጭ ብሎ ሳይሰለች ሚሰማኝ ልክ እንደንሰሀ አባቴ ሀጥያቴን ሁሉ ምናዘዝበት ሰው ፈልጌ ነበርና ማታ ነግርሻለሁ አሁን ከስተመር ስለሚበዛ ተረጋግተን ማውራት አንችልም አልኳትና ማታ ላይ በጊዜ ሱቅ ዘግተን ሁሌ ወደምሄድበት ቤት ሄደን ቁጭ አልን።

አንተ ግን በጣም እንደከፋህ ያወኩት የውስጥህ ቁስል ፊትህ ላይ መነበብ ሲጀምር እንደጓደኛ ካየኸኝ ንገረኝ ውስጥህ ግን ለኔ መንገርህ ልክ እንዳልሆነ ከነገረህ ተወው አለችኝ፡፡ በሰአቱ ማውራት ብቻ ነው የፈለኩት በቃ ሚያዳምጠኝ ሰው ፈልጌ ስለነበር ከመጀመሪያው ጀምሮ ታሪኬን መተረክ ጀመርኩ።

እናትና አባቴ ፍቅር የሞላበት : ነበሩ በቃ ሚዋደዱ ፍቅር ማንን ይመስላል ቢባል እነሱን ማለት ይቻላል እናቴ አባቴ ካልመጣ ምግብ ሚባል አትቀምስም አባቴም ቢሆን ስራ ሰርቶ ገንዘብ ሲያገኝ ለሚስቴ ብሎ ልብስ ገዝቶ ይመጣል እሱ አናፂ ነው እሷ ደሞ የቤት እመቤት በፍፁም ፀሀይ እንዲነካት እንድትገላታበት አይፈልግም ለደቂቃ እንዲቸግራት እንድትሳቀቅ አድርጓት አያቅም ሁሌም ቢሆን ከራሱ በላይ ያስብላታል ይንከባከባታል ይወዳታል ከዛ እኔ ተረገዝኩ የመውለጃ ቀኗ እንደደረሰ አላወቀችም ነበር ድንገት ምጧ ሲመጣ ጎረቤት አፋፍሶ ወደሆስፒታል ወሰዳትና እኔ ተወለድኩ ጎረቤቶቻችን ለአባቴ ደውለው እንደወለደች ሲነግሩት በደስታ ብዛት እራሱን አያውቅም ግን ሚስቴ ደና ናት ምንም አልሆነችም ወይኔ በዚህ ሰአት ከጎኗ ሳልሆን እያለ እያወራ እንዴት እንደሆነ ሳይታወቅ ከአስራ አንደኛ ፎቅ ላይ ወድቆ ሞተ።

እኔ ወደምድር ስመጣ እሱ ወደመቃብር ቸሸኘ እናቴ የአራስ ደሟ ሳይቆም ለቅሶ ላይ ዋለች በቃ ይቺ ሴትዮ ትሞታለች ሰው አትሆንም ልጁም ይሞታል እያለ ሰው ሁሉ ሲያወራ እኔም እናቴም በህይወት ቆየን ስሜንም ታምራት
አለችኝ፡፡

ከአባቴ ሞት ቡሀላ እናቴ ያለሆነችውን ሆና አሳደገችኝ አንድም ቀን ሳይርበኝ ሳይጠማኝ በደና ቀን ካባቴጋ የሰሩትን የሚከራይ ቤት እያከራየን ከዛም ተጨማሪ እናቴ የሴት ወንድ ሆና ሰው አድርጋ አቆመችኝ እኔ አድጌ ግቢ ከመግባቴ በፊት ግን ግቢያችን ውስጥ ከእናቷጋ ምትኖር ፅናት ምትባል ልጅ ተከራይታ ገባች በቃ ጥንቅቅ ያለች ቆንጆ ናት አቋሟ ያምራል ፀባይዋ ማንንም ይገዛል ድርብብ ያለች ናት ሰውን ቀና ብላ አታይም ፀጉሯ እስከቂጧ ተንዘርፍፎ ሳየው ልቤ ስንጥቅ ይላል በቃ ልቅም ያለች ሰው ናት ግን አንድ ነገር ይጎላት ነበር እሱም ሀብታም መሆን ነው።እኔ ግን በቃ የመጀመሪያ ያየኋት ቀን አፍቅሪያት ጨርሻለሁ።

እሷ ግን እኔን ልትወደኝ ልትቀበለኝ አልቻለችም ለሷ ስል ከግቢ ቀረሁ ለሷ ስል ጎበዝ ሰራተኛ ትሁት ጨዋ ወንድ ሆንኩላት ከራሴ በላይ ስላፈቀርኳት እሷን የኔ ለማድረግ ከሶስት አመት በላይ ተሰቃይቻለሁ ያያት ሁሉ ስለሚወዳት ከዛሬ ነገ አንዱ ቀማኝ እያልኩ ወጥታ በገባች ቁጥር እሳቀቅ ነበር።

ከስንት ልመናና ስቃይ ቡሀላ እሷም እሺ አለችኝ ከድሮ ጀምሮ እንደምትወደኝና ግን አፍቅሮ ማጣትን ስለምትፈራ ከኔ እየራቀች እንደቆየች ተሰቃይታ ያሰደገቻትን እናቷን መካስ እንደምትፈልግ ነገረችኝ።

ከዛ በቃ የራሳችን ስራ ለመጀመር ብዙ እቅዶችን ማቀድ ጀመርን አብረን ለማደግ ተስማማን እሷም እኔም ስራ ሳንመርጥ እየሰራን ፍቅራችንን እያጧጧፍን በመሀል ለፅናት ሀብታም ባል መጣላት የሷንም የናቷንም ህይወት የሚቀይርላቸው ሀብታም ሰውዬ ላግባት ዳሪልኝ ብሎ እናቷጋ ሽማግሌ ላከ እናቷ ግን ልጄ እራሷ ትወስን እኔ በሷ ህይወት አላዝም ህይወታችንን እንቀይር ላግባው ካለች እሰየው ካልሆነ ግን እሷ የራሷ ምትወደው ምታፈቅረው ሰው ካለ አላስገድዳትም አለች፡፡



ይቀጥላል...



🔻ክፍል1️⃣0️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ቤተሰብ አንዴት ናችሁ   ሀና  ክፍል 9  ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል 
8️⃣ 



አይ ሀኒ እኔ በራሴ ነው የሳኩት ይልቅ ሙዜቃውን ትንሽ ድምፅ ጨምሪበት ደሞ ከዚህ ሰውዬ ውጭ ዘፈን አታውቂም እንዴ አልኳት።

ባክህ እኔ በቃ ሙዚቃ ከተባለ ፀጋዬ እሸቱ አበባ ደሳለኝና ሸዋንዳይ ሀይሉ ናቸው ጭንቅላቴ ውስጥ ሚመጡት ግን ብዙ ማደንጋቸው ዘፋኞችም አሉ ብላ የፀጋዬ እሸቱን ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርጋ ከፈተችው።

የሚገባሽ የሚሰማሽ መስሎኝ በቁም ነገር ስተርክ መውደዴን ሳይሆንልኝ ጊዜዬን ጨረስኩት ስዘረግፍ አውጥቼ የሆዴን እያለ ያቀነቅናል እኔ ምልሽ ግን ጥሩ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሆነሽ የሚወድሽ የሚያፈቅርሽ ሰው እያለ እንደዚህ አይነት ሙዚቃ ለምን ትሰሚያለሽ አልኳት፡፡

ምን መሰለህ ታሜ እኔ በእርግጥ ዘፈኖቹን ዝም ብዬ ደስ ስለሚሉኝ ነው ምሰማቸው ግን እያንዳንዱ ዘፈን ምስት ብለህ ከሰማኸው ሁሉም ሙዚቃ ጥልቅ መልእክት አለ ሞር ደሞ የሆነ ሙዚቃ ያለህበትን ስሜት በትክክል ከገለፀልህ ትወደዋለህ እኔ ግን ስለሚመቸኝ ነው ምሰማው አለችኝና ቆን ፍቅርጋ ልደውልልት ብላ ስልኳን አንስታ ወደጆሮዋ አስጠጋችው።

ማታ ላይ ሀናን ቤት አድርሼ እኔም ወደቤቴ ሄድኩ ቤዛ ከፈተችልኝና እላዬ ላይ ተጠመጠመችብኝ ግን ጠረኗ ደስ አይልም ነበር ፀጉሯ እርስ በራሱ ተያይዞ አየሁትና ሰውነቴ ልክ አደለም ሻወር እንውሰድ እንዴ አልኳት።

እሺ ብላኝ ወደውስጥ ገባንና ልብሳችንን አወላልቀን ገንዳው ውስጥ ተዘፍዝፈን እኔ ገላዋን እያሸኋት እኔ ምልሽ ቤዚ ለምን ሁሌ ማታ ማታ ገላችንን አንታጠብም ስልሽ እኔም ቀኑን ሙሉ ሲያልበኝ ምን ስል ምን ስል ስለምውል ቤት ስገባም ድካሜ እንዲጠፋ ሁሌም ማታ ማታ ሻወር እንውሰድ አልኳት።

ከት ብላ ሳቀችና በየቀኑ ውሀ ውስጥ ስንዘፈዘፍ
ሞቅሙቀን እንድንሞት ነው እንዴ ሲጀመር አንተ ሁሌ ወደውጭ ስለምትወጣ ታጠብ እኔ ቤት ለምውለው ሁሌ ምን አስታጠበኝ ስወጣ ተጣጥቤ አደል ምወጣው
አለችኝ።

ዝም ብዬ አጥቢያት እኔም ታጥቤ በፎጣ እያደራረቅን ወጣንና ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን ፀጉሯን ሁለት ቦታ
ለመስራት ማበጠር ጀመርኩ።

እየሰሯኋት ቤዛ ግንኮ ገላሽን ለመታጠብ ወደውጭ መውጣት የለብሽም ለራስሽ አደል እራስሽን ምጠብቂው አልኳት ለመናገር እየፈራሁ ነበር ካሁን ካሁን ነገሩን ወደ ጭቅጭቅ ቀየረችው ብዬ እየተሳቀኩ ነው ቃላቶቹን ካፌ ሳወጣቸው የነበረው፡፡ እሷም እሺ በቃ ልክ ነህ አሁን አጨቅጭቀኝ ብላ ዝም
አለች፡፡

ፀጉሯን ሰርቻት እራት ለማቅረብ ወደኪችን ስገባ ምንም የለም እንዴ ቤዚ ምነው ምንም አልሰራሽም እንዴ?? አዎ በናትህ ፊልም እያየሁ ነበርኮ ለኔም ምሳ ቴካዌ አስደርጌ ስለበላሁ እራት ትዝ አላለኝም በቃ አሁን እንስራ አለችኝና ወደኪችን ገባን እሷ ካጠገቤ ቁጭ ብላ እያወራችኝ እራት ሰራርቼ በላንና ተኛን።

ይሄ ፍቅራችንና ሰላማችን ለሳምንት ያህል እንደቆየ ምን እንደተፈጠረ ሳይገባኝ አኮረፍችኝ እኔም ቤቱ አስጠላኝና ውጭ ማምሸት ጀመርኩ ሶስት ቀን ካኮረፈችኝ ቡሀላ ደግማ ደሞ ጠዋት ቀድማኝ ተነስታ ቁርስ ሰራርታ እስከበር ሸኝታኝ አስሬ እየደወለች የት ነህ ከመምጣትህ በፊት ንገረኝ ስትል ዋለች።
መልሰን ታረቅን ስል እንጣላለን ተጣላን ስል እንታረቃለን።

በቃ በህይወት ውስጥ የመጨረሻው አስቀያሚ ነገር ሰላም ያልሆነ ትዳር ነው ጭቅጭቅ ከመስማት ጠዋት ማታ ከመጨቃጨቅ መሞት በስንት ጣሙ በቃ ያስጠላል ድብርት ውስጥ ይከታል።


ይቀጥላል...



🔻ክፍል9️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ቤተሰብ አንዴት ናችሁ   ሀና  ክፍል 8 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
7️⃣

ከዛ በላይ ቃል አልተናገረችም አብረን አደርን ስነሳ ምግብ አዘገጃጅታ ቤቱን አሰማምራ ጠበቀችኝ። የውሸት ሳቅም ቢሆን እየሳኩ አብሪያት አመሸሁ።

በነጋታው ልብሴን ለባብሼ ወደስራ ለመውጣት ተዘጋጀሁ ቤዛ ከአጠገብ ከአጠገቤ እያለች እኔ ምልህ ይቺ ሀና ምትባለው ልጅ ግን ሼፓ እንዴት አባቱ ነው ሚያምረው አሮጊት ይመስል ረጅም ቀሚስ ታበዛለች ቆንጆ አቋም ነበራት አለችኝ። እኔጃ ቤዚ አስተውያት አላቅም ያምራል እንዴ??
አረ ባክህ አብራችሁ አደል እንዴ ምትውሉት እኔ ባንድ ቀን ያስተዋልኩትን እንዴት ይሄን ያህል ቀን ማስተዋል ከበደህ አለችኝ።

በቃ ካንቺጋ ሰላም አድሮ ሰላም መዋል ቅንጦት ነው አደል ስራ ልሰራ ነው ሱቅ ምገባው እሷ ተቀጣሪ እኔ ደሞ አለቃዋ ነኝ ስራችን ካላገናኘን ምን አገናኝቶን ነው የሷን የሰውነት ቅርፅ ጡትና ቂጥ እያየሁ ምውለው ቻው ብያት ወጣሁ።

መኪናዬን አስነስቼ ከወጣሁ ቡሀላ ከራሴጋ ክርክር እያደረኩ ነበር በቃ እንደምንም ብዬ በራሴ ስም ሱቅ መክፈት አለብኝ የለፋሁበትን ገንዘብ ሁሌ ጥገኛ ሆኜ መጠቀም የለብኝም ያሁኑን ሱቅ በሷ ገንዘብ ስለተነሳሁ ነው አደል እንደዚህ ምታንገበግበኝ በቃ የውሳኔ ሰው መሆን አለብኝ ከራሴጋ እያወራሁ ሱቅ ደረስኩ። ሀና ቀድማኝ ገብታ ነበር ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርቤላት ቁጭ ካልኩ ቡሀላ ስለልደቱ ጠየኳት።

ውይ በናትህ እንዴት ደስ እንዳለው ፍቅር ምሽቱን ሙሉ ሲፍለቀለቅ ነው ያመሸው ደሞ ብታይ ምን እንደሰራኝ በሱ ልደት ቀን ለኔ ስጦታ ገዝቶልኝ መጣ አየኸው አያምርም በናትህ አለችኝ ከፊት ለፊቴ ቆማ እየተሽከረከረች የለበሰችውን ቀሚስ እያሳየችኝ ሙሉ ሼፒ ቀሚስ ነው ሰውነቷን በአግባቡ ፍንትው አድርጎ ያሳያል እውነትም ቤዛ ልክ ናት ሰውነት ቅርጿ ያምራል ለካ ወገቧ ምግብ በልታ ምታቅ አይመስልም ከወገቧ በታች ያልተጋነነ የሰውነት ቅርፅ አላት ጡቶቿ ጉች ጉች ብለዋል በደንብ አስተዋልኳት እሷ እየተፍለቀለች ማውራቷን ቀጠለች እውነት ለመናገር ቁመቱ እንደዚህ ረጅም መሆኑን ወድጄዋለሁ ግን ሰውነቴ ላይ ጥብቅ አለ እሱ ነገር ትንሽ ደበረኝ አለችኝ፡፡ አይ በጣምኮ ነው ሚያምርብሽ ምርጫ ላይ ጎበዝ ነው አልኳት ።

ከት ብላ ሳቀችና ምርጫ ላይ ጎበዝ ባይሆን ከሄዋን ዘሮች ሁሉ እኔን ይመርጥ ነበር እንዴ አለችኝ።
ሳቋ ተጋብቶብኝ ከሷ እኩል እየሳኩ በነገራችን ላይ ኮንፊደንስሽን በጣም ነው ምወድልሽ አልኳት።
አመሰግናለሁ !! ሴት ልጅ ኮንፊደንስ የግዴታ ሊኖራት ይገባል በራስ መተማመን ካላትና እሯሳን ከወደደች ካከበረች ተከታያና ወዳጇ ብዙ ነው አለችኝ።

ለሚያምር የሰውነት ቅርፅ ከሚማርክ አስተሳሰብጋ ነው የተሰጣት ታድላ ምነው ግን ለሷ ይሄን ሁሉ ሲሰጥ ቤን የት እረስቶት ነው ወይስ ሀናን ሰርቶ በተረፈው ጭቃ ነው ቤን ለጠፍ ለጠፍ ያረጋት አልኩና መልሶ አባባሌ ለራሴ አስቆኝ ብቻዬን መሳቅ ጀመርኩ ሀና በአግራሞት እየተመለከተችኝ ምነው አባባሌ ያስቃል እንዴ???



ይቀጥላል...



🔻ክፍል8️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ሰላም ሰላም ቤተሰብ ሀና  ክፍል 7 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?

ላይክ ቀንሳችዃል ቤተሰብ ቶሎ አንዲለቀቅ አንብባችሁ ስትጨርሱ ላይክ ማድረግ አትርሱ


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
6️⃣

እንዴ ከዚህ በላይ እንዴት ትሁን ስትለኝ ልክ ነሽ የኔ ሚስት አደለች እንዴት ቆንጆ አትሆን ብለሽ ነው ለማኝኛውም እኔ ልወጣ ነው ሱቁን አደራ ብያት ወጣሁ።

ወጥቼ ወዴት ልሂድ እድሜ ለቤዛ ጓደኛ ሚባል ነገር የለኝም ሲከፋኝ ሄጄ ማማክረው አብሮኝ ሚሆን የለኝ ቤት አልሄድ የእናቴ አይን አስፈራኝ ሱቅ አልሆን ጨነቀኝ ግራ ሲገባኝ ዝም ብዬ መራመድ ጀመርኩ ከሱቅ ተነስቼ እስከየት እንደተጓዝኩ ፈጣሪ ይወቀው ብቻ እስኪታክተኝ ተራመድኩና የሆነ ቤት ገብቼ ቁጭ አልኩ ።

እሮብኛል ግን መብላት አልችልም ጠምቶኛል ቢሆንም መጠጣትም አልፈለኩም ግራ ገባኝ በህይወታችሁ ውስጥ የባዶነት ስሜት በጣም ከባድ ስሜት ነው ያማል በሰው መከበብን የመሰለ ፀጋ የለም ።
ትታ ወደማትተወኝ እናቴ መሄዱ ይሻላል ብዬ ተነስቼ ወዴቤቴ ሄድኩ ቤዛ ቀድማ ቤት ደርሳ ለእናቴ ምንሽ ላይ ልሳምሽ ምን ልሁንልሽ እያለቻት ደረስኩ ልቤን ድክም እያለኝ ገብቼ ቁጭ አልኩ።

ቤዛ ምን ልትሰሪ መጣሽ አልኳት።
ባለቤቴን ልወስድ ነው የመጣሁት በዛውም እናቴ ስለናፈቀችኝ ማየት ፈልጌ ነው አለችኝ ።
ቆይ ለብቻችን እናውራ ነይ ብዬ ይዣት ልወጣ ስል እናቴ እጄን ምንጭቅ አድርጋ አስለቀቀችኝና ምንም ምታወሩት ነገር የለም ጭራሽ አንተ ሄደህ እግሯ ላይ መውደቅ ሲገባህ በጥፊ መተሀትም ይቅርታ ልትልህ ስትመጣ በምን ጉዳይ ነው ምታወሩት አለችኝ ።

ቤዛ ቀድማ የተቀመጠውን ሻንጣዬን እየጎተተች ና የኔ ፍቅር በቃ ቤታችን እናወራለን አለችኝና ወደመኪናዋ ገባች።በዝምታ ወደቤት ደረስን።
በዝምታ ወደቤት ደረስን።ቤት ገብተን ቁጭ አልን ።

ንግግሩን እኔ ጀመርኩ ቤዛ ለመጨረሻ ጊዜ ልንገርሽ እኔ የእናቴ ነገር ሆኖብኝ እንጂ ገዝተሽ ያስቀመጥሽኝ እቃ አደለሁም ጠዋት ከቤትሽ እንደ እቃ አስወጥተሽኝ 12 ሰአት እንኳን ሳይሞላው እንደገና መልስሽ ወደቤት አመጣሽኝ ቢያንስ አላሳዝንሽም ወንድ ልጅኮ ነኝ ስሜቴ ይጎዳል ክብር ሚባል ነገር አለኝ፡፡
ወይስ ደሞ ልክ ከዚህ ቤት ውጣ ብለሽ ስታባሪሪኝ እባክሽ አታድርጊው እያልኩ እንድለምንሽ ፈልገሽ ነው አልኳት፡፡

ብድግ ብላ መጥታ መተሻሻት ጀመረች እያቀፈችእየሳመችኝ እኔኮ ምቀያየርብህ ስለማፈቅርህ ነው....


ይቀጥላል...



🔻ክፍል7️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ቤተሰብ አንዴት ናችሁ   ሀና  ክፍል 6  ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
5️⃣

ዞሬ አላየኋትም ገብቼ ሶፋ ላይ ተዘረርኩ።
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ባለቤቴ (ቤዛ) ከፊት ለፊቴ ቁጭ ብላ እያፈጠጠችብኝ ነቃሁ።

አይኔን ለመግለጥ ጭፍግግ እስኪለኝ ነበር ያስጠላችኝ ተነስቼ ቁጭ አልኩ ሻንጣ ከፊት ለፊቴ አስቀምጣ ጎበዝ ጥሩ ሰአት ላይ ነው የነቃኸው አሁን ቀጥ ብለህ ከቤቴ ውጣ ደቂቃዎች እንዲቆጠሩ አልፈልግም አለችኝ፡፡

የሰው ልጅ ድምፅ በራሱ እጅ እጅ ይላል እንዴ?
ፊቴን አዙሬ ሳላያት ወደውጭ ሻንጣዬን እየጎተትኩ ወጣሁና ወደመኪናዬ አመራሁ ኮስተር ብላ ይቅርታ ከመኪናዬ አጠገብ ዞር በል አለችኝ
ቀና ብዬ አይቻት ወደሷ መኪና እየጠቆምኩ ያውኮ መኪናሽ አልኳት።

ሀሀ ሁሉም የኔ መስሎኝ እሱንም ቢሆን በኔ ገንዘብ እንደገዛኸው አትርሳ ባዶህን እንደመጣህ ባዶህን ውልቅ በል አለችኝ።

ወንድ ልጅ አደለሁ ከዛ በላይ መታገስ አቅቶኝ
ከዛ ወጥቼ ወደናቴ ቤት ሄድኩ ገና ከውጭ ስገባ ለወትሮው በእልልታ ምትቀበለኝ እናቴ ፊቷን ነሳችኝ ደሞ እንደለመድከው ተጣላኻት አደል ድሮስ አንተ እኔን ማስደሰት መች ትፈልግና በእስተርጅና ማቅቄ እንድሞትልህ ነው እንጂ ምትፈልገው ብላ ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ነጠላ ብድግ አድርጋ ለብሳ ወጣች።

እሺ ምን ልሁን እኔ ልበድ ወይስ ምን ልሁን ብቻዬን መብሰልሰል አበዛሁ ከዛ በላይ መቆዘም ስላላስፈለገኝ ተኘስቼ ወደሱቅ ሄድኩ። ቤዛ እምር ቁንጅት ብላ ከመቼውም በላይ ዘንጣ ሱቅ ውስጥ ቁጭ ብላ ከሀናጋ እያወራች አገኘኋት።

ገና ሳያት ደሜ ፈላ ልናገራት አልናገራት ከራሴጋ ቆሜ እየተከራከርኩ እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ የምትመክረኝ ምክር ትዝ አለኝ ያለችኝ ነገር ትዝ ሲለኝ ቀስ ብዬ ሄድኩና ሀና ደና አረፈድሽ ስራ እንዴት ነው ??. አሪፍ ነው ዛሬ ቤዚ ከመምጣቷ ገበያ በገበያ ሆነናል አለችኝ።
ቤዛን እጇን ይዣት ወደውጭ ወጣሁና ምን ልቶኚ ነው እዚህ የመጣሽው ብዬ ጠየኳት
መብቴ አደል እንዴ በኔ ገንዘብ መሰለኝ ሱቁን የከፈትከው አለችኝ፡፡

_ _ ቀና ስል ሁሉም ሰው አይኑ እኛ ላይ ነው ወደራሴ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳትና ቤዛ እናቴን ይንሳኝ ድጋሜ እዚህ ሱቅ ካየሁሽና የኔ ነው የሚል ነገር ካፍሽ ከወጣ እደፋሻለሁ ለመነሻ ያበደርሽኝን ብር አፍንጫሽ ላይ እወረውርልሻለሁ ግን ድጋሜ መተሽ የኔ ነው ሚል ጥያቄ ካነሳሸ ብቻ አላቅም አሁን ከዚህ ጥፊ አልኳትና ፈገግ ብዬ አይቻት ወደሱቅ ገብቼ ቁጭ አልኩ።

ሀኒ አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለችና አንተ ሚስትህ ግን በጣም ቆንጆ ናት አለባበሷ እራሱ ኩል የሆነ አለባበስ ነው እኔ ሴት ልጅ እራሷን ስጠብቅ ደስ ይለኛል አለችኝ ሳቄ አለመለጠኝ አይ ሀኒ እራሷን ትጠብቃለች ብለሽ ነው አልኳት?



ይቀጥላል...



🔻ክፍል6️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ተመልሰናል ቤተሰብ አንዴት ናችሁ ሀና  ክፍል 5 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


Репост из: Wave
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

በአጭር ጊዜ ህይወታቹን የሚቀይሩ የተረጋገጡ ጨዋታዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ 👇

betting ሁሌ ማሸነፍ ከፈለጋቹ ይሄንን ቻናል ተቀላቀሉ🏆👇


🎬ምን አይነት ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?😱😱😱😱😱😱😱😱😱👇👇👇

'https://t.me/addlist/8fKNPukq-f0zYzFk' rel='nofollow'>▶️የቱርክ ፊልም    JOIN 👈 ይንኩ

▶️የአሜሪካ ፊልም   JOIN 👈 ይንኩ

▶️ የህንድ ፊልም     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የቻይና ፊልም      JOIN 👈 ይንኩ

▶️የአማርኛ ፊልም      JOIN 👈 ይንኩ

▶️ተከታታይ ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️ አኒሜሽን ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️አክሽን ፊልሞች     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የጫካ ፊልሞች     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የፍቅር ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️የsex ፊልሞች    JOIN  👈  ይንኩ

✅ እንደ ምርጫው መርጦ ይቀላቀሉ ✅

                    JOIN

ይቀላቀሉ                        ይቀላቀሉ


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
4️⃣


በቃ ከዛ ቤት ለመውጣት ቅር እያለኝ ነበር ግን
ስለራበኝም ቤቷን ቆላልፌ ወደ ሱቅ ተመለስኩ። ገና ከመኪናዬ ስወርድ ሀኒ ከአንድ ከስተመርጋ እየተሳሳቀች ልክ እረጅም አመት እንደሚተዋወቅ ሰወሰ እሷ ስታማርጠውና እሱም የሷን ቃል ተቀብሎ ገዛዝቶ ሲሄድ አየሁና ፈገግ ብዬ እኔ ግን እዚህ ሱቅኮ ለምን እንደምመጣ አላቆም አልኳት።

መምጣትህማ ግድ ነው አለቃ የሌለው ስራ ደስ አይልም እና እንዴት ነበር ተኛህ አልጋዬ ተመቸችህ አለችኝ።

ውይ አዎ ስገባ እንዴት ብዬ አልጋው ላይ እንደተዘረርኩ እራሱ አላቅም ስነቃ ነው ቤትሽን ያየኋት በጣምም ነው ምታምረው ዛሬ ደሞ ፏ አድርገሻት ነው የወጣሽው እንግዳ አለብሽ መሰለኝ አልኳት።
ከት ብላ ሳቀችና አንተ ሴትኮ ነኝ የወንደላጤ ቤት መሰለህ እንዴ ሁሌም ቢሆን ቤቴንና እራሴን ከማፅዳች ውጭ ምን ስራ አለኝ እኔ ጠዋት ከቤቴ ስወጣ ቤቴን ፅድትድት አድርጌ ወጥቼ ልክ ስራ ውዬ ደክሞኝ ስገባ ፍክት ብላ ማየት ነው ምፈልገው ደሞ ሰው ነህ ስንት ነገር አለ ከቤት ከወጣሁ ቡሀላ ከማንጋ ተመልሼ እንደምገባ አላቀውም ለራሴም ለሰውም አይን ቆንጆ ነገር ማሳየት ደስ ይላል ፍቅርም የሚወድልኝ ይሄን ነገሬን ነው አለችኝ፡፡ በውስጤ ፍቅረኛዋ ምን ያህል እድለኛ ሰው እንደሆነ እያሰብኩ ነበር።

የኔንም ሚስት ከሀና እኩል ሴት ተብላ መጠራቷን ሳስብ ብቻዬን አሳቀኝ። ሀና ቀጠል አድርጋ ስማማ ደሞኮ ያሁኑ ሀሙስ ልደቱ ውይ በናትህ ያለኝን ብር እንዳለ እያጠራቀምኩ ነው ግን ሊሞላልኝ አልቻለም ካልደበረህ ደሞዝ ቀድሜ ልውሰድ ደሞዝሽን ለሱ አጥፍተሽ ቤት ኪራይ ሲደርስ ምን ልትከፍይ ነው አልኳት።

ችግር የለም እሱ ደስ ብሎት ካየሁ ሌላ ምን ፈልጋለሁ ብቻ የዛን ቀን ደስ ብሎት ማየት እፈልጋለሁ አለችኝ እሺ ብዬ ቀድሜ ሰጠኋት፡፡
ያ የተጠበቀው ሀሙስ ደረሰ በጠዋት እብድ እብድ እያለች መጣችና ዛሬ እነሆ የልቤ ሌባ ልደቱ ነው እና አስደሳችና የተለየ ቀን ስለሆነ ከሰአት ወደቤት እሄዳለሁ አለችኝ እአልኳት።

☞ ትንሽ ቆየችና ከጣራ በላይ ሳቀች በቃ ሳቋ እስኪጋባብኝ ድረስ ማቋረጫ የሌለው ሳቅ ሳቀች እኔ ለምን እንደሳቀች ሳይገባኝ እንደጅል አብሪያት መሳቅ ጀመርኩ ውይ በናትሽ ንገሪኝ እንደሞኝ ዝም ብለሽ አትሳቂ ምንድነው ያሳቀሽ አልኳት።

በአይኖቿ የሞሉትን እንባ እየጠረገች እኔኮ ልጅ እያለሁ ፍቅረኛዬ ይሆናል ብዬ ማስበውን ሰውና አሁን አብሬው የሆንኩትን ሰው ሳስበው በቃ ሳቄ ይመጣብኛል ልጅነትን የመሰለ ነገር ግን የትም አይገኝም አለች።

ምሳ ሰአት ላይ ወደቤት ልትሄድ ስትል ምሳ ሰአት አደል አብረን እንሂድና ላግዝሽ ከዛ እኔ እመለስና እከፍታለሁ ብያት በኔ መኪና ወደቤቷ ሄድን እንደተለመደው ቤቷ ጨረቃ መስላለች አልጋ ላይ ፊኛዎች ተነፍተው አልጋውን ሞልተውታል ስራ ላቅል ብዬኮ ነው ፊኛዎቹን የነፋኋቸው አሁን በመሰቃቀል አግዘኝ እረዘም ስለምትል ለኔ አሪፍ ነው አለችኝ ግድግዳውን እየተቀባበልን በፊኛ ሞላነው ኮርኒሱንም በፊኛ አጥለቀለቅነው ብቻ ዲኮሩ የተለየ ነበር እየሰራን ብዙ ነገር እያወራን ነበር ስንጨርስ አይ የሁለት ጥበበኞች እጅ ምን እንደፈጠረ አየህ አደል አያምርም በናትህ ውይ እንዴት ደስ እንደሚለው እያሰብኩ እንባ እየተናነቀኝ ነው አሁን በቃ አብረን እንውጣና እኔም ያዘዝኩት ኬክና ወይን ይዤ ልምጣ አለችኝና ተያይዘን ወጣን እሷም ወደመንገዷ እኔም ወደሱቄ ሄድኩ ገና ገብቼ ቁጭ ከማለቴ ደወለችና አረ ታሜ አልበላም አልጠጣም ብዬ የገዛሁለትን ስጦታ ሳላሳይህ ትሄዳለህ እንዴ ቁም ሳጥኔ ውስጥ ነበርኮ እረስቼው ነው አለችኝ በቃ በ vedio አየዋለሁ መልካም ምሽት ብያት ስልኩ ተቋረጠ፡፡

ቁጭ ብዬ ምናለ ለኔም ወጥቼ እስክገባ ምትናፍቀኝን የምወዳትን ምትወደኝን አግብቼ ቢሆን ምናለ ልደቷ ደረሰ ብዬ ምጨነቅላት እሷም ምትጨነቅልኝ ሚስት ኖራኝ በሆነ ብዬ ተመኘሁ፡፡እኔም የሚስቴን የልደት ቀን አላቀውም እሷም አታቀውም


ነገሮችን ሳስባቸው ድብርት ውስጥ ገባሁ ህይወቴን መለስ ብዬ ሳየው ለራሴ እጅ እጅ አለኝ። ሱቄን ዘግቼ ወደ መጠጥ ቤት ሄድኩኝ እስከጥግ ድረስ ጠጣሁ ያው ሰካራምና እብድ ውሉን አይስትም እንደሚባለው እየነዳሁ ወደቤቴ ሄድኩ።
በር ላይ ቆሜ ክላክስ ባደርግ ባደርግ ሚከፍትልኝ አጣሁ እኔም እልህ ይዞኝ ሰፈሩ እስኪበጠበጥ ድረስ አጮኩት እንደምንም መጥታ ከፈተችልኝና ገባሁ።

ከመኪናው ስወረድ ዘላ አንቃ ያዘችኝና አንተ ሰራተኛነት የቀጠርከኝ መሰለህ እንዴ ላንተ ስትወጣ ስትገባ በር ምከፍተው ደሞ ምን ሚሉት ንቀት ካልከፈትኩና ዝም ካልኩህ እራስህ ወርደህ አትከፍትም እንዴ ጀብድ መሆኑ ነው ሰፈር ምትበጠብጠው አለችኝ።

በቃ በሰአቱ ለአይኔ አስጠላችኝ የመጠጡ ሀይል ገፋፋኝና እጇን ከአንገቴ ላይ አስለቁቄ ወረወርኩት አልፊያት ልገባ ሰል ወዴት ነው እኔ ውጭ ቆሜ ምትገባው አስፈላጊ ከሆነኮ ቤቴ ድርሽ እንዳትል ማድረግ እችላለሁ just ጥገኝነት ጠይቀህ እንደምትኖር ቁጠረው አለችኝ።

በቃከዛ በላይ አልቻልኩም በጥፊ ደረገምኳትና መጀመሪያ ቤት ተዘፍዝፈሽ እየዋልሽ ፀጉርሽን ማበጠርና ገላሽን መታጠብ ሳትችይ እኔ ላይ አትለፋደጂ እኔስለሆንኩ ነው
አብሬሽ ምኖረው አልኳትና ወደ ውስጥ ገባሁ።

ይቀጥላል...



🔻ክፍል5️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ሰላም ሰላም ቤተሰብ ሀና  ክፍል 4 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


ዝም ብለህ ስማኝማ… ልክ ጥዋትህ ነግቶልህ ከእንቅልፍህ ስትነቃ

ባልካፈትከው በሌለህ የባንክ አካውንት ውስጥ 86,400 ብር ቁጭ ብሎ ቢያድርልህና ውሰደው ይሄ ቀን መሽቶ እስክትተኛ ድረስ በትክክል ተጠቅመህ ጨርሰው ብትባልስ?

አስበሃዋል በምን ፍጥነት ልታጠፋው እንደምትችል… ለሌላ ሰው ማበደርም ሆነ መለገስ አትችልም ለራስሀ ብቻ አጥፍተህ ጨርሰው ቀኑ እስኪመሽ አጥፍተህ ባትጨርሰው ይቃጠላል expired ያደርጋል… በቃ ሁሌ ጥዋት ስትነቃ የትላንቱ አልቆ ወይም ተቃጥሎ አዲስ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ብር አለህ በዛሬዋ ቀን አጥፍተህ ጨርሰው ብትባልስ?

ይሄን ሁሉ ብር በየቀኑ እንዴት አድርገህ ልታጠፋው እንደምትችል አስበው… ።
ምን ብትገዛ በምን ብትዝናና በየቀኑ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ብር ልታጠፋ ትችላለህ።

ለነገዬ ብለህ መቆጠብ አትችል ደሞ ነገ ሌላ ተመሳሳይ ብር ይሰጥሃል እንዴት ታጠፋዋለህ? አስብከው? ምን ልታደርገው እንደምትችል መጣለህ? ወይስ መጀመሪያ ላግኘውና አስብበታለው አልክ…

እኔ ግን በምን አይነት ፍጥነት ተንገብግቤ እንደማጠፋው እያሰብኩ ነው… ለማንኛውም ምን ልልህ መሰለህ በየቀኑ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ሰከንዶች በነፃ ያለጥያቄ ይሰጥሃል በልዋጩ የምትከፍለው ነገር የለም መታውቂያ እንኳን አትጠየቅም።

ማመልከቻ ሳታስገባ ሳትከፍል በቅጡ ሳትለምነው የትላንቱን ቀንህን በዝባዝንኬ ነገር እንዳሰለፍከው እያወቀም ለዛሬው ቀንህ ሰማንያ ስድስት ሺ አራት መቶ ሰከንድ አምላክ በነፃ ሰጥቶሃል እንዴት ልትጨርሰው አስበሃል? ምን ልታደርግበት እየወሰንክ ነው?

በየትኛው ሰክንድ ላይ የዛሬ ኮታህ እንደሚጠናቀቅ የምታውቀው ነገር የለም… ከምትወዳት እናትህ እራሱ አንዲት ሰከንድ መበደር ማበደር አትችልም ሰከንዱ ሲጠናቀቅ አለቀ ትሞታለህ።

ገንዘብ አላቂ ነው ብለህ እንደምታጠፋው ጊዜ አላቂ ነው ተጠቀምበት።
የዛሬው ቀንህ ልክ መጠቀምህ ማጥፋትህ ግዴታ እንደሆነ ገንዘብ አድርገህ ተጠቀምበት ነገ መኖሩን አታውቅምና።

ጠቃሚ መስሎ ከታያችሁ አሁኑኑ ሼር አድርጉ

via የፍቅር ክሊኒክ


https://t.me/yefikirtelegramet
  


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ ሀና ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣


በቃ ችግር የለውም እኔ ማቃት ልጅ አለች በጣም ትግስተኛና ጎበዝ ልጅ ናት ከሷጋ ይስማሙ ይሆናል ላምጣት እንዴ አለችኝ፡፡
እሺ እስቲ እንሞክራለና ከምግብ ቤት ቁርስ ደርሶ ስለመጣ እኔ ቁርሴን መመገብ ጀምርኩ ።
አትበይም?? አረ እኔ ቁርሴን ሰራርቼ ግጥም አድርጌ ነው የበላሁት ቆይ ስንት ሰአት ነው ከእንቅልፍሽ ምትነሽው???
☞ 12 ሰአት ሲል እነሳለሁ ቤቴን አፀዳዳለሁ ቁርሴን ሰርቼ በላልቼ ሻወር እወስድና ወደስራ እመጣለሁ ቤቴ ቅርብ ስለሆነኮ ነው ቶሎ ምደርሰው አለችኝ። አቀው የለ የቤትሽን ቅርበት መች አጣሁት አልኳትና ቁርሴን በላላሁ እሷም ደውላ ሰራተኛዋን አወራቻትና ዛሬውኑ መምጣት እንደምትችል ነገረቻት እኔ እራስ ምታቱ በጣም ስለበረታብኝ በዛውም ሰራተኛዋን ይዤ ወደቤት ለመሄድ ስላሰብኩ 8 ሰአት ሲል ወደቤት ሄድኩ።

ቤት ስደርስ ሚስቴ የለበስቸውን ቢጃማ ሳትቀይር ብርድልብሱን እንደተጠቀለለች ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ትበላለች ስታየኝ ደሞ ዛሬ ማንን እየጎተትክ ነው የመጣኸው አለች። አዲሷ አጋዣችን ናት አንቺ ከምትደክሚ እሷ ትሰራራልሻለች አልኳትና ወደውስጥ ገብተን ቁጭ አልን።

ስማቸውን ከተዋወቁ ቡሀላ በቃ ተነሽና ቤቱን አስተካክይ ኪችን ውስጥ የታጎረ የሶስት ቀን እቃም አለ ግቢና እጠቢ አለቻት እኔ ከዛ በላይ ንግግራቸውን መስማት ስላልፈለኩ ወደመኝቻ ቤት ገብቼ ተኛሁ።

ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ስላልተኛሁ ከመቼው እንቅልፍ እንደጣለኝ አላቅም ብቻ ሁለት ሰአት አካባቢ እራት እንድበላ ልጅቷ ቀሰቀሰችኝ ተመስገን ቢያንስ ቤቱን ቤት አስመስላዋለች እያልኩ ወደሶፋው ሄጄ ቁጭ አልኩ እራት ቀረበ ከስንት ቀን ቡሀላ ክብር ያለው እራት በክብር ቁጭ ብዬ ተመገብኩ።

በላልተን ስንጨርስ ወደመኝታ ቤቴ ተመልሼ ገብቼ ጋደም ስል ሚስቴ መጣችና መተሻሸት ጀመረች አይ አምላኬ ሆይ ቆይ ምን ይሆን እንደዚህ በየደቂቃው ሚቀያይራት እያልኩ እኔም እቅፍ አደረኳት መሳሳም ጀመርን ጠረኗ ደስ አይልም ፀጉሯን ለመነካካት ስሞክር ውስጡ ተያይዞ ድሬድ ለመሆን የጀመረ ይመስላል።

ቤት አደል ምትውለው ምናለበት ገላዋን ብትታጠብ ምናለበት ቁጭ ብላ ፊልም እያየች ፀጉሯን ብታበጥር ውስጤ እየተብከነከነም ቢሆን ፍቅር ሰራንና ተቃቅፈን ተኛን ።

ጠዋት ስነሳ ቁርስ ተዘገጃጅቶ ጠበቀኝ ሚስቴ ሞቅ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ስለነበረች ብቻዬን በልቼ ወደስራ ወጣሁ፡፡

ከአስራ አምስት ቀን ቡሀላ ሀና ስልክ ተደወለላትና እየተቻኮለች ወጣች በዛው ሳትመለስ ቀረች እኔም እሷ ሳትኖር ከከስተመርጋ መከራከር ስለከበደኝ በጊዜ ዘግቼ ወደቤቴ አመራሁ ሰራተኛዋ የለችም የት ሄደች ብዬ ጠየኳት ጠዋት ተኝቼ በራሴ ጊዜ መነሳት ስፈልግ መነሳት እየቻልኩ ቁርስ ደርሷል ብላ ትቀሰቅሰኛለች እንዴ ከዛ አባረርኳት አለችኝ።

ፊት ለፊቷ ከት ብዬ ሳኩና በቃ ለዚህ ብለሽ አባረርሻት?? ምን ማለት ነው ቤተሰቦቼ ሀብቴን ያወሩሱኝ በፈለኩት ሰአት ተኝቼ በፈለኩት ሰአት እንድነሳ ፈታ ብዬ እንድኖርኮ ነው ከፈለክ አንተም ውልቅ ማለት ትችላለህ ብላኝ እየተመናቀረች ወደመኝታ ቤት ገባች።

ከልቤ ተሰማኝ በቃ ውስጤ ባዶ የሆነ ያህል ተሰማኝ ምድር ላይ ጥቅም የሌለው ሰው ልክ ገበያ ሄዳ ገዝታ እንዳመጣችው እቃ እንደዚህ ስትሆንብኝ አቃተኝ ከራሴጋ ስታገል አንዴ ላለማልቀስ ስሞክር ሲያቅተኝ ተነስቼ ከፊርጅ ውስጥ ያሉትን መጠጦች እያወጣሁ መጠጣት ጀመርኩ እስኪወጣልኝ ጠጣሁ ትንሽ እንቅልፍ ሊወስደኝ ሲል ሰአቱን ሳየው ነግቷል ተነስቼ መኪናዬ ውስጥ ገባሁና ወደሱቅ ሄድኩ ሀኒ እስክትመጣ ሱቁን ዘግቼ መተኛት ፈልጌ ነበር ግን በሩ መስታወት ስለሆነ ሰው ምን ይለኛል ብዬ ፈራሁና ቻል አድርጌው ቁጭ አልኩተ ሀና ገና እንዳየችኝ አንተ ምን ሆነሀል ቀድመኸኝ ስትገባ ስትገባ ፊትህ ልክ አደለም እየነጋብህ ነው እንዴ በዚሁ ምትመጣው አለችኝ፡ አረ አደለም ሀኒ ሌሊቱን ሙሉ ስጠጣ ነው ያደርኩት እራሴን ልሞት ነው እንቅልፌ የአይኔ ሽፋሽፍት ላይ ነው ያለው መሞቴ ነው አልኳት።
እና እንቅልፍ ከመጣ ቤት አትሄድምና አትተኛም እንዴ ለሱቁ ከሆነ እኔ አለሁ አደል አለችኝ።
ቀና ብዬ አየኋትና ቤት አሌድም ከሚስቴጋ ተጣልቻለሁ ።

እና ወይ እኔ ቤት ሂድና ተኝተህ ና አለችኝ እሺ ግን ባልሽ ድንገት ቢመጣስ ??? አንተ ደሞ ፍቅረኛዬ እንጂ ባሌ አደለምኮ እሱ ደሞ ሳይደውልልኝ አይመጣም ቢመጣም ችግር የለውም ብቻህን ተኝተህ እያየ ምን ያስባል ብለህ ነው ሂድ በቃ ግን ምግብ የለም ባይሆን ምሳ ሰአት ላይ ና እንቅልፍህን ስትጨርስ ብላ የቤቷን ቁልፍ አውጥታ ሰጠችኝ:: ቁልፉን ተቀብዬ እንደምንም መኪናዬን እየነዳሁ ቤቷ ሄድኩ ግቢ ውስጥ ሁለት ሚከራዩ ቤቶች አለ ። ምልክት ወደሰጠችኝ ቤትጋ ሄድኩና ከፍቼ ገባሁ።

ቤቷ በጣምም ታምራለች በቃ ታምራለች አይገልፀውም አንድ ክፍል ብትሆንም የተዋበች ናት ቀጥታ እንደገባሁ አልጋውን ስላየሁት በሩን ቆለፍኩና ገብቼ ተዘረርኩ ወዲያው እንቅልፍ ወሰደኝ ስልኬን አጠፋፍቼ ስለተኛሁ ምንም የረበሸኝ ነገር አልነበረም ፡፡

ከእንቅልፌ ብንን ስል 6 ሰአት ሆኗል በስማም ሁለት ሰአት የመጣሁ እስከስድስት ሰአት ምንም ሳልነቃ ብዬ ነቃ ለማለት ሞከርኩ የትራሱ ሽታ ከላዩ ላይ ለመነሳት አያስመኝም ተነስቼ በተረጋጋ መንፈስ ቤቷን ቃኘት ቃኘት ማድረግ ጀመርኩ።

ነጭ ቁም ሳጥን አለች ከጎኗ ነጭ ቲቪ ስታንድ ትልቅ ቴሌቪዥን ተሸክሞ አለ።
መሬቷ ሴራሚክ መሳይ ምንጣፍ ተነጥፎባታል በቀኝ በኩል የእቃ ማስቀመጫ ቡፌና የኤሌትሪክ ምጣድ አለ፡፡

ቤቱን ዞር ዞር እያልኩ ሳይ ሁሉም ነገር ንፁህ ነው የእያንዳንዱ የእቃው አቀማመጥ ደርዝ አለው stovu ከተገዛ ወጥ ተሰርቶበት ሚያቅ አይመስልም ፅድት እንዳለ ነው በስተት አንድ የቆሸሸ እቃ የለም አልጋዋ ላይ ያነጠፈችው አልጋ ልብስ በራሱ እንዲተኙበት ሚጋብዝ ነው



ይቀጥላል...



🔻ክፍል4️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ሰላም ሰላም ቤተሰብ ሀና  ክፍል 3 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


ሰውዬው ያለችውን አንድ ግመል ተጠቅሞ ወተቷን ለሰፈሩ በመሸጥ የታወቀ ነው።

ይህ እያለበ የሚሸጠው ወተት ለመንደሩ አልበቃ ቢለው፤ “ንፁህ ወተት ነው” በማለት ውሃ ጨምሮ በማብዛት መሸጥ ጀመረ።

በዚሁ ተግባሩ ብዙ አትርፎ ሌላ ግመል ገዛ። ከሁለት ግመሎቹ የሚያገኘውን  ወተት እንዲሁ ውሃ በመጨመር እየሸጠ ሀብቱ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ሄደ።

በዚሁ ስራው ብዙ ግመሎችና ፍየሎች በብዛት ይገዛል።

አንድ ቀን ያሉትን ግመሎቹን እና ፍየሎቹን በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ ላይ በለምለም ቦታ አሰማርቷቸዋል።

በድንገት አዋሽ ጨክኖ ደራሽ ሆኖ፤ ሞልቶ እየፈሰሰ ከወደላይ በፍጥነት ወደ ሰውየው መጉረፍ ጀመረ።

ሰውዬውም ግመሎቹን እና ፍየሎቹን ማዳን ሳይችል፤ ደራሽ ወንዙ ይዟቸው ሄደ። እሱም እንደምንም የግራር ግንድ አቅፎ ከመወሰድ ይድናል።

የግመሎቹና የፍየሎቹ መወሰድ ቢያሳዝነው እሪታውን አቀለጠው። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰበሰበ።

አንድ ሽማግሌ ከታዳሚው ነጠል ብለው ወደ ሰውየው ቀርበው፦

“አየህ!?” አሉት። “አየህ!? ለመንደሩ ሰው ለአመታት ከወተት ጋር ስትቀላቅለው የነበረው ውሃ ዛሬ ደራሽ ሆኖ፤ ተሰባስቦ መጥቶ ግመሎችህን እና ፍየሎችህን ይዞብህ ሄደ። የእጅህን ነው ያገኘኸው።” ብለውት ዞር አሉ።
—————————————-
✔መልካምነት በዝቶ ተባዝቶ ባልጠበቅነው መንገድ መልሶ ይከፍለናል።

✔ክፋትም በዝቶ ተባዝቶ መልሶ ይቀጣናል።

✔ለመፅደቅም ይሁን ለመኮነን ብለን ባናስብ እንኳን  መልካምነት በየትኛውም መስፈርት ከክፋት እንደሚሻል ህሊናችን አሳምሮ ያውቀዋል።

መልካም መልካሙን እናስብ፤ እንተግብር!!❤️💯

ከማህበራዊ ሚዲያ አግኝተነው ስለወደድነው እና አስተማሪ ነው ብለን ስላሰብን አጋራናችሁ

ታሪኩን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ደርሷቸው ይማሩበት ዘንድ
#Like #Copylink #Share እያደረጋችሁ 🙏


✍limitless

Показано 20 последних публикаций.