ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸውን ካማላ ሐሪስ አስመልክተው "የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል" ብለዋል።
"ከዚህ ቀን በኋላ አገራችን ታድጋለች፣ ትከበራለች፣ አሜሪካ ትቀድማለች" ብለዋል።
ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው በሚከናወንበት የካፒቶል ሂል አዳራሽ አካባቢ በደጋፊዎቻቸው ተሞልቷል። ከዜሮ በታች 5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቅዝቃዜ ቢኖርም የትራምፕን ንግግር ለመስማት ደጋፊዎቻቸው ተሰባስበዋል።
ከትራምፕ ደጋፊዎች አንዷ "የቤተሰብ ዋጋ የሚጠበቅባቸው" እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብላ እንደምትጠብቅ ተናግራለች። የቀድሞው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የትራምፕ ተፎካካሪ የነበሩት ምክትላቸው ካማላ ሀሪስ ወደ አዳራሹ ሲገቡ ጭብጨባ ተደርጎላቸዋል
ትራምፕ ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ ለአሜሪካ ያላቸውን የወደፊት ዕቅዶች ተናግረዋል።
"ሉዓላዊነታችንን መልሰን እናስከብራለን። ደኅንነታችን የተጠበቀ ይሆናል። የተዛባው ፍትሕ ይሰፍናል" ብለዋል።
"ዋና ግባችን ኩሩ አገር መገንባት ነው። ኩሩ፣ ነጻና የበለጸገች" ሲሉም አክለዋል።