Фильтр публикаций


Репост из: ATC NEWS
" የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ፥ " ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና በተናገሩበት ወቅት 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ፥ " እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


#COVID ተብሎ ቤት የተቀመጥን ሰሞን Applied Mathematics One በቴሌግራም በድምፅ ያስተማርኩበትን ቻናል መቀላቀል የምትፈልጉ ተማሪዎች ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ቼክ ማድረግ ትችላላችሁ ✌️


👇👇👇👇
https://t.me/Applied1Tutor


ከስድስት ዓመት በፊት ሙሉ ኮርሱን በቪድዮ ሰርቼ የነበረ ቢሆንም ዩትዩብ ቻናሌ ሲዘጋ ሙሉ ቪዲዮዎቹም አብረው ስለጠፉና እኔም ቪዲዮ ከጫንኩ በኋላ የትም save ስለማላደርግ የቪድዮ ትምህርቱን ላገኘው አልቻልኩም። ብዙ ልጆች በውስጥ applied 1 ስለምትጠይቁኝ ይሄን የድምፅ እና የምስል ትምህርት እንደ አማራጭ ተጠቀሙበት።

ኮርሱን በመማር ላይ ለሚገኙትም ሼር አድርጉላቸህ
👇👇👇👇
https://t.me/Applied1Tutor


Репост из: ATC NEWS
በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ድግሪ እና በላይ ለተመረቃችሁ ምሩቃን በሙሉ:-

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መምህራንን አቅርቦት ለማሳደግ የተለያዩ የስልጠና ሰርዓቶችን ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት አጠናቋል፡፡

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያ ድግሪና በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላችሁ ምሩቃን ከታች የተያያዘውን link በመጠቀም የፅሁፍ መጠይቁን እንድትሞሉ

https://forms.gle/N8uPaW7uXYTEZWQC8

(ትምህርት ሚኒስቴር)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


ተመርቀው ስራ ያጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በፈቃደኝነት ለአንድ ዓመት ማህበረሰባቸውን ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ተደርጎ ትጋታቸው እና ብቃታቸው ታይቶ ወደ መምህርነት ሙያ እንዲቀላቀሉ ማድረግ ይሻላል ወይስ መቼ ነው ምመረቀው እያሉ የሚማሩ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን በግዳጅ ከመመረቂያ ጊዜያቸው አንድ ዓመት ጨምሮ እንዲያስተምሩ ማድረግ?

በመማር ላይ ያሉ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው የግድ በዚህ ፕሮግራም ማለፍ ያለባቸው ከተባለ ደግሞ የመመረቂያ ግዜያቸው ሳይራዘም ለጥቂት ወራት ማህበረሰባቸውን እንዲያስተምሩ ማድረግ ጥሩ አማራጭ ይመስለኛል።

3.7k 0 14 14 64

Репост из: ATC NEWS
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🎙የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ንግግር

ከተቻለ በሚቀጥለው ዓመት ካልሆነም በ2019 ዓ.ም. የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት የተማሩበትን ማህበረሰብ እንዲያስተምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

፨ይህ አዲስ አሰራር ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር ለምሳሌ አምስት ዓመት የሚማር የምህንድስና ተማሪ የአራተኛ ዓመት ትምህርቱን ሲጨርስ ለአንድ ዓመት የተማረበትን ማህበረሰብ እንዲያስተምሩ ይደረግና በቀጣዩ ዓመት አምስተኛ ዓመት ትምህርቱን ይቀጥላል። ከዚያም ይመረቃል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


ይሄን ነገር መጫወት ለምትፈልጉ ተጀምሯል ✌️


Urgent ‼️

በዚህ ምስል ላይ ያለሐው ግለሰብ ከ PHD ቤተ መጻሕፍት (ከዋናው ሬጅስትራር) የወሰድከውን PC ለደሕንነትሕ በማያሰጋ መልኩ ከዚሕ በታች በምናስቀምጥልሕ ስልክ ወይም በቴሌግራም በማዋራት እንድትመልስ እንጠይቃለን ፣ ይሕ ካልሆነ ግን በድሕንነት ካሜራ የተቀረፀ ምስል እና ቪዲዮ ስላለ በማሕበራዊ ትስስር ግፅ የምንለጥፍ እና በሕግም የምንጠድቅ ይሆናል ፣ PC' ውስጥ ብዙ የተለፋበት የምርምር ስራ ስላለው እንዲመለስልኝ
ሁላችሁም ይሕን መልዕክት ለዚሕ ግለሰብ እንዲደርስ #Share አድርጉ
እመሰግናለው
ባለ ንብረት፣ ለማ ሚደቅሳ
0911796294


Репост из: ATC NEWS
#EntranceExam #2017

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች #በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡ በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

👉ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-

1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣

2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።


[የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት]


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


በ20 ለተገረማቹህ ወገንታት እና ህዝብታት

፨ፍሬሽ ማን እያለሁ

👉 ሻይ 1ብር
👉ምግብ 10-15ብር
👉ነጭ ወረቀት የብር ሶስት አራት
👉 ሰላም ባስ 250ብር


ግቢ ውስጥ የኔ ትልቁ ወጪ ሻይ ነበር። ቡና አልጠጣም።ካርድ አልሞላም።


አንደኛ እና ሁለተኛ ዓመት ላይ ምንም ዓይነት ገቢ አልነበረኝም።

ኑሮም በጣም መጦዝ የጀመረው ከኮቪድ በኋላ ነበር ✌️

3k 0 3 15 14

ባንክ ቤት ተሰልፌ 20ብር ያወጣሁ ሰው ነኝ 😊

#ግቢ




🚍 Help Improve Public Transport in Ethiopia! 🚍
We are developing Derash, a mobile app to solve public transport challenges like:
✅ Long wait times
✅ Overcrowding & safety concerns
✅ No real-time bus tracking
✅ Lack of cashless payment options

💡 Your opinion matters! Take this quick 2-minute survey and help shape the future of public transport.

📣  click the link to participate!

👇👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeW9_gPyh8KfgqN0DDQ1UgIr9lxRL8Thra-oi7k6K60GE5-TQ/viewform?usp=preview

Thank you for your support! 🙌


Management Exit Exam Full Day Schedule.xlsx
308.8Кб
Management Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Tuesday February 04, 2025 (ጥር 27/2017 ዓ.ም)

9.8k 5 50 14 10

Accounting Exit Exam Full Day Schedule.xlsx
301.5Кб
Accounting Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Monday February 03, 2025 (ጥር 26/2017 ዓ.ም)


Репост из: ATC NEWS
ዛሬ ምሽት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አነስተኛ የእሳት አደጋ አጋጥሞ የነበረ ሲሆን እሳቱ በአሁኑ ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋሉን የግቢው ተማሪዎች ነግረውናል።

ከእሳት አደጋው ጋር በተያያዘ ከቤተ-መፃህፍ ለመውጣት በነበረ ጥድፊያ ቀላል ጉዳት ያስተናገዱ ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን የግቢው ተማሪዎች ጨምረው ነግረውናል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


🧐




ይሄ ቲክቶክ ብዙ ልጆችን ማሰብ እንዳይችሉ አድርጓል።

እባካቹህ በምን እንደምትቀልዱ አርቃቹህ አስቡ‼️

ነገ እነዚህ ልጆች ይቅርታ እያሉ ቢነፋረቁም ይቅርታ ላያስጥላቸው የሚችል ከባድ ጥፋት ነው የፈፀሙት😢


Репост из: ATC NEWS
#Update

ማሳሰቢያ - ሁለት ቀን ብቻ ቀረው!

የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ( የ12 ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ስለሆነም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ ካላችሁ በነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን።

⚡️ያልተመዘገበ አይፈተንም❗️


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


ዩትዩብ ላይ የጥሪ ማስታወቂያዎችን ስታዩ ቪድዮው የተለቀቀበትን ቀን ተመልከቱ 🙏

Показано 20 последних публикаций.