Addis መረጃ™


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ ማቅረቡን ዳጉ ጆርናል ከፋና ዘገባ ተመልክቷል።

በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል።ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ፈቅዷል።

@Addis_Mereja


«ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ህወሓት ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል» ሲል የአማራ ክልል መግለጫ ሰጠ!

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ በእርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ሆነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡

ተቸንካሪነት ዋና መለያ የሆነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመሆኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈፀመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈፅሟል፡፡ በመሆኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ሕብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመሆኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ሆነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡

ሆኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ሚያዚያ 08 /2016 ዓ‹ም
ባሕር ዳር

@Addis_Mereja


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ!

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል።

@Addis_Mereja


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ!

አንድ የኢትዮጵያ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ቻይናዊ ሯጭ የቤይጂንግ ግማሽ ማራቶንን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ተጀመረባቸው።

የውድድሩ አዘጋጅ ቤይጂንግ ስፖርትስ ቢሮ ክስተቱን እየመረመርኩ ነው ሲል ለፈረንሳይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ተናግሯል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ቢቂላ እንዲሁም ኬንያውያኑ ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ማናንጋት ቻይናዊው አትሌት ሂ ጂ እንዲያሸንፍ ያደረጉበት ሁኔታን የተመለከቱ ቻይናውያን “ስፖርታዊ ሥነ ምግባር የሌለበት አሳፋሪ ተግባር” ሲሉ ገልጸውታል።

ሦስቱ አትሌቶች ከውድድሩ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ ቻይናዊውያን አትሌት አጅበው ሲሮጡ ነበር።በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት በተጋራው ቪዲዮ ላይ የውድድሩ መጨረሻ አካባቢ ሦስቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናዊው አትሌት እንዲያልፋቸው በእጃቸው ሲጠቁሙት ይታያሉ።

በመጨረሻም የመላው እስያ ጨዋታዎች የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ቻይናዊ አትሌት ሦስቱን የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች አስከትሎ በአንድ ሰከንድ ልዩነት ብቻ ውድድሩን አሸንፏል። የውድድሩ አዘጋጆች ለኤኤፍፒ “ምርመራ እያደረግን ነው። ምርመራችን ሲጠናቀቅ ውጤቱን ይፋ እናደርጋለን” ብሏል።

@Addis_Mereja


⚡️⚡️ቦሌ የነበረው ተኩስ

ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር

የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል።

ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት ከነበሩት ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወዲያውኑ የሞተ ሲሆን ናሁሰናይ ቆስሎ ቢያዝም ህይወቱ አልፏል ተብሏል። አንደኛው ምንም ሳይሆን ተይዟል ተብሏል።

ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንድ የሞተ ሲሆን የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት።
ከቦሌ SNAP PLAZA እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።

@Addis_Mereja

19.4k 0 60 24 201

ዛሬ በሳዑዲ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል!

ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

@Addis_Mereja

24k 0 5 16 87

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር ታካሂዳለች!

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር እንደምታካሂድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ገለፁ።አቶ ገብረ-መስቀል ጫላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ ጀምራለች። ይሁንና በኮቪድ 19 ወረርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ጥረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከቆመበት ለማስቀጠል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል።ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሐምሌ 2015 ዓ.ም ወደ ጄኔቫ አቅንተው ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

በውይይቱም ኢትዮጵያ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የድርድር ሂደቱ እንዲጠናቀቅና የድርጅቱ አባል እንድትሆን ከሥምምነት መደረሱንም ጠቁመዋል።በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር ለማድረግ ፍላጎት ካላቸው አባል ሀገራት 180 የሚጠጉ ጥያቄዎችና 9 ሰነዶች መቅረባቸውን ተናግረዋል።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ በሚያመቻቸው መድረክ ድርድሩ እንደሚጀመር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን የሀገሪቱን ጥቅም በሚያስጠብቅ እንዲሁም የኢኮኖሚ ልማትና የንግድ ተወዳዳሪነት በሚያረጋግጥ አግባብ ለመደራደር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል።ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት ውስጥ በታዛቢነት መሳተፍ የጀመረችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2003 ነበር።

ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን የእቃዎችና የአገልግሎት ንግድ ኦፈር፣ የገቢ ንግድ ፈቃድ አሰራር መረጃዎች፣ የመንግሥት የንግድ ድርጅቶች መረጃ፣ ንግድና ንግድ ነክ ሕጎች መርኃ ግብር እንዲሁም የወጪ ንግድ ድጎማና የግብርና ምርቶች ድጋፍ ሰነዶችን የማሟላት ሥራ እየሰራች መሆኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

@Addis_Mereja


የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል!

የዘንድሮው የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ አንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።ምክር ቤቱ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፥ የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም አንደሚከበር አስታውቋል።ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በጾም ወቅት ሲያደርግ እንደነበረው እርስ በርስ በመደጋገፍና ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል ሊሆን እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

Via FBC
@Addis_Mereja




ኣርጅናል ሽቶ በተመጣጠነ ዋጋ በ Elegant cosmetic store ከነፃ ትራንስፓርት ጋር


ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንደማይዘጉ አስታወቁ!

ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ በግዛቶቻቸው የሚገኙትን ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንዲዘጉ የተሰጠውን ትዕዛዝ እንደማይቀበሉ ዛሬ አስታወቁ።ሶማሊያ፣ በሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሀገር ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን፣ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ትላንት ኀሙስ፣ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር።

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን በመግለፅ ክስ ያሰማው የሶማሊያ መንግሥት፤ ሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰአት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መጠየቋን እና አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም መጥራቷን ትናንት አስታውቃ ነበር።በተመሳሳይም ከሶማሊያ የተገነጠለችውን የሶማሊላንድ ግዛት እና ከፊል ራስ ገዟን ፑንትላንድ በዚያ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሰባት ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ አዛለች።

ይሁንና ሶማሌላንድ በዋና ከተማዋ ሀርጌሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ሞቃዲሾ ያቀረበችውን ጥያቄ የሶማሌ ፌደራል መንግሥት እንደዚያ ያለ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ ውድቅ አድርጋለች።ሶማሊያ ኢትዮጵያ ባለፈው ጥር ወር ከሶማሌላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የባህር በር የተመለከተ ስምምነት፣ “ህገ-ወጥ” እና ሉአላዊነቴን የጣሰ ነው ስትል ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቷም ይታወቃል።

Via VoA
@Addis_Mereja


የአዲስ አበባ 'ልማት ኮሪዶር' ፕሮጀክትን በተመለከተ ዘ ጋርዲያን የተነሺዎችን ቅሬታ የያዘ መረጃ አጋርቷል

"ተነሺዎች ለዘመናት ከኖሩበት ቤት እንዲወጡ አምስት ቀን ብቻ እንደተሰጣቸው፣ ከዛም ከሶስት ቀን በኋላ ውሀ ሆን ተብሎ እንደተቋረጠባቸው እና ንብረታቸውን በማውጣት ትርምስ ውስጥ ዝርፊያ እና ውድመት እንደደረሰባቸው ለሚድያው ተናግረዋል"።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ተጫኑ

https://shorturl.at/ahuwW
@Addis_Mereja


መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ተዘገበ!!

ከነዚህም መካከል ከስራ ፈቃድ፣ ግብር፣ ቢሮ ኪራይ፣ ፋይናንስ አቅርቦት፣ ጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉት ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው ግዥ የቀጥታ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚፈቅድ ነው።

Via Capital
@Addis_Mereja


በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት አያገኙም እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድ ፍቃድ ምዝገባ አገልግሎት እስካሁን በነበረው አሰራር የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች አገልግሎቱን አንደሚያገኙ እና ለቀጣይም በዛው እንደሚገለገሉ ተነግሯል፡፡በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እነደተናገሩት የተሰራጨዉ መረጃ ስህተት ነዉ ብለዋል፡፡

ከሁሉም ተቋማት ጋር በመተባበር ለንግድ ስራ ፈቃድ አገልግሎት የሚያስፈልግ ግብአቶች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የግብር ክሊራንስ እና በሰነድ የሚረጋገጡ ነገሮችን በሙሉ ከተቋማቶቹ በቀጥታ ማግኘት የሚቻልበትን አሰራር እየዘረጋን እንገኛለል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ ተግባራዊ ሲሆን መረጃዎቹን ከተቋማቱ ማግኘት ስለሚቻል ሰዎች አገልግሎት ሲፈልጉ ጥያቄ የማቅረብ ስራ ብቻ እንደሚኖርባቸው አንስተዋል፡፡አሁን ላይ አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉት የገለፁት መሪ አስፈፃሚው እስከቀጣይ አመት ተጠናቆ ስራ ላይ ይውላል የሚል እቅድ መያዙን ተነግረዋል፡፡

Via Ethio FM
@Addis_Mereja


#NewsAlert

👉በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።

🌟የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

🚧ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።

⏺በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።

🖱ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦

➡ ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
➡ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
➡ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
➡ በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

@Addis_Mereja

13k 0 19 2 58

የጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር(1)(1).pdf
2.6Мб
#Update : የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

በከተማው በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ለጨረታ መቅረባቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝሩን የያዘው ፋይል ምንጭ የአ/አ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ መሆኑን ይገልጻል።

@Addis_Mereja


በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ!

ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ወራት ታግዶ የቆየው የመሬት አገልግሎት፣ የዜጎችን መብት የጣሰ እንደነበር በመናገር  ተገልጋዮች ሲያማርሩ ቆይተዋል።

አስተዳደሩ እንደገለጸው አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከቀን ከመጋቢት 23 ቀን2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን አስታውቋል።

Via Reporter
@Addis_Mereja


ስፔን ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ልትሰጥ ነው!

ስፔን ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና ለመስጠት መዘጋጀቷን አስታወቀች።ማድሪድ እውቅናውን የምትሰጠው በመጪው ሀምሌ ወር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ገልጸዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን በዮርዳኖስ የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በኳታር እና ሳኡዲ አረቢያ በሚኖራቸው ቆይታ በጋዛው ጦርነት ዙሪያ ይመክራሉ መባሉን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና የሰጡት ዘጠኙ ብቻ ናቸው።የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በአማን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለምልልስ፥ በርካታ የህብረቱ አባል ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና እንዲሰጡ ግፊት እየተደረገ ነው ብለዋል።

አየርላንድ፣ ማልታ እና ስሎቫኒያም እስራኤል በሃይል የያዘችው ዌስትባንክ እና የጋዛ ሰርጥ የፍልስጤም ሉአላዊ ግዛት መሆኑን በመቀበል እውቅና ለመስጠት መስማማታቸውን ሳንቼዝ ይፋ አድርገዋል።

እስራኤል የአራቱ ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና የመስጠት እቅድ “ለሽብርተኝነት የሚቀርብ ሽልማት” አድርጋ እንደምትመለከተውና የጋዛውን ጦርነት በንግግር ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የሚያውክ ነው በሚል ተቃውሞዋን ማሰማቷን ሬውተርስ ዘግቧል።

Via Alain
@Addis_Mereja


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አደረገ!

በባን
ኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መመለሳቸውን ባንኩ ገልጿል፡፡

ባንኩ "የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች አሉ ያለ ሲሆን ባንካችን ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንካችን ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት ተገደናል ብሏል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ባንካችን የተለያዩ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ያራዘመ በመሆኑ፣ ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ እያሳሰብን፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ የምናቀርብ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን ብሏል፡፡

ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይፋ አድርጓል።

https://combanketh.et/list-of-customers
@Addis_Mereja


አቶ አድም ፋራህ በም/ል ጠ/ሚ ማዕረግ ተሾሙ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ አደም ፋራህን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበሪያ ሃላፊ አድርገው መሾማቸውን ዳጉ ጆርናል ተሰምቷል።

@Addis_Mereja

Показано 20 последних публикаций.