አጭርና ቆፍጠን ያለች ማስታዎሻ ለሚቀበሉኝ በሙሉ።
በመካከላቸው ያለውን አለመግባባትና በሁሉም ዘንድ ያለውን ሰው በመሆናቸውና ፍፁምነትን ያልተሰጡ በመሆናቸው ሰበብ የተፈጠረውን ስህተት አሏህ አግርቶላቸው በሰከነ መልኩና ተከባብረው የነፍስያን ጣጣ አሽቀንጥረው ጥለው በመወያየት እስከሚፈቱት ድረስ ለሐቅ እየሰሩት ያለውን ጉልህ አስተዋፅዖ ባለመካድና በቻልኩት ለመቀራረባቸው ካልቻልኩም በመካከላቸው የተፈጠረባቸውን ፊትና ባለማባባስና ባለማሰራጨት እተባበራቸዋለሁ። አሏህ ሁሉንም ሰለፊዮች ሐቅን በሐቅነቱ አሳይቶ መከተልን ባጢልን በባጢልነቱ አሳይቶ መራቅን ይወፍቃቸው ዘንድ ብቸኛ ተለማኙንና በሁሉም ነገር ላይ ቻይ የሆነውን ጌታዬን ችክ ብዬ በመማፀን ወደሱውም እቃረብበታለሁ። የማንም ሳልሆን የአሏህ ጥገኛ ነኝና በድፍረቴ አትደመሙ። በእርግጥ በጣም ወደ ኋላ የቀረሁባችሁ ሊመስል ይችላል አሏህ ኸይር ነው ካለልኝ እንደዔሊ ብዘገይም ተከታይ መሆኔን እመርጣለሁና አልሰጋም። መንገዱ ረጅምና የጀመረው እንጅ የጨረሰው የለምና ብቻ በመንገዱ ላይ አሏህ ይግደለኝ። ሁላችንንም መጨረሻችንን ያሳምርልን። ወደ አማራ ክልል ገጠር መራቄ እንጅ ሶስቱንም(ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር፣ ኡስታዝ ባህሩ ተካ፣ ሸይኽ ኢሊያስ) በአካል አግኝቼ ለእርቅ ሰበብ ከማድረስ ተስፋ ውስጤ አልቆረጠም።
አቡ ሐኒፋ ዐብዱልከሪም ከገጠር
ቅዳሜ፣ ሸዋል 4፣ 1445 H.
ሚያዚያ 5፣ 2016 ዓ.ል.
Saturday, April 13, 2024 G.C.