◉ ፅኚ በሂጃብሽ !!
በሱረቱል አህዛብ በደማቅ ተከትቧል
ከአንገትሽ ቀናበይ ታሪክሽ ተውቧል
ድንቅ ነው ኢስላምሽ ከአምላክ የተሰጠሽ
ቅይጥ የሌለበት ጥርት ያለ ሀብትሽ
እስኪ መለስ በይ እልፍ አመታትን
ትእዝዛ ሲመጣ ወህይ ከአምላካችን
እንዴት ነበረ እስኪ ድንቁ ታሪካችን?
የሂጃቡ ኣያ ሲወርድ ለአለማት
ያኔ ሲታዘዙ እኒያ ሶሀቢያት
ሀገሩን አስዋቡት በጥቁር ቀለማት
በኒቃብ በጅልባብ አበሩ በውበት።
አንቺስ ምንሽ ሞኙ ማማር የምትጠይው
በሂጃብ ተውበሽ አምላክሽን ታዘዢው
አዎ ታዘዢው ሀያሉን ህልምሽ እንዲሳካ፤
በዱንያም በአኼራም እንድትይ ፈካ
አትስጊ በፍፁም ባል ይጠፋል ብለሽ
እዝነቱን ፈልገሽ ኒቃብ በመልበስሽ
አንቺ ጀግና ሆነሽ ለትእዛዙ ካደርሽ
ቤትሽን ያንኳኳል ይቆማል ከበርሽ።
ዒልምሽን ተማሪ ጠዋት ማታ ድከሚ
ጅህልናን ለመግፈፍ በደሊል ታከሚ
በሰላሙ ጊዜ ስንቅሽን ካልሰነቅሽ
ጎታችሽ ይበዛል አንችም ትሄጃለሽ
ስለዚህ እህቴ ዒልም ላይ ጠንክሪ
አሰሱን ገሰሱን ቆሼ ፍርፋሪ
እንደ እስፓንጅ አትምጠጭ ፈጣሪሽን ፍሪ
አህባሹ ሲመጣ ከአህባሽ አትስፈሪ
ከኢኽዋን ዘናጩ ከሱናው ርቆ
ላይሽ አልመኝም ያ ውበትሽ ደርቆ
ከጀምዒይ ለስላሴ ልወደድ ባይ ከንቱ
ላይሽ አልመኝም ስትቀሪ ከንቱ።
ያንቺ መታለልሽ መሸወድ ሳይበቃ
ትውልድ ይበላሻል የኢስላም ውድ እቃ
የነገውም ተስፋ ያ እንቁ ፀሀይ
አንድነት ይሰብካል ከኢኽዋን ስትውይ
ከተውሂድን ይርቃል ከሱና ሰማይ
ከአህባሽም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል፤
ከተውሂድ ርቆ በሽርክ ይደበቃል
በዱአው አሳቦ ከሱስም ይወድቃል
ከድቤ ዳንኪራ አጥር ይወሸቃል
ከተብሊጉም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል
ኡሉህያን ርቆ እድሜውን ይፈጃል
በ 3 በ40 ቀን በተብሊግ ፍከራ
ወገኑን ሊታደግ ተውሂድ ሳይጣራ
እድሜውን ይፈጃል አንድ ውል ሳይሰራ
ለዚህ ሁሉ ስህተት ምክንያቷ አንቺ ነሽ
በኢስላም ስር ውለሽ መንሀጅ ስላልገባሽ
መሰረት የጣልሽው ካለቦታው ሆኖ
ግንቡን አፈረሽው የትም ቀረ ተኖ
ሰንደቅሽ ከፍ ብሎ ሁሌም እንዲያምርብሽ
እዛም እዛም አትበይ ይለይ መንሀጅሽ
እውነቱን ልንገርሽ የሂጃብሽን ዋጋ
ሊያናግርሽ ያፍራል ካንቺ የተጠጋ
መናቅኮ አይደለም ክብር ስላለው ነው
ሊቀርብሽ ያልቻለው በሩቁ የሸሸው
አንቱታን አተረፍሽ በ15 አመትሽ
ድል አጎናፀፈሽ ኒቃብ በመልበስሽ
ወለም ዘለም አትበይ ፅኚ በሂጃብሽ
ፊትናም አትፍጠሪ ተደበቂ ቤትሽ
ምድር ሁኝ ለባልሽ ሰማይ እንዲሆንልሽ፤
ክብርን አጎናፅፊው እሱም እንዲያከብርሽ
ደሞ ሴቶች አሉ ፀጉር የሚቆልሉ
ሂጃብ ለበስን ብለው የሚንቀዋለሉ
ረሱል ተራግመዋል ብለሽ ስትነግሪያቸው
አቦ አታጠባብቂ እነሱን ተያቸው
ገና አልሰለጠኑም ኃላ ቀር ናቸው
ብለው ያሾፋሉ ሞኛ ሞኝ ናቸው
ፀጉር መቆለሉ ደሞም መወጣጠር
ቅርፅን ማሳየቱ ሂጃብን መወርወር
ይሄ አይደል መስፈርቱ ለትዳርሽ መስመር
ይልቅማ አዳምጪኝ ለትዳርሽ ማማር
ዘላቂው መፍትሄ በሰላም ለመኖር
ሁሌ ለመወደድ ሁሌም ለመፈቀር
ሂጃብ ነው ሚስጥሩ ልቀቂው ከላይሽ
ሀያእም ተላበሽ አርጊው ጎረቤትሽ
ፈላስፋም አትሁኝ ማስረጃን ሰንቂ
ለምትሰሪው ስራም ደሊሉን እወቂ
ይህንን ካደረግሽ እህቴ እወቂ
ፍፁም አትወድቂም የለሽም ነቅናቂ።
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
በሱረቱል አህዛብ በደማቅ ተከትቧል
ከአንገትሽ ቀናበይ ታሪክሽ ተውቧል
ድንቅ ነው ኢስላምሽ ከአምላክ የተሰጠሽ
ቅይጥ የሌለበት ጥርት ያለ ሀብትሽ
እስኪ መለስ በይ እልፍ አመታትን
ትእዝዛ ሲመጣ ወህይ ከአምላካችን
እንዴት ነበረ እስኪ ድንቁ ታሪካችን?
የሂጃቡ ኣያ ሲወርድ ለአለማት
ያኔ ሲታዘዙ እኒያ ሶሀቢያት
ሀገሩን አስዋቡት በጥቁር ቀለማት
በኒቃብ በጅልባብ አበሩ በውበት።
አንቺስ ምንሽ ሞኙ ማማር የምትጠይው
በሂጃብ ተውበሽ አምላክሽን ታዘዢው
አዎ ታዘዢው ሀያሉን ህልምሽ እንዲሳካ፤
በዱንያም በአኼራም እንድትይ ፈካ
አትስጊ በፍፁም ባል ይጠፋል ብለሽ
እዝነቱን ፈልገሽ ኒቃብ በመልበስሽ
አንቺ ጀግና ሆነሽ ለትእዛዙ ካደርሽ
ቤትሽን ያንኳኳል ይቆማል ከበርሽ።
ዒልምሽን ተማሪ ጠዋት ማታ ድከሚ
ጅህልናን ለመግፈፍ በደሊል ታከሚ
በሰላሙ ጊዜ ስንቅሽን ካልሰነቅሽ
ጎታችሽ ይበዛል አንችም ትሄጃለሽ
ስለዚህ እህቴ ዒልም ላይ ጠንክሪ
አሰሱን ገሰሱን ቆሼ ፍርፋሪ
እንደ እስፓንጅ አትምጠጭ ፈጣሪሽን ፍሪ
አህባሹ ሲመጣ ከአህባሽ አትስፈሪ
ከኢኽዋን ዘናጩ ከሱናው ርቆ
ላይሽ አልመኝም ያ ውበትሽ ደርቆ
ከጀምዒይ ለስላሴ ልወደድ ባይ ከንቱ
ላይሽ አልመኝም ስትቀሪ ከንቱ።
ያንቺ መታለልሽ መሸወድ ሳይበቃ
ትውልድ ይበላሻል የኢስላም ውድ እቃ
የነገውም ተስፋ ያ እንቁ ፀሀይ
አንድነት ይሰብካል ከኢኽዋን ስትውይ
ከተውሂድን ይርቃል ከሱና ሰማይ
ከአህባሽም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል፤
ከተውሂድ ርቆ በሽርክ ይደበቃል
በዱአው አሳቦ ከሱስም ይወድቃል
ከድቤ ዳንኪራ አጥር ይወሸቃል
ከተብሊጉም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል
ኡሉህያን ርቆ እድሜውን ይፈጃል
በ 3 በ40 ቀን በተብሊግ ፍከራ
ወገኑን ሊታደግ ተውሂድ ሳይጣራ
እድሜውን ይፈጃል አንድ ውል ሳይሰራ
ለዚህ ሁሉ ስህተት ምክንያቷ አንቺ ነሽ
በኢስላም ስር ውለሽ መንሀጅ ስላልገባሽ
መሰረት የጣልሽው ካለቦታው ሆኖ
ግንቡን አፈረሽው የትም ቀረ ተኖ
ሰንደቅሽ ከፍ ብሎ ሁሌም እንዲያምርብሽ
እዛም እዛም አትበይ ይለይ መንሀጅሽ
እውነቱን ልንገርሽ የሂጃብሽን ዋጋ
ሊያናግርሽ ያፍራል ካንቺ የተጠጋ
መናቅኮ አይደለም ክብር ስላለው ነው
ሊቀርብሽ ያልቻለው በሩቁ የሸሸው
አንቱታን አተረፍሽ በ15 አመትሽ
ድል አጎናፀፈሽ ኒቃብ በመልበስሽ
ወለም ዘለም አትበይ ፅኚ በሂጃብሽ
ፊትናም አትፍጠሪ ተደበቂ ቤትሽ
ምድር ሁኝ ለባልሽ ሰማይ እንዲሆንልሽ፤
ክብርን አጎናፅፊው እሱም እንዲያከብርሽ
ደሞ ሴቶች አሉ ፀጉር የሚቆልሉ
ሂጃብ ለበስን ብለው የሚንቀዋለሉ
ረሱል ተራግመዋል ብለሽ ስትነግሪያቸው
አቦ አታጠባብቂ እነሱን ተያቸው
ገና አልሰለጠኑም ኃላ ቀር ናቸው
ብለው ያሾፋሉ ሞኛ ሞኝ ናቸው
ፀጉር መቆለሉ ደሞም መወጣጠር
ቅርፅን ማሳየቱ ሂጃብን መወርወር
ይሄ አይደል መስፈርቱ ለትዳርሽ መስመር
ይልቅማ አዳምጪኝ ለትዳርሽ ማማር
ዘላቂው መፍትሄ በሰላም ለመኖር
ሁሌ ለመወደድ ሁሌም ለመፈቀር
ሂጃብ ነው ሚስጥሩ ልቀቂው ከላይሽ
ሀያእም ተላበሽ አርጊው ጎረቤትሽ
ፈላስፋም አትሁኝ ማስረጃን ሰንቂ
ለምትሰሪው ስራም ደሊሉን እወቂ
ይህንን ካደረግሽ እህቴ እወቂ
ፍፁም አትወድቂም የለሽም ነቅናቂ።
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik