#የቤት_ኪራይ ውል ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ ተከራይ ቤቱን ለቆ እንዲያስረክበው ለቆ የማያስረክብ ከሆነ ግን የኪራይ ተመኑ በማስጠንቀቂያው ላይ በተመለከተው ተመን እንደሚሆን በመግለጽ አከራይ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶት ተከራዩ ቤቱን ለቆ ካላስረከበ ተከራይ በኪራይ በቤቱ መገልገሉን እንዲቀጥል አከራዩ አለመፍቀዱን በማያሻማ ሁኔታ የሚያሳይ ቢሆንም ተከራይ ሊከፍል የሚገባውን የኪራይ ተመን በተመለከተ ውሉ ላለመራዘሙ ዋናው ምክንያት የኪራይ ተመን አለመግባባት ከሆነና ተከራይ የኪራይ ተመን መጨመርን በግልጽ ከተቃወመ ሊከፍል የሚገባው በማስጠንቀቂያው ላይ በተገለጸው የኪራይ ተመን ሳይሆን በቀድሞው ተመን ነው።
በዚህ መዝገብ ተከራይ ቤቱን ለ4 ዓመታት ተከራይቶ የውሉ ዘመን ሲያልቅ ቤቱን ለቆ እንዲያስረክብ የማያስረክብ ከሆነ የኪራይ ተመኑ ብር 80,000 እንደሚሆን በመግለጽ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ሊከፍል የሚገባው በ 20,000 ነው በሚል በሰበር ችሎቱ ውሳኔ ተሰጥቷል።
ሰ/መ/ቁ. 220884 ቀን ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ/ም
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig