ቅድስት
ቅዱስ ያሬድ ለዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት የሰጠው ስያሜ “ቅድስት” የሚል ነው፡፡ ቅድስት ‹‹ቀደሰ›› ከሚለው ሥርወ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ቀደሰ፣ ለየ፣ አከበረ የሚል ነው፡፡ በዚህ መሠረት ቅድስት የሚለው ቃል የተለየች ክብርት ንጽህት የሚል ትርጔሜ ይሰጠናል፡፡ ቅዱስ የሚለው ቃል የባሕርይ ቅድስና ካለው ከእግዚአብሔር በጸጋ የቅድስና ሀብት ለተሰጣቸው አካላት ኹሉ ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ፡- ቅዱሳን ሰዎች፣ ቅዱሳን መላእክት፣ ቅዱሳት መካናት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እና ቅዱሳት ዕለታት ይገኙበታል፡፡ በዚሁ መሠረት የሰንበትን ቅድስና አስመልክቶ ጌታችን ያስተማረው ትምህርት በዜማ (በምስባክ) እንዲሁም በንባብ እየተነበበ በዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሣምንት ይተረጎማል፡፡
“እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ፤ አሚን መሠናይት ቅድሜሁ፤ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፤ ምስጋናና ውበት በፊቱ፣ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው” (መዝ. 95፥5-6) ከሚለው የዳዊት መዝሙር ተወስዶ የሚሰበከውን ምስባክ መምህራን እየተረጎሙ ያስተምሩበታል፡፡ “ቅድስት” በተሰኘች የዐቢይ-ጾም ሳምንት ማቴ. 6 ከቁጥር 16-25 ያለው የጌታችን ትምህርት ይነበባል፤ በሊቃውንት ተተርጎሞ ትምህርት ይሰጥበታል፡፡
|| @AHATI_BETKERSTYAN