TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ዶ/ር ምህረት ደበበ እና ዶ/ር እዮብ ማሞ

24 Aug 2023, 08:46

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

የትኩረት መዛባት
ከእቅድህ ክልል ውጪ በሆነው ነገር ላይ ትኩረትህን በመጣል ዘመንህን አታቃጥል፡፡ በየእለቱ የምታሰላስለው፣ የምታየው፣ የምትመኘውና ስሜትህንና ጊዜህን የምታሳልፈበትን ነገር አስበው፡፡ ይህ ነገር በወደፊት እቅድህና ዓላማህ ውስጥ የተካተተ ነገር ካልሆነ ወይም ከዚያ ጋር ግንኙነት ከሌለው የትኩረት መዛባት ውስጥ ነው ያለኸው፡፡

ወደ አንድ አቅጣጫ ለመድረስ ዓላማን ይዞ ወደፊት የሚሄድ ሰው የትኩረቱ ቅኝትና የስሜቱ ግለት በዚያው አቅጣጫ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የሚገሰግሰው ወደፊት፣ የሚያየውና የሚመኘው ግን የጎንዮሽ ወይም ወደኋላ ከሆነ የትኩረት መዛባት አለ፡፡

ከእቅድህና ከዓላማህ ውጪ ስለሆነ የሕይወት ዘይቤ ሲያወጡና ሲያወርዱ መዋል . . . ልታገኛቸው የማትችላቸውንና በሕይወትህ ምንም መዋጮ ሊያደርጉ ስለማይችሉ ሰዎች ሁኔታ ሲደመሙ ውሎ ማደር . . . ካለህ ወቅታዊ እውነታም ሆነ ከወደፊት እቅድ ጋር በፍጹም ሊጣጣምና ሊዋሃድ በማይችል አለም ውስጥ በሃሳብ ሲዋዥቁ መኖር . . . የተዛባ ትኩረት!

ዓላማህን ለይተህ እወቅ . . . እውነታህን ተቀበል . . . ትኩረትህን በዚያ ላይ ሰብስብ . . . ሃሳብህን፣ ምኞትህን፣ ስሜትህንና ያለህን አቅም ሁሉ በዚያ ላይ አውለው! የሆንከውን፣ ያለህን ነገርና ሁለንተናህን አስተባብረህ ወደፊት በመገስገስና እደርስበታለሁ ብለህ በማመን ባላቀደከው ነገር ላይ አይንህንና ሃሳብህን በመትከል ጊዜህን አታባክን፡፡

የትኛው ንስር ነው ከፍታው ላይ መብረሩንና መናጠቁን ትቶ የሜዳ እንስሶችን ሩጫ ሲመኝ የሚውለው? የትኛው አንበሳ ነው ደኑን እየገዛና እያደነ ከመኖር ይልቅ በውሃ ዳር ሆኖ የአሳዎችን ዋና በማየትና በመመኘት ጊዜውን የሚያሳልፈው? . . .  እነዚህ ምሳሌዎቻችን የወደፊታቸው በሌለበት ነገር ላይ ጊዜያቸውን አያባክኑም፡፡ ትኩረትህን ወደ ማንነትህና ወደነገው ዓላማህ መልስ!

Join us.....
     @Ab_book
     @Ab_book
     @Ab_book

1.7k 0 14
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Наш блог Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot