ነጃ በለን ጌታዬዋ አደራህን እነጃው ጎራ...። ድንገተኛ ዝናብ ሲጥል አላግባብ ስንራወጥ አለቦታው የመጣ ጎርፍ እንዳያባልለን። በሱና ወንድሞች መካከል ከባድ የፊትና ዝናብ ዶፍ ሰሞኑን እየወረደ ይመስላል። ለማንኛውም በአደብ አሏህ ሁሉንም እውነት ለሐቅ ከሆነ ወደ አንድና ብቸኛ ሐቋ ይሰብስባቸው እላለሁ። ከዚህ ውጭ ለጊዜው ምንም የለኝም። ነገር ግን ጎርፉ ከላይ አላግባብ የተኮፈሰውን አረፋ ጠራርጎ ሲወስደው የትም እንደገባ በማይታወቅ መልኩ ያጠፋዋል፤ ለሰው ልጅ ጠቃሚ የሆኑትን ነገሮች ግን በማስመጥ ሰበብ ትቷቸው ይሄዳል። ከጎርፉ በኋላ ግን ጠቃሚዎቹ የሰመጡት ወይ በራሳቸው ወይም በፈላጊዎቻቸው ይገለጣሉ፤ ጊዜው ቢረዝምም ለጥቅም ይውላሉ። የፊትናው ጎርፍ እየጎረፈ ስለሆነ እንደማይጠቅመውና መድረሻው እንዳልታወቀው አረፋ ሳያደርገን ከቻልን አሁንም ቢሆን ወይም በአደብ ተርፈው ወደፊት እንደሚጠቅሙት ነገሮች ከመሆን የሚያግደንን አጓጉል በሸር ላይ መሪነትና መጥፎን የማሰራጨት ጥማት ይቅርብን። በኸይር ላይ እንከተል አደራ በሸር ላይ መሪ ከምንሆን። አሏሁመ ሰሊምና ሚነልፊተን ማዞሃረ ሚንሃ ወማ በጦን።