ክፍል ፯
ውድ የ አሐቲ ቤተክርስቲያን ቻናል ቤተሰቦቻችን እንደምን ቆያችሁ! ዛሬ ወደ ቤተ ክርስቲያን (ቤተ መቅደስ) በምንሄድበት ጊዜ ሊኖረን ስለሚገባው ዝግጅት እንማራለን።
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምንሄድበት ጊዜ እግራችንን ከመጥፎ ቦታ እንደምንጠብቀው ሁሉ ልባችንንም ከኃጢአትና ከበደል ልንጠብቀው ይገባል። ጠቢቡ ሰሎሞን በመክብብ 5:1 ላይ "ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ" እንዳለው።
ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ የውስጥም የውጭም ዝግጅት ያስፈልገናል።
1. የልቦና ዝግጅት
• ወደ ቤተ መቅደስ የሚገባ ሰው ከቂም፣ ከበቀል፣ ከክፋት፣ ከተንኮል እና ከዝሙት የጸዳ ልብ ሊኖረው ይገባል።
• ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ እግዚአብሔር ልባችንን ይመረምራልና ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 7:9 ላይ "እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራል" ይላል።
• ቂም እና ጥላቻ ይዘን ወደ ቤተ መቅደስ መቅረብ እንደሌለብን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ላይ ተገልጿል።
• እግዚአብሔር "የተሰበረ መንፈስን" እንደማይ ንቅ በመዝሙር 51:17 ላይ ተጽፏል።
• እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤል ካዘዛቸው ትዕዛዛት አንዱ የልቡና ግርዛት ነው (ዘዳ 10:16)። የልቦና ግርዛት ማለት ልባችንን ከቂም፣ ከበቀልና እግዚአብሔር ከማይወደው ነገር ሁሉ ማራቅ ማለት ነው።
ለምን የልቦና ዝግጅት ያስፈልገናል?
• እግዚአብሔር ልባችንን ይመረምራል፦ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 7:9 ላይ "እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራል" ይላል። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንሄድ ንጹሕ ልብ ይዘን መቅረብ አለብን።
• የተሰበረ መንፈስን አይንቅም፦ በመዝሙር 51:17 ላይ "የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።" ተብሎ እንደተጻፈ ልባችንን ዝቅ አድርገን በንስሐ መቅረብ አለብን።
• የልቦና ግርዛት፦ እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤል "የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ" (ዘዳግም 10:16) ብሎ አዟቸዋል። ይህም ማለት ልባችንን ለእርሱ ማስገዛት እና ከማይወደው ነገር ሁሉ መራቅ አለብን።
2. ንጹህ ልብስ መልበስ (የግል ንጽህናን መጠበቅ)
• ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ስፍራ ነውና ንጹህ ልብስ ለብሰን እና ንጹህ ገላ ይዘን መሄድ ይገባናል።
• ያዕቆብ ቤተሰቦቹን "እንግዶች አማልክቶቻችሁን ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሃንም ሁኑ ልብሳችሁንም ለውጡ" እንዳላቸው (ዘፍ 35:2)።
3. ነጭ ልብስን ማደግደግ (በትዕምርተ መስቀል መልበስ)
• ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ነጭ ልብስ መልበሳችን የተገባ ነው። ነጠላ ወይም ጋቢ በትዕምርተ መስቀል ቅርጽ መልበስ የክርስቶስን መከራ እና ሰማያዊ ክብራችንን እንድናስብ ይረዳናል። እንዲሁም ቅዱሳን መላዕክት ከእኛ ጋር እንዳሉ እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጠልን እንድናስብ ያደርገናል።
• የክርስቶስን መከራ ማሰብ: ነጠላውን በትዕምርተ መስቀል ስናደርግ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የደረሰበትን መከራ እናስባለን።
• የሰማያዊ ክብራችንን ተስፋ ማሰብ: ነጭ ልብስ የሰማይ ክብር ምሳሌ ነው። በሃይማኖት ጸንተን ከኖርን በሰማይ የምናገኘውን ክብር እንድናስብ ይረዳናል።
• ቅዱሳን መላእክት ከእኛ ጋር እንዳሉ ማሰብ: ነጭ ልብስ የለበሱ መላእክት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከእኛ ጋር እንዳሉ እና ሁልጊዜም እንደሚረዱን እንድናስብ ያደርገናል።
• የጌታችን መገለጥን ማሰብ: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠ ጊዜ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ እንደነበረ እናስባለን (ማቴዎስ 17:2)።
4. መባዕ (ስጦታ) ይዞ ማቅረብ
• ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ባዶ እጃችንን ሳይሆን መባዕ ይዘን መሄድ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ራሱ ስጦታ ማቅረብ እንዳለብን አስተምሮናል።
• በብሉይ ኪዳን "ስጦታዬን ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ተናገር" (ዘጸአት 25:2) ብሏል። በሐዲስ ኪዳንም "መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ" (ማቴዎስ 5:23) የሚል ቃል አለ።
5. በትዕምርተ መስቀል አማትቦ ደጃፍን መሳለም
ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባ በመስቀል ምልክት አማትበን ደጃፉን እንስማለን።
• የማማተብ ትርጉም: ጣቶቻችንን በትዕምርተ መስቀል ስናመሳስል የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት እንመሰክራለን። ከላይ ወደ ታች እና ከግራ ወደ ቀኝ ስናማትብ የክርስቶስን ከሰማይ መውረድ እና ከ ሲኦል ወደ ገነት ማሻገሩን እናስባለን።
• ደጃፉን የምንሳለምበት ምክንያት: ቤተ መቅደሱ የክርስቶስ ማደሪያ እና ቅዱስ ስፍራ ስለሆነ ነው።
6. በቤተ መቅደስ ፊት መስገድ
• ወደ ቤተ መቅደስ ለጸሎት የሚገባ ሰው ደጀፉን ከተሳለመ በኋላ ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት ሊሰግድ ይገባዋል። ነብየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝሙር 138:2 ላይ "ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ" እንዳለው።
7. በቤተ መቅደስ ዙሪያ ያሉትን ቅዱሳን ሥዕላትን እጅ መንሳት
• በቤተ መቅደስ ዙሪያ ያሉ ቅዱሳን ሥዕላት አሉ።
• ብናከብራቸው የስዕሉን ባለቤት በማሰብ ተገቢውን ክብር ብንሰጣቸው ከስዕሉ ባለቤት ( ከቅድሱ ወይም ከቅድስቲቱ) በረከት እንቀበላለን፡፡
ማጠቃለያ
ወደ ቤተ መቅደስ በጸሎት ስንቀርብ መንፈሳዊ ጉዞአችን የተሟላና ፍሬያማ እንዲሆን ልባችንን፣ ሰውነታችንንና አለባበሳችንን ማዘጋጀት ያስፈልገናል። ከቂምና ከበቀል የጸዳ ልብ፣ ንጹሕ ልብስ፣ መባዕ ይዞ መቅረብ፣ በትዕምርተ መስቀል አማትቦ ደጃፉን መሳለም፣ በቤተ መቅደስ ፊት መስገድና የቅዱሳንን ሥዕላት ማክበር ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚያስፈልጉን ቁልፍ ነገሮች ናቸው። እነዚህን በማድረግ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችንና ነፍሳችን እንደምናመልክ እናሳያለን ::
ይህን መልዕክት ለሌሎችም በማጋራት ያወቅንውን እንድናሳውቅና ና በረከትን እንድናገኝ እንጋብዛችኋለን እንዲሁም ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካላችሁ ግሩፑ ላይ አሳውቁን እንመልሳለን
በቀጣይ ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ ነገሮች......
|| @AHATI_BETKERSTYAN