ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሊሰጡ እንደሚችል ተነገረ።
የቀድሞ የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስትር ሰር ጋቪን ዊሊያምሰን በቀይ ባህር ላይ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ስላላት የሶማሌላንድ ይፋዊ እውቅና ከትራምፕ የፖሊሲ ሀላፊዎች ጋር መነጋገራቸውን ለኢንዲፔንደንት ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ትራምፕ በመጪው ጥር ስልጣን በያዙበት ፍጥነት ለሀርጌሳ እውቅናን ሊሰጡ ይችላሉ ነው ያሉት።በ1991 ከሶማሊያ የተገነጠለችው ሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድታገኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት የቀድሞ ሚኒስትር ከትራምፕ የፖሊሲ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር ገልጸዋል።
በውይይቱም ለሀርጌሳ እውቅና መስጠት በቀጠናው ባሉ የውሀ አካላት እና አካባቢው ላይ ሊኖር የሚችለውን በጎ ተጽዕኖ ማስረዳታቸውን ነው የተናገሩት።ትራምፕ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ከወሰኗቸው የመጨረሻ ውሳኔዎች መካከል የአሜሪካን ጦር ከሶማሊያ ማስወጣት የሚለው አንዱ ነበር ሆኖም ይህ ውሳኔ በባይደን አስተዳደር ተሽሯል።
የቀድሞ የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት የነበረችው ሶማሊላንድ ከብሪታንያ ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት ያስቀጠለች ሲሆን የሀገርነት እውቅናን ለማግኝት የተለያዩ ባለስልጣናትን እንደምትጠቀም ይነገራል።የቀድሞ ሚኒስትር ለኢንዲፔንደንት እንደተናገሩት ትራምፕ እውቅናውን የሚሰጡ ከሆነ የቀጠናውን ጂኦፖለቲካ የሚቀይረው ይሆናል።
የሞቃዲሾን የሶማሊላንድ ይገባኛል ጥያቄ የሚደግፉት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እውቅና እንዲሰጣት የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል። ምንም እንኳን ሶማሊያ የአለም አቀፍ የባህር ላይ ወንበዴ እና የሽብርተኝነት ማዕከል ብትሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን አቋም አስቀጥለዋል።
@Addis_Mereja