"መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ"
አበው ሲተርቱ...
"መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ
አይባልም ደርሶ
የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ"
ብለው ይሉ ነበር፤
ዛሬ አላዩምና
መንገድ ባመጣው ጦስ እጅ እግሬ ሲሰበር፡፡
ለሃገሬ ማደግ...
ጤፍ ከጎጃም ጭኜ - ቡናውን ከጅማ
ውብ ሰንጋ ከሀረር - ሰሊጥ ከመተማ
ኮንቴነር ከሞጆ - ከአፋር አሞሌ ጨው
ስኳሩን ከወንጂ - ወርቁንም ከማይጨው
ውብ የ'ናት ተፈጥሮን - ለልጆቿ ላሳይ
ወዲህ እያመጣሁ - ወዲያ ያለን ሲሳይ
እንዳልዘከርኩላት - ላንዱ ያንዱን ፀጋ
ሀገር ከጠላችኝ - በኔ ላብ በልፅጋ
የምን መውጣት መውረድ
የምን መመላለስ?
እግሬን አላነሳም መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ፤
አዎ ዐይኑ ይፍሰስ!
ፈልቶበታልና የጎበዝ አለቃ፤
ጊዜው ካልታወቀ
ይሄ የኔ ስቃይ መቼ እንደሚያበቃ፤
አዎ ይጥፋ ይሙት
ይውደቅ ይንገዳገድ፤
ከሀገሬ ያወጣኝ ያሻገረኝ መንገድ፤
ካልተቆጠረልኝ ልፋት ውለታዬ
መገደል ከሆነ ደራሽ ወረታዬ
እጣዬ ከሆነ
በመንጋዎች መንደድ፤
ኧረ ለማን ብዬ ልናፍቀው ያን መንገድ፤
ቤቴም ካላስገባኝ በሰላም መልሶ፤
መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ ይታወር ጨርሶ፡፡
በገዛ ሃገሬ ላይ
ባይተዋር ከሆንኩኝ - ጉልበተኛ አምላኪ፤
የምን ሹፍርና
ቋጠሮ ልሸከም - ልሁን ተላላኪ፤
ነገሩም ካሰኘኝ
"ምናለ ባልነዳሁ"
መሪውን ስጨብጥ - ያኔ በፈነዳሁ፤
ቦዘኔ በሆንኩኝ
ብታይ እንደ አውደልዳይ፤
ሰርቼ መብላቴ - ካ'ረገኝ ተገዳይ፤
(ከዛሬ በኋላ)
አንት የሱዳን መንገድ
በል እርምህን አውጣ፤
ልጅህ ቀርቶብሀል በዛው እንደወጣ፤
የጅቡቲው መንገድ
ሰርክ የሚናፍቀኝ ምንይለኝ ያ ልብህ?
"ሰላም ግባ" እንዳልከኝ በዛው ስቀርብህ፤
ናልኝ ብትሉኝም ከማዶ ከወዲያ
ማን እግሩን ያነሳል? ደፍሮ ካሁን ወድያ?
አዎ ካሁን ወድያ...
ልጄም በ'ኔ ናፍቆት አትሙትብኝ በቃ፤
በሰው በርሃ አልሙት ጥለውኝ እንደ እቃ፤
ከትቢያም አይገኝ ታስሮ ሰውነቴ፤
ሄጄ እሷን ልቀፋት ናፍቃኛለች ሚስቴ፤
አዎ ካሁን ወዲያ...
ፍራጅ ሰው ላይገኝ ማንንም አልክሰስ፤
እግሬን አላነሳም መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ
እግሬን አላነሳም መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ፡፡
(በመላው ሃገሪቷ እየተሰቃዩ ላሉ ሹፌሮች መታሰቢያ ይሁንልኝ)
ሳሚ አንተነህ
24/03/17
አበው ሲተርቱ...
"መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ
አይባልም ደርሶ
የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ"
ብለው ይሉ ነበር፤
ዛሬ አላዩምና
መንገድ ባመጣው ጦስ እጅ እግሬ ሲሰበር፡፡
ለሃገሬ ማደግ...
ጤፍ ከጎጃም ጭኜ - ቡናውን ከጅማ
ውብ ሰንጋ ከሀረር - ሰሊጥ ከመተማ
ኮንቴነር ከሞጆ - ከአፋር አሞሌ ጨው
ስኳሩን ከወንጂ - ወርቁንም ከማይጨው
ውብ የ'ናት ተፈጥሮን - ለልጆቿ ላሳይ
ወዲህ እያመጣሁ - ወዲያ ያለን ሲሳይ
እንዳልዘከርኩላት - ላንዱ ያንዱን ፀጋ
ሀገር ከጠላችኝ - በኔ ላብ በልፅጋ
የምን መውጣት መውረድ
የምን መመላለስ?
እግሬን አላነሳም መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ፤
አዎ ዐይኑ ይፍሰስ!
ፈልቶበታልና የጎበዝ አለቃ፤
ጊዜው ካልታወቀ
ይሄ የኔ ስቃይ መቼ እንደሚያበቃ፤
አዎ ይጥፋ ይሙት
ይውደቅ ይንገዳገድ፤
ከሀገሬ ያወጣኝ ያሻገረኝ መንገድ፤
ካልተቆጠረልኝ ልፋት ውለታዬ
መገደል ከሆነ ደራሽ ወረታዬ
እጣዬ ከሆነ
በመንጋዎች መንደድ፤
ኧረ ለማን ብዬ ልናፍቀው ያን መንገድ፤
ቤቴም ካላስገባኝ በሰላም መልሶ፤
መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ ይታወር ጨርሶ፡፡
በገዛ ሃገሬ ላይ
ባይተዋር ከሆንኩኝ - ጉልበተኛ አምላኪ፤
የምን ሹፍርና
ቋጠሮ ልሸከም - ልሁን ተላላኪ፤
ነገሩም ካሰኘኝ
"ምናለ ባልነዳሁ"
መሪውን ስጨብጥ - ያኔ በፈነዳሁ፤
ቦዘኔ በሆንኩኝ
ብታይ እንደ አውደልዳይ፤
ሰርቼ መብላቴ - ካ'ረገኝ ተገዳይ፤
(ከዛሬ በኋላ)
አንት የሱዳን መንገድ
በል እርምህን አውጣ፤
ልጅህ ቀርቶብሀል በዛው እንደወጣ፤
የጅቡቲው መንገድ
ሰርክ የሚናፍቀኝ ምንይለኝ ያ ልብህ?
"ሰላም ግባ" እንዳልከኝ በዛው ስቀርብህ፤
ናልኝ ብትሉኝም ከማዶ ከወዲያ
ማን እግሩን ያነሳል? ደፍሮ ካሁን ወድያ?
አዎ ካሁን ወድያ...
ልጄም በ'ኔ ናፍቆት አትሙትብኝ በቃ፤
በሰው በርሃ አልሙት ጥለውኝ እንደ እቃ፤
ከትቢያም አይገኝ ታስሮ ሰውነቴ፤
ሄጄ እሷን ልቀፋት ናፍቃኛለች ሚስቴ፤
አዎ ካሁን ወዲያ...
ፍራጅ ሰው ላይገኝ ማንንም አልክሰስ፤
እግሬን አላነሳም መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ
እግሬን አላነሳም መንገድ ዐይኑ ይፍሰስ፡፡
(በመላው ሃገሪቷ እየተሰቃዩ ላሉ ሹፌሮች መታሰቢያ ይሁንልኝ)
ሳሚ አንተነህ
24/03/17