✍ እድሜ ልኩ በክህደት ኖረ:
ሙቶም ጀናዛው አቃጠሉት: በአለም ዙሪያ ያሉ ሙወሒዶች በሌለበት ሰግደ ዱዐ አደረጉለት!!
ያ...ረሕማን ዕዝነትህ ምንኛየሰፋ ነው!!??
🖌️ በወርቅ ቀለም ሳይሆን በዐይን ደም መፃፍ ያለበት ሊታመን የሚከብድ አስገራሚ እና አስተማሪ የሆነ ገጠመኝ………
የገጠመኙ ባለቤት “ኻሊድ አል-ኪንዲ” ይባላል 🤲አላህ ይዘንለት🤲
ይህ ወንድም በገጠመው ህመም ምክንያት ወደ ህንድ ሀገር ለህክምና ይሄዳል። ህክምናውን ለማድረግ ሆስፒታል ገብቶ አልጋውን ይዞ ይተኛል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ነው ተኣምሩ የተከተሰው።
🖌️ ባለ ታሪኩ ኻሊድ አል_ኪንዲ ገጠመኙ እንዲህ ፅፎ አስቀምጦታል……
"ከዕለታት በአንዱ ቀን ሆስፒታል ውስጥ ተኝቼ ባለሁበት ዕንቅልፍ ሸለብ ያደርገኛል። በዕንቅልፍ ሰመመን ላይ ሆኜ ሳለሁ አጠገቤ የሚዟዟር ሰው ያለ ዐይነት ስሜት ተሰማኝ። አንገቴን ቀና አድርጌ ስመለከት: አጠገቤ ያስቀመጥኩት ስልክ የለም። ዐይኔን ሳዟዙር አንድ የሆስፒታሉ ሰርቨር የሆነ ህንዳዊ ወጣት ስልኬን ይዞ ተቀምጧል። ይህ ህንዳዊው "ቡድሂዝም" የሚባል የኩፍር ሐይማኖት ተከታይ ሲሆን በተወሰነ መልኩ ዐረብኛ መረዳት የሚችል ነበር።
ስልኬን እንዲመልስልኝ ብጠይቀውም አልሰማኝም። ተነስቼ ልቀበለው ስል ዐይኖቹ እንባ ቋጥረው በተመስጥኦ የሆነ ነገር እያዳመጠ ነው። ሲሰማው የነበረው ሸይኽ ሷቢር 🤲አላህ ይዘንለት🤲 ስለ ሞት ያደረገው ሙሓደራ ነበር። ወጣቱ ስልኬን መለሰልኝና ወጣ። ከዝያች ሰዓት ጀምሮ ክፍት በሚሆንበት ሰዓት ሁሉ ወደ እኔ እየመጣ "ያ አሰምተኸኝ የነበረው ዐይነት ነገር ክፈትልኝ" ይለኛል።
🎧 እኔም አንዳንድ የሰለፍዮች ሙሓደራዎች እና ቁርኣን እከፍትለታለሁ። ተመስጦ ያዳምጣቸውና "በጣም ደስ የሚል ነው" ይለኛል። እኔም 🤲አላህ ሆይ! ወደ እስልምና ምራው🤲 እያልኩ ዱዐ አረግለታለሁ። ስለም ልለው ግን እምቢ ይለኛል ብዬ ፈራሁኝ፤ ዱዐ ብቻ አደርግለታለሁ።
ህመሜ እየበረታብኝ እየሆነ መሆኑ ሲያይ
"የከፈትክልኝ መንገድ ሳታሳየኝ እንዳትሞት ፈራሁኝ" አለኝ። እኔም: “እንግዲያውስ አንተ ስለም፤ ለእኔ አትፍራ። እኔ ብሞት እንኳ በእስልምና ላይ ሆኜ ነው: አላህ በዕዝነቱ ጀነት ሊያስገባኝ ይችላል። አንተ ግን እስልምና ሳትቀበል ከሞትክ መጨረሻህ ማብቂያ የሌለው እሳት ነው የሚሆነው አልኩት።”
ጉልቤቴ ላይ ተደፍቶ "እሺ ምን ልበል?" አለኝ።
ሁለቱም ዐይኖቼ ዕንባ ማፍሰስ ጀመሩ። ማልቀሴን እንጂ ለምን እንደ ማለቅስ ሁላ አላቅም።
☝️ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ እመሰክራለሁ!! ብሎ እስልምና ተቀበለ።
ራሴን መቋቋም እስኪያቅተኝ ድረስ ተንሰቅስቄ አለቀስኩኝ"
ብሎ ወንድም ኻሊድ አል-ኪንዲ ገጠመኙን ፅፎታል።
በጣም አስገራሚው ታሪክ ቀጥሎ ያለው ነው………
የሞት ፅዋ የማትጎነጭ ነፍስ የለችምና ወንድም ኻሊድ ህንዳዊው ወጣት በሰለመበት ቅፅበት በጣም በመደሰቱ የልብ ህመሙን ይባባስበትና ሩሑ ከስጋው ትለያለች።
ህንዳዊው ወጣት በጣም ዐዘነ፤ ተከዘ። ገና ጨርሶ ያልተዋወቀው ጓደኛው፣ ከጨለማ ወደ ብርኀን ያመላከተው ወዳጁ በዐይኑ እያየው ዱንያን ተሰናብቶ ወጣ። 🤲አላህ ከደጋጎች ተርታ ያሳርፈው🤲
ቀጣዩን ታሪክ የሚነግረን ደግሞ ማዚን የሚባል ከኻሊድ ጋ የነበረ የቋንቋ አስተርጓሚ ነው።
"ወንድም ኻሊድ ከሞተ በኋላ ህንዳዊው ወንድማችን በጣም ዐዘነ። ዐይኖቹ እንባውን ማቆም አልቻሉም። ጀናዛውን ስናጥብ እና ስንከፍን ከእኛው ጋ ሆኖ አገዘን። በዚህ ጥልቅ በሆነ ሀዘን ላይ እንዳለ ለካስ የእሱ የዱንያ ኮንትራት ማብቂያ ደርሶ ነበርና ራሱን ስቶ ወደቀ። የወዳጁን ሩሕ ተከትላ የእሱም ሩሕ ከስጋው ተለየች። የወንድም ኻሊድ ጀናዛ ሳይቀበር ህንዳዊው ወጣትም ገና እስልምና ከተቀበለ ጥቂት ሰዓቶች እንደተቆጠሩ ዱንያ ተሰናብቶ ወደ አኼራ። አላሁ አክበር!! 🤲አላህ በሰፊ ዕዝነቱ ይቀበለው🤲
ህንዳዊው ወጣት ባልደረቦቹም ይሁን ቤተሰቦቹ የሚያውቁት በኖረበት የኩፍር እምነት ላይ ነውና ጀናዛውን በቡድሂዝም ሐይማኖት መሰረት በእሳት አቃጠሉት።"
ኢንሻ አላህ ይህ የመጨረሻው ቃጠሎው ይሆንለታል!!
ይህንን አስገራሚ ተኣምር የሆነ ታሪክ ከተሰማ በኋላ በዓለም ዙርያ ያሉ ብዙ ሱንዮች በህንዳዊው ወንድማችን ሰላት አል_ጋኢብ ሰግደውበታል!!
☝️አላህ
🤲ሁለቱም ወንድሞቻችን በጀነተል ፊርደውስ ይሰብስባቸው🤲
🤲ኣሚን!!🤲
ከገጠመኙ የምንማራቸው ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም; ትልቁ ትምህርት………
👌አንድ ሰው ቦታ እና ጊዜ ሳይገድበው ባገኘው አጋጣሚ እስልምናውን ማንፀባረቅ እና ወደ እስልምና መጣራት እንዳለበት ነው !!
🤲በእስልምና አኑሮ በእስልምና ይግደለን🤲
✍️ t.me/hamdquante
📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio