Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
📹እየተዝናናቹህ ብዙ የህይወት ልምድ የምታገኙበት ምርጥ ፖድካስት ልጋብዛቹህ
ይህ ሰው እናቱ በልጅነቱ አሜሪካ ሄዳ ከአያቱ ጋር በቅንጦት ያደገ ሲሆን እስከ 12 ኢትዮጵያ ውስጥ ከተማረ በኋላ የኮሌጅ ትምህርቱን የአሜሪካ ስኮላርሺፕ በማግኘት ተምሯል። የአሜሪካን ወታደር ሆኖም ብዙ መልካም ትውስታዎች አሳልፏል።ከውትድርና ህይወት በኋላም በፍቅር ታውሮ ካናዳ ድረስ በመሄድ የህይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ገብቷል። ከካናዳ ህይወቱ መልስ አሜሪካ ላይ ከማይሆኑ ሰዎች ጋር ጓደኛ ሆኖ ወንጀል ውስጥ በመግባቱ(ዕፅ ዝውውር) በኛ አቆጣጠር 1997 ላይ ከአሜሪካ deport ተደርጓል።
🇺🇸ከአሜሪካ deport ከተደረገ ከ20 ምናምን አመታት በኋላ አሁንም ድረስ የአሜሪካ ወታደር ሲሰደብ ወይም የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ክብሩ ዝቅ ሲል ያመዋል።
ይህ ሰው አሜሪካ ላይ በአፍላ እድሜው ከዝነኞች ጋር እስከ ጥግ ተቀራርቧል።ጀርመን ላይ የአሜሪካ ወታደር ሆኖ ብዙ ቆይቷል። ኳታር በረሃ ላይ ሳዳምን ለመጣል ዘምቷል።ሳዑዲ ላይ በሳዑዲ ህግ እርምጃ ሲወሰድ ቆሞ አይቷል። አምስተርዳም ከተማ ላይ በአጭሩም ቢሆን ፏ ብሏል።ካናዳ አግብቶ ወልዶ ኋላም ተፋቶ ህይወትን አይቷል።
📌 ይህ ሰው ያሳለፋቸውን ታሪኮች የሚተርክበት መንገድ እጅጉን ማራኪ ሲሆን ሲበዛ ግልፅ እና ተጫዋች ነው።
የዚህ የ69 ዓመት ሰው ታሪክ ለወጣቶች በተለይም ውጭ ሀገር ለምትሄዱ ሰዎች በብዙ አስተማሪ ነው።
በመጨረሻም እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ....ምክር ምከር ብትባል የምትመክረው ምክር ምንድነው?
👉 ለጊዜው የከፋ ነገር ቢሆንም ቤተሰቦችህንም የሚያስከፋ ቢሆንም Be honest ከሁሉም ነገር በላይ እውነታውን ተናገር።
👉 ያለህን ነገር ስጥ። እንደ መስጠት ጥሩ ነገር የለም። ምክርም ይሁን ያለህን አንድ ዳቦ ማካፈል ይሁን ስጥ።
👉 በቀን ውስጥ ቢያንስ አንድ ሰው ለማሳቅ(ደስተኛ ለማድረግ) ሞክር።
👉 ከሰው የተቀበላችሁትን እቃ እንደነበረው አድርጋቹህ መልሱ። አታቆዩት።
ሙሉ ፖድካስቱን ለመስማት 👇
https://youtu.be/qIODzbIMq5o?feature=shared