ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


💠
እንኳን ደና መጡ!
በቻናላችን ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
መዝሙሮችን 🔔 ያገኛሉ።
💠
@Eotc_books
@Orthodox_film
@Orthodox_poem
@Orthodox_bealat
@Orthodox_question
@Orthodox_mezemur
@Orthodox_Tewahdo_picture
💠
@EOTC_LIBRARY
@EOTC_LIBRARY_BOT
💠
ለአስተያየት ➱ @Orthodox2_bot
💠

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ዘ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
🔔  የንስሐ መዝሙሮች  🔔
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰


የሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
የሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

የዲ/ን ቀዳሜ ፀጋ ዮሐንስ
የዲ/ን ታደለ ገድፍ
የዲ/ን አቤል ተስፋዬ

የመምህር ሲሳይ ደምሴ

የመጋቤ ስብሐት አለሙ አጋ ቁ.1
የመጋቤ ስብሐት አለሙ አጋ ቁ.2

የዘማሪት ሶስና ገ/ኢየሱስ
የዘማሪት የትምወርቅ ሙላት የበገና

የአቶ ደምሴ ደስታ(ደምሴ በገና)
የአቶ ዘርፉ ደምሴ (የደምሴ ደስታ ልጅ)


➲ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ስብስብ 🔔
https://t.me/+o4Lx0cg9quI0ZTZk

.




Репост из: ኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪዎች ☎️
💒 የአለማየሁ ዋሴ መፅሐፍት 📚
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

➱ 1, እመጓ
➱ 2, ዝጓራ
➱ 3, መርበብት
➱ 4, ሰበዝ
➱ 5, ሜተራሊዮን


➲ ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍ ማውጫ 📖
https://t.me/+bmWacGGbXvJjOTQ8
.




Репост из: ኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪዎች ☎️
💒  ድርሳነ ሚካኤል  📚
▰▰▰▰▰▰▰▰▰

➱ ድርሳነ ሚካኤል ክፍል 1
➱ ድርሳነ ሚካኤል ክፍል 2
➱ ድርሳነ ሚካኤል ክፍል 3




#አጅቡት_በዕልልታ

አጅቡት በእልልታ ሲመጣ ሙሽራው 
ፍጹም የሚያስደስት የሠርጉ እለት ነው 
ዘመዶቹ ሁሉ ተቀበሉት ውጡ 
የሙሽራው መምጫ አሁን ነው ሰዓቱ 
እልል እንበል/2/ እንዘምር በእልልታ 
ይህን ላደረገ ለሠራዊት ጌታ 
ሁሉንም በጊዜው ይፈጽማልና 
ይኸው አበቃቸው ለዚህ መልካም ዜና 

ሙሽሪት ተደሰች ዝምታው ምንድነው 
የዳግም ልደትሽ የሠርግሽ እለት ነው 
አዳም ጐንሽ ቆሞ ሔዋን ሆይ ሲልሽ 
መንፈሳዊ ሐሴት ይሙላ በልብሽ 
አዝ --- 
እህት ወንድሞቿ እናትና አባቷ 
ተነሡ ዘምሩ ለልጃችሁ ደስታ 
መሄዷ ነውና ወደ ቤቷ ዛሬ 
ወደ አዲስ ጐጆዋ ሽኙአት በዝማሬ 
አዝ --- 
ቤተሰቦችሽን ሁሉንም ትተሽ 
መሄድሽ ነውና ወደ መኖሪያሽ 
ከአማኑኤል ጋራ ባልሽን ይዘሽ 
ተነሽ ሙሽራዬ ደርሰዋል ሰዓትሽ 
ከድንግልም ጋራ ሚስትህን ይዘህ 
ተነሥ ወንድሜ ሆይ ደርስዋል ሰዓትህ 

#በወርሀ_ሚያዝያ_ሰርጋችሁን የምትፈፅሙ መልካም ጋብቻ እንዲሆንላቹ እንመኝላቹሀለን።

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥




✞ኧኸ ቃና ዘገሊላ✞

ኧኸ ቃና ዘገሊላ(፪)
በእመብርሃን ምልጃ በረከት ተመላ
በክርስቶስ ተአምር በረከት ተመላ
ኧኸ ቃና ዘገሊላ

የዶኪማስ እልፍኝ ያልተስተካከለው
ሁሉን ለመሸኘት ብዙ የጎደለው
ጥቂት ብቻ ነበር የጓዳው ዝግጅት
ሞልቶ ተራረፈ ጌታ ሲገኝበት
        አዝ= = = = =
አልባሌውም ወይን ፈጽሞ እንዳለቀ
ኋላም በምትኩ አዲስ ተጠመቀ
ለስካር አይደለም ለእምነት ሆነላቸው
የእመብርሃን ምልጃ  እጅግ ደነቃቸው
       አዝ= = = = =
የቃናው ሰርግ ቤት ትንሽ የምትመስለው
ዝናዋ ገነነ ዓለም ሁሉ ሰማው
ዛሬም ይህች ድንኳን ትንሽ አይደለችም
ስለታደመባት ጌታ መድኃኒዓለም
       አዝ= = = = =
ጋኖቻችሁ ሁሉ የጎደለባቸው
ወይን ስላለቀ እጅግ ያፈራችሁ
የጌቶቹን ጌታ ጥሩት ከእናቱ ጋር
ባርኮ ከሰጣችሁ ይዳረሳል ለአገር
       አዝ= = = = =
አልባሌውን ወይን ፈጽሞ እንዳለቀ
ኋላም በምትኩ አዲስ ተጠመቀ
ለስካር አይደለም ለእምነት ሆነላቸው
የክርስቶስ ተአምር ስለበዛላቸው

                መዝሙር
            በማህበረ ሰላም

"በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች..."
               ዮሐ ፪፥፩-፳፭

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥




​​ቃና ዘገሊላ

ቃና ዘገሊላ (፪)
በዚያ በሠርግ ቤት ተገኝተሻል ድንግል
ከልጅሽ ጋራ ተገኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ

እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም
አንች ደረስሽለት ሆንሽው አማላጅ
       አዝ = = = = = =
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ
      አዝ = = = = = =
የጌታን አምላክነት የተገለፀበት
ምንኛ ታደለ የነዶኪማስ ቤት
ዛሬም ይሄው በሰርገኞቹቤት
በረከት ፈሰሰ በአምላክ ቸርነት
     አዝ = = = = = =
ውሃው ተለውጦ ወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ዘገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን
ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን

"በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበር
      የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች …"
                   ዮሐ ፪፥፩-፲፪

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥




💍 በሠርጋችን ዕለት 💍

በሠርጋችን ዕለት እንድትባረከን
ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን
ከእናትህ ጋር ከእመቤታችን
ከመላእክት ጋር ና በሠርጋችን
ከሐዋርያት ጋር ና በሠርጋችን
ከወዳጆችህ ጋር ና በሠርጋችን

በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳን ጌታ ስንጠራህ
የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር
አንተ ነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር
        አዝ= = = = =
ነይ ከልጅሽ ጋራ እመቤታችን
እንድታሟይልን የጎደለውን
ንገሪው ለልጅሽ ባዶው እንዲሞላ
በረከት የእርሱ ነው ቤታችንን ይሙላ
        አዝ= = = = =
በጎደለው ሁሉ እየጨመርሽልን
ቤታችንን ሁሉ ሙይው እናታችን
ለአገልጋዮቹ ድንግል ንገሪያቸው
ጠርተን እንዳናፍር ጋኖቹን ይሙሏቸው

           መዝሙር
       በማኅበረ ሰላም

የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፪

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥




✞💍 ሙሽራዬ አበባዬ 💍✞

ሙሽራዬ(፫)አበባዬ

ከጎንህ የምትሆን እህት አገኘህ
የኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለህ
የእግዚአብሔር ፈቃዱ ለዚህ ካበቃችሁ
ቤታችሁ ይመረቅ በፍቅር ያጽናችሁ
         አዝ= = = = =
ወንድም አግኝተሻል የሚያስብልሽ
የእኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለሽ
እግዚአብሔር ይመስገን እኛም ደስ ብሎናል
በቤተክርስቲያን ሠርጋችሁ ውብ ሆኗል
         አዝ= = = = =
እንደ ነፍስህ አርገህ እንድትወዳት
አደራ ሰጠንህ በጌታችን ፊት
እንድታስቢለት አንቺም ለአካልሽ
አደራ ትላለች ወንጌል እናትሽ
        አዝ= = = = =
በሥጋ ወደሙ ሕይወት አግኝታችሁ
ፍሬአችሁም ይብዛ ይባረክ ጓዳችሁ
አምላክ ያለበት ነው ይኄ ጋብቻችሁ
እስከ መጨረሻ ኑሩ ደስ ብሏችሁ

💍 💍

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥




✞ ይህን ላደረገ ✞

ይህን ላደረገ ሃሌሉያ በሉ 
እግዚአብሔር ታማኝ ነው ሁልጊዜ በቃሉ 
ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ ያላችሁ 
የያዕቆብ አምላክ ሞገስ ሆነላችሁ 

ስንቱን ተራራ አልፈነዋል
በሠገነት ላይ አቁሞናል 
እስቲ እንዘምር በደስታ
ሁሌ ታማኝ ነው የኛ ጌታ 
ከእኛ የሆነ ምንም የለም
ተመስገን ጌታ ለዘላለም 
ስራህ አበራ በምስጋና
በሙሽሮች ላይ እንደገና 
         አዝ= = = = =
የማይሆን መስሉ የታየን
በእግዚአብሔር ሆኖ ስላየን 
እንደ አሳፍ ልጆች ተስልፈን
ስሙን ለቅኔ ለማመስገን 
የተባረክ በመዳፉ
ቅኔን ያፈሳል ሁሌ በአፉ 
ከመላእክት ጋር አንድ ሆነናል
የእግዚአብሔር ሥራ መስጦናል 
         አዝ= = = = =
ጋኑ ቢጎድል የወይን ጠጁ
ያስባል ጌታ ለወዳጁ 
መናኛ ይውጣ ከቤታችን
አዲስ እንጠጣ እርሱን ይዘን 
አቤንኤዘር ነው መዝሙራችን
እየረዳን ነው አምላካችን 
ፊታችን በራ በደስታ
ውበት ሆኖናል የእኛ ጌታ 

                  መዝሙር
           ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥




✞ ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ ✞

ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ/2/
በእግዚአብሔር በሕያው ቃሉ
ሁለቱም አንድሆኑ ዛሬ

ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠራቸው
በኋላም በቃሉ አንድ አደረጋቸው
እናትና አባቱን የአዳም ልጅ ይተዋል
ከሚስቱም ጋር በሰላም በአንድ ይተባበራል
        አዝ= = = = =
ሁልቱም አንድ ሥጋ ሆነው ይኖራሉ
ብሎ አስተምሮናል ጌታችን በቃሉ
አንድ ሥጋ ናቸው አይደሉም ሁለት
የባልና የሚስት ሕይወት ወደ ፊት 
       አዝ= = = = =
እንግዲህ እግዚአብሔር ካጣመራችሁ
በሆነው ባልሆነው ሰው አይለያችሁ
ለወገኖቻችሁ ምሳሌ ሆናችሁ
በክርስትና ፍቅር በዓለም ያቁማችሁ
       አዝ= = = = =
ምንጣፋችሁ ቡሩክ መኝታችሁ ንጹሕ
ስለሆነላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
ዓለም እንዲደነቅ ጠላት እንዲያፍር
በኃዘን በደስታ ይኑራችሁ ፍቅር


✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥

💿የተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ💿
        💿 / audio ለማግኘት 💿

💠 @Orthodox_mezemur

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot

✥ ┈•◦●◈◎ ❖ ◎◈●◦•┈ ✥



Показано 20 последних публикаций.

9 957

подписчиков
Статистика канала