ይህ ግለሰብ እንደሚለው፤ ይህ ክስተት በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ኃይል የትግራይ ቴሌቪዥንና ድምጸ ወያኔ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ከእጁ ስለወጣ ኤፍ ኤም መቀለን በመሣሪያ ኃይል በመንጠቅ መጠቀሚያ ለማድረግ ያደረገው ሙከራ ነው።
ሌላ የድርጅቱ ሠራተኛ በበኩሉ፤ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃ "በዶክተር ረዳኢ የተሾምኩት ትክክለኛው የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ እኔ ነኝ፣ ሥልጣን አስረክበኝ" በሚል ነባር የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሀለፎም ንርአን እንደጠየቀ ተናግሯል።
"ሥልጣን አስረክበኝ አለው፣ አቶ ሀለፎም ደግሞ ሹመት የሰጠህ ዶ/ር ረዳኢ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕገወጥ የተባለ ሰው ስለሆነ ሥልጣን ላስረክብህ አልችልም። ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ ይዘህ ከመጣህ ግን ሥልጣን አስረክብሃለው አለው፤ በዚህን ጊዜ አቶ ዘመንፈስ ቅዱስ ማኅተብ ከፀሐፊዋ በኃይል አስገድዶ ወስዶ፣ ለጣቢያው ሠራተኞች የስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ ለጠፈ" ብሏል።
ይህን ተከትሎ አቶ ሐለፎም፤ "እኔ እያለሁ ለምን ማህተም ነጥቀህ ማስታወቂያ ትለጥፋለህ?” በማለት የተለጠፈውን ማስታወቂያ እንዳነሱትና በዚህም የተነሳ ውጥረት እንደተፈጠረ ተናግሯል።
ይህ ፍጥጫ ከጠዋቱ 3፡30 እስከ ቀትር 6፡00 ሰዓት የቆየ ሲሆን፣ በመጨረሻ ከቀዳማዊ ወያነ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ተጠርቶ ሁለቱንም ግለሰቦችና ጣቢያውን ለመቆጣጠር የመጡትን ታጣቂዎች ይዘዋቸው መሄዳቸውን የጣቢያው ሠራተኞች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰዓት መቀለ በሁለቱም ህወሓት ክንፎች የተሰየሙ ከንቲባዎች ቢኖሯትም ላለፉት ሦስት ወራት ያለ ከንቲባ ቆይታለች። ቢቢሲ የዛሬ ጠዋቱን ከስተት በተመለከተ ለጣቢያው ነባር ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃለፎም እንዲሁም ተሾሚያለሁ ለሚሉት አቶ ዘመንፈስቅዱስ ስልክ ደውሎ ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልሰመረም።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የመቀለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር አንድነት ነገሰ በበኩላቸው ጣቢያውን ለመቆጣጠር የተደረገውን ሙከራ አረጋግጠው ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።
ኤፍ ኤም መቀለ 104.4 ጣቢያ፤ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ሕግ መሠረት በትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ፈቃድ የሚንቀሳቀስ ሆኖ ከተመሠረተ 16 ዓመታት ያስቆጠረ የሬዲዮ ጣቢያ ነው።