በባል ላይ ባል መደረብ
~
አንዳንድ ሴቶች ከባላቸው ጋር ፍች ሳያፈፀም ሌላ ሰው "ያገባሉ"። ከባሏ በፍች እንዳልተለያየች እያወቀ የማይሆነውን "ኒካሕ አስሬያለሁ" ብሎ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር በዝሙት የሚጨማለቅ ወንድ በተጨባጭ አለ። ይሄ ከባድ ጥፋት ነው። ፍቺ ባልተፈፀመበት ሁኔታ አንዲት ሴት ለሌላ ወንድ ፈፅሞ ሐላል አትሆንም።
ስለዚህ ከባሏ ጋር መኖር አቅቷት መለያየትና ሌላ ሰው ማግባት የፈለገች ሴት ከባሏ ፍቺ ማግኘት አለባት። እሱ ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም ደግሞ ለረጅም ዘመን ከአገር ርቆ ሊገኝ ካልቻለ ጉዳዩን ፍርድ ቤት በማቅረብ በቀላሉ በቃዲ መጨረስ ይገባል። ይህ እስከሚሆን ድረስ ከሌላ ሰው ጋር ኒካሕ መፈፀም አይቻልም። ተደርጎም ከሆነ እንደ ኒካሕ ስለማይቆጠር ባስቸኳይ መለያየት ግድ ነው። ከዚህ ከሁለተኛው "ባል" ለመለያየት ፍቺ አያስፈልግም። ኒካሕ በሌለበት ፍች የለምና። የመጀመሪያው ኒካሕ ባልወረደበት ሌላኛው ኒካሕ ካለም አይቆጠርም። ስለዚህ ባለማወቅ ወይም በመዘናጋት በእንዲህ አይነት ነገር ውስጥ የወደቃችሁ ወገኖች ባስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ ውሰዱ።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor