Репост из: Bahiru Teka
🚫 ሙአዚኖች አላህን ፍሩ
➧ ኢስላም ለኢማምና ሙአዚን ትልቅ አክብሮት ችሯል። የሙአዚን ሚናው ከተሸከመው ሀላፊነት አንፃር ከባድ ነው። እንዳጠቃላይ የሙስሊሞች ሶላት በተመይ ዑዝር ኖሯቸው እቤት የሚሰግዱ ሰዎች፣ የሴቶች፣ ሶላት በሙአዚኑ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነው።
↪️ የረመዳን ወር ፆም መያዣና መፍቻም በሙአዚኑ ጫንቃ ላይ ነው። ሙአዚን እንዲህ አይነት ሀላፊነት የተሸከመ ሲሆን አብዛኞቹ የኛ ሀገር ሙአዚኖች አዛን ማለት ትርጉሙም ሆነ አላማው የገባቸው አይመስልም። አንዳንዱ ከ15 ደቂቃ በፊት ሌላው ሌላው ከ20 ደቂቃ በኋላ አዛን ያደርጋሉ። ይህ ማለት ሰዎች ያለ ሳአቱ እንዲሰግዱ እንዲያፈጥሩ ያደርጋል።
➲ ሶላታቸው ውድቅ የሆነባቸውና ፆማቸው የተበላሸባቸው ሰዎች ወንጀል እነርሱ ላይ ነው የሚሆነው። በመሆኑም ሙአዚኖች አላህን ፈርተው አዛንን በጊዜው በማለት የሙስሊሞችን ዒባዳ ጠብቀው በአዛን የሚገኘውን ምንዳ እንዲያገኙ ማድረግ አለባቸው። የየመስጂዱ ኮሚቴዎች ሙአዚኖችን በማስታወስና ወቅቱን ጠብቀው አዛን እንዲያደርጉ በማድረግ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል እላለሁ።
⛱ አላህ በመልካም ከሚተዋወሱት ያድርገን።
http://t.me/bahruteka