◉የረመዳን ወር አቀባበል!!
ክፍል ❶
ታላቁ እንግዳችን! የተከበረውን የረመዳን ወር ለመቀበል ሁሉም በየፊናው ተፍተፍ እያለ ይገኛል። ከፊሉ ቤቱን በማሰናዳት፣ ሌላው የምግብ አይነቶችን በመሸመት፣ እኩሉም የወሩን ትሩፋት ለመጠቀም እቅድ እያወጣ…ወዘተ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ለመሆኑ ይህ አያሌ የፈጣሪ ትሩፋትን በውስጡ ይዞ የመጣውን ይህን ወር ለመቀበል ትክክለኛው መንገድ የትኛው ነው?
በወሩ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን የጦዓ (አምልኮ) ወቅቶችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? በነዚህ በተከበሩ ጊዜያት ውስጥ በኸይር ነገሮች መሽቀዳደም ያስፈልጋልና፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
وَفِي ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ
“በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ።”(አል-ሙጦፊፊን 83፤ 26)
በመሆኑም ከዚህ በመቀጠል የረመዳንን ወር በተሻለ መንገድ ለመቀበል የሚረዱ መንገዶች እንጠቁማለን፡-
❶ ዱዐ ማድረግ፡- በፆም፤ በሶላትና በዚክር ላይ እንድትጠነክር አላህ (ሱ.ወ) በሙሉ ጤንነትና አቅም ላይ ሆነህ ረመዳን ወር እንዲያደርስህ ከአሁኑ ዱዓ አድርግ፤ አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረጀብ ወር ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር ብለዋል፡-
اللهم بارك لنا في رجب وشعبان وبلغنا رمضان
“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ብሩክ አድርግልን፤ ረመዳንንም አድርሰን” (አህመድና ጦብራኒ ዘግበውታል)።
ሰለፎች (ቀደምት ደጋግ አቦዎች) ረመዳንን እንዲያደርሳቸውና ከዚያም ሥራቸውን እንዲቀበላቸው አላህን (ሱ.ወ) ይለምኑ ነበር፤ ስለዚህ አንተም የረመዳን ጨረቃ ስትወጣ እንዲህ ብለህ ዱዓ አድርግ፡-
الله أكبر اللهم أهله علينا بالأمن والإيمان والسلامة والإسلام , والتوفيق لما تحب وترضى ربي وربك الله
“አላሁ አክበር አላህ ሆይ! ይህን ጨረቃ የአማንና የኢማን፣ የሰላምና የኢስላም፣ እንዲሁም አንተን የሚያስደስት ተግባር መስራት የምንችልበት ጊዜ አድርግልን፤ የኔም የአንተም ጌታ አላህ ነው፤” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)።
❷ ምስጋና ማቅረብ፡- ረመዳን ወር ከደረስክ ምስጋና ለአላህ አቅርብ፤ ኢማሙ ነወዊይ አል-አዝካር በተባለው ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል
“አንድ አዲስ ፀጋን ያገኘ ወይም አንድ ችግር የተወገደለት ሰው ለአላህን ምስጋና ለማቅረብ ሱጁድ አድረጎ አላህን በሚገባው መልኩ ማወደስ ይገባዋል።
”አላህን ማምለክና የሱን ትእዛዝ መፈጸም መቻል በራሱ አላህ (ሱ.ወ) ለአንድ ሙእሚን ከሚለግሰው ታላላቅ ፀጋዎች ነው።
አንድ ሙእሚን የረመዳን ወር ሲገባ በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘቱ ብቻ ፀጋውንና ችሮታውን ለለገሰው አላህ (ሱ.ወ) ምስጋና እንዲያቀርብ የሚያስገድደው በቂ ነገር ነው፤
ስለዚህ የረመዳንን ወር በሰላምና በጤና የደረሰ ሰው ለአላህ (ሱ.ወ) ትልቅ ምስጋና ሊያቀርብና እሱን በብዛት ሊያወድስ ይገባል፤ ለልቅናውና ለግዙፍ ስልጣኑ የሚመጥን ታላቅ ምስጋናና ውዳሴ ለአላህ (ሱ.ወ) ይሁን!!
❸ መደሰት፡- ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረመዳን ወር ሲመጣ እንዲህ በማለት ባልደረቦቻቸውን ያበስሩ እንደነበር ተረጋግጧ፡-
جاءكم شهر رمضان شهر مبارك كتب الله عليكم صيامه فيه تفتح أبواب الجنان وتغلق فيه أبواب الجحيم
“የተባረከው የረመዳን ወር መጥቶላችኋል፤ እሱን መፆም አላህ (ሱ.ወ) በናንተ ላይ ደንግጓል፤ በረመዳን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የገሀነም በሮች ደግሞ ይዘጋሉ”(አህመድ ዘግበውታል)።
ሰሐባዎችንና ታቢዒዮችን ጨምሮ ያለፉት ደጋግ አቦዎች (ሰለፎች) ለረመዳን ወር ልዩ ትኩረት ይሰጡ ነበር፤ ረመዳን ሲመጣም ይደሰቱ ነበር፤ አዎ ይህ ትልቅ ደስታ ነው!
የኸይርና የአላህ እዝነት መውረጃ የሆነ ወቅት ሲመጣ ጤና ሆኖ በሂይወት ከመኖር የበለጥ የሚያስደስት ነገር አለን?!
❹ ወሩን በአግባቡ ለመጠቀም መወሰንና ቀድሞ እቅድ ማውጣት፡- ብዙ ሙስሊሞች- ዲነኞችን ጨምሮ- ለዱንያ ጉዳያቸው በሚገባ እቅድ ሲያወጡ ይታያሉ፤ ነገር ግን ለአኺራቸው እቅድ በማውጣት የሚሰሩት ጥቂቶች ናቸው።
ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሙእሚን በዚች ህይወት ያለውን መልዕክት ካለመረዳትና አንድ ሙእሚን ነፍሱ በአላህ ዲን ላይ ፅናት እንዲኖራት ራሱን ለማለማመድ ከአላህ ዘንድ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎች ችላ ከማለት የሚመነጭ ነው።
ለአኺራ ከምናቅድባቸው ጉዳዮች መካከል የረመዳንን ወር በጧዐና ኢባዳ ለማሳለፍ የምናደርገው ዝግጅትና እቅድ አንዱ ነው፤ ስለሆነም ማንኛውም ሙስሊም የረመዳንን ወር በትክክል አላህን በመታዘዝ ማሳለፍ እንዲችል ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም ማውጣት ያስልገዋል።
❺ ቁርጠኛ አቋም፡- የረመዳንን ወር በመልካም ሥራዎች ለመሙላት ቁርጠኛ አቋም መያዝ። ከልቡ በእውነት ወደ አላህ የቀረበ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ እሱን ለመገዛትና ኸይር ለመስራትም ያግዘዋል፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
فَلَوْ صَدَقُوا اللَّهَ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ
“እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር።” (ሙሐመድ 47፤ 21)
#ሼር #ሼር ይደረግ
ክፍል ❷
ይ
ቀ
ጥ
ላ
ል
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik