የሱብሒ አዛን❗️
• ከሌሎች የሶላት አዛኖች በተለየ መልኩ በሱብሒ አዛን ላይ የምትጨመር ቃል አለች፡፡ «አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም» ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡― የምትል፡፡ አዎን ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡
▶እንቅልፍ የሥጋ ጥሪ ነው፤ ደከመኝ አሳርፉኝ ይላል። ሶላት የአላህ ጥሪ ነው፡፡ አላህ ወደኔ ኑ እረፉ ይለናል፡፡
▶ እንቅልፍ ሞት ነው፤ ሶላት ደግሞ ሕይወት፡፡ በሶላትህ ነፍስ ዝራ፣ ከነፍስህ ጌታ ጋር ተገናኝ፡፡
▶ እንቅልፍን አካልን ያሳርፋል፤ ሶላት ግን ቀልብን ያረጋጋል፣ መንፈስን ያሰክናል፡፡
▶ ሶላት የአማኞች መለያ ናት፤ ጌታ እንደሌለው ባሪያ ያለ ሀሳብ ዥው ብለህ አትተኛ፡፡ ተለይተህ ተነሳ፡፡
▶ እንቅልፍ ሲበዛ ያሰንፋል፣ ለድካምም ለዱካክም ያጋልጣል፡፡ተነስቶ መስገድ ንቃትን ይሠጣል፣ አካልን ያፍታታል፣ ፊትን ያበራል፣ ወዝን ይመልሳል፡፡
▶ የማለዳ አየር የተለየና ፀጥ ያለ ነው፡፡ ለዒባዳም፣ ሀሳብን አሰባስቦ አላህን ለመማፀንም ምቹ ነው፡፡
▶ በሶላት የተከፈተ ቀን ድል አለው፣ በረከትና ስኬት አለው፡፡
▶ ሱብሒ ላይ የሚተኛ የሸይጣን ምርኮኛ ነው፤ ለሸይጧን ጆሮ የሠጠ ነው፡፡ አልነጋም ተኛ ይለዋል፡፡
የሱብሒ ጊዜ እንዴት ያማረ ጊዜና ዉብ ሰዓት መሠላችሁ!
☞ የሱብሒ ሶላት ሱንናው በዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
☞ የሱብሒ ሶላት ግዴታው የአላህን ጥበቃና ዋስትና ያስገኛል፡፡
በርግጥም «አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም'ን» እየሰሙ «ሐይየ ዐላ ሶላህ፣ ሐይየ ዐለል ፈላሕ'ን» እያዳመጡ መተኛት ይከብዳል።
ወዳጆቼ ለይል ቢያቅተን አሁን ላይ ሆነን ሱብሒን ብናስብ ምን ይለናል!?
منقول
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik