በሶማሊላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ መጀመሩ ተገለጸ
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ንብረት የሆነው ዲፒ ወርልድ የሚያስተዳድረው የሶማሊላንዱ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀምሯል።
የዲፒ ወርልድ በርበራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ በማስጀመሪያ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ቢሮዎቹ ከወደብ የሚራገፉ ጭነቶችን ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚያሳልጥ መሆኑን ገልጸዋል።
የሶማሊላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስትሩ ሳድ አሊ ሺሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው "120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን መጠቀም ትችላለች" ብለዋል።
በተጨማሪም ቢሮዎቹ ስራ መጀመራቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና እና የኢንቨስትመንት ትስስር እንደሚያሳድገው አመላክተዋል።
በተጨማሪም ትልልቅ ጭነቶችን ጨምሮ በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከአውሮፓ የሚገቡ እንደ ስንዴ፣ ሩዝ፣ የተቀነባበሩ ምግቦችና ማሽነሪዎች የጉምሩክ ህግን ጠብቀው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ እና ለማዳረስ ያስችላል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።
@Addis_Mereja