⛔️⛔️የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች⛔️⛔️
👉 ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
👉በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
👉 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ- ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
👉መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም ከጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል መሆናቸውን ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።