አለሕግAleHig ️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ሕጋዊ ውጤት ያስከትል ዘንድ ዉሉ በሕግ-አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውሉ ፈራሽ ከመሆኑም በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የሕግ መሠረት የለም::
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሰ.መ.ቁ 224476 የተወሰነ


ባለፉት 6 ወራት ብቻ 89 ዳኞች ስራ መልቀቃቸው ተሰማ::
‼️💎📊
👉🏽የደህንንት እና ፀጥታ ስጋት እንዲሁም የክፍያ ማነስ ለዳኞቹ ከስራ መልቀቅ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

👉🏽 “የዳኞች እስር ለፍትህ ስርዓቱ እንቅፋት ሆኗል”

#Ethiopia | ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይህን ያለው የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ሪፖርቱን ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።

የስድስት ወሩን የስራ ክንውን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የአማራ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አለምአንተ አግድው ናቸው፡፡

ፕሬዝደንቱ በክልሉ ያለው የሰላም እጦት ለፍትህ ስርዓቱ እንቅፋት መሆኑን በሪፖርታቸው አስረድተዋል፡፡

ይህም በእቅዳችን ለመከውን እንዳንችል አድረጎናል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት በክልሉ በየደረጃው ከሚገኙ 221 ፍርድቤቶች መካከል 28 የወረዳ ፍርድቤት ምድብ ችሎቶች አገልግሎት እየሰጡ አደሉም ተብሏል ፡፡

በዚህም ምክንያት የዜጎች ፍትህ የማግኝት መብት ላይ አሉታዊ ተጽኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል፡፡

በግጭቱ አንዳንድ ፍርድቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት የአማራ ክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አለምአንተ አግድው ከእነዚህ ፍርድ ቤቶችም ዳኞች አመራሮች እና የጉባዔው ተሿሚዎች ከስራ ውጭ ሆነዋል ብለዋል፡፡

በክልሉ ያለው የዳኞች እስራትም ለፍትህ ስርዓቱ እንቅፋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

ችግር ያለባቸውን ዳኞች በህገመንግስቱ በተቀመጠው ስርዓት መሰረት በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ለማየት ከዛም ያለፈ ሲሆን በመደበኛው ስርዓት ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን ብለዋል፡፡

ነገር ግን በአንዳንድ ክትትሎቻችን የተወሰኑ የዳኞች እስራት ከሰጠዋቸው ወሳኔዎች ጋር የሚገናኝ ሆኖ ስላገኘናቸው የተከበረው ምክርቤት ማስተካከያ እንዲደረግበት በአፅኖት እንዲታይልን እንፈልጋለን ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ምክር ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

በክልሉ 9ኝ ዳኞች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ መሆናቸውንም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ አሳሳ የዛሬ ወር መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

መሃበሩ ዳኞችን ከችሎት እያነሱ ማሰር ኢትዮጵያ ፈርማ ባጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ህጎችም ሆነ በህገመንግስቷ ሲታይ ተቀባይነት ስለሌለው ሊቆም ይገባል ሲል በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ከወራቶች በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለክልሉ ፕሬዝዳንት እና ለክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በፃፈው ደብዳቤ ችግሩ መኖሩን አረጋግጫለው ብሏል፡፡

ከድብዳቤው ላይ እንደተመለከትነው በፍርድ ቤት ስራ ላይ የአስፈፃሚው አካል ጣልቃ ገብነት መኖሩን ኢሰመኮ አረጋግጧል እንዲቆምም ጠይቋል፡፡
via sheger FM


አከራካሪ የነበረው የሙስና ወንጀል ክርክር ትርጉም ተሰጠው!!
~~
በሙስና ወንጀል ጊዜ የተገኘ ጥቅም ከፍተኛ ነው ብሎ ለመፈረጅ የቅጣት አወሳሰን ማንዋሉ ላይ ያለውን መሰረት በማድረግ ሳይሆን መወሰን ያለበት ጥቅሙ በተገኘበት በወቅ ገንዘቡ ያለውን የመግዝት አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

በዚህ የሰበር ውሳኔ መሰረት 203 ሺ ብር ከፍተኛ ጥቅም አይባልም ተብሏል።ቅጣት አወሳሰን ማንዋሉ ግን ከብር 100 ሺ በላይ ከፍተኛ ጥቅም ተብሎ እንዲወሰድ ያስቀምጥ ነበር።

ከብር 100ሺ በላይ ጥቅም ያገኘ ተከሳሽን ዐ.ህግ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ዋስትና በህግ ይከልከል በሚል ሲያሳስቡ እና ፍርድቤትም ሲቀበል ይታይ ነበር።


የአማራ ክልል ዳኞች ያለመከሰስ መብት በህግ ጥበቃ አገኘ!!
.................
ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የአራተኛ ቀን ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ በአራተኛተኛ ቀን ውሎው በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በኩል የቀረቡትን አምስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል። ካጸቃቸው ረቂቅ አዋጆች መካከል የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 281/2014 ለማሟላት የቀረበው አንዱ ነው። ይህ አዋጅ በማሟያነት ከያዛቸው ድንጋጌዎች አንዱ የክልሉ ዳኞች ያለመከሰስ መብት ይገኝበታል።

እንደሚታወቀው የክልሉ ዳኞች ያለመከሰስ መብት ከዚህ በፊት ለዚሁ ምክር ቤት ለሁለት ጊዜ ያህል ቀርቦ ተቀባይነት እንዳይኖረው የተደረገ መብት ነው። የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበርም የዳኞች እስራት እና ወከባ እንዲቆም፣ የክልሉ የዳኝነት ነጻነት በዘላቂነት እንዲከበር እና ከምንም በላይ ደግሞ የዳኞች ያለመከሰስ መብት በህግ ጥበቃ እንዲሰጠው የሚመለከታቸውን አካላት በተደጋጋሚ ሲጠይቅበት የነበረ ጉዳይ ነበር። ይህንን የማኅበሩን ጥያቄ መነሻ በማድረግም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን(ኢሰመኮ) ጨምሮ በርካታ አካላት ይህ መብት በህግ ጥበቃ እንዲያገኝ ለክልሉ መንግስት ሲያሳስቡበት የቆየም ጉዳይ ነው። እናም የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሔደው ጉባኤ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥቷል።

የዳኞች ያለመከሰስ መብት በህግ ጥበቃ ማግኘቱ በዳኞች ላይ የሚፈጸመውን እስር፣ እንግልት እና ወከባ በመጠኑም ቢሆን እንደሚቀንሰው እና ለክልሉ የዳኝነት ነጻነት መከበርም ዋስትና የሚሰጥ ስለመሆኑ ማኅበሩ ያምናል። ይህ መብት በህግ ከለላ እንዲሰጠው በርካታ አካላት ርብርብ ያደረጉ ሲሆን ይህንን ጥያቄ በባለቤትነት ተቀብሎ የህግ ማሟያ አዘጋጅቶ በርካታ አካላትን በሚገባ አስረድቶ ለምክር ቤት በማቅረብ ለውጤት ያበቃውን አዲሱን የጠቅላይ ፍ/ቤት አመራር ማኅበሩ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረበ የክልሉ ዳኞችንም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ይፈልጋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት ሹመታችሁ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ የጸደቀ 9 የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደብረ ማርቆስ ምድብ ችሎት፣ 46 የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች እና 171 የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ማኅበሩ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁም መልካም ምኞቱን ይገልጻል።








የሕግ ምክር ያስከፍላል !!!


ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ጠበቃ በአሜሪካ የተከሰሰውን ቻይናዊ ነፃ አወጡ፡፡ የስልሳ አምስት አመቱ ቻይናዊ ሊታንግ ሊያንግ በአሜሪካ ፌዴራል ፍርድ ቤት የተከሰሱት የቻይና ሰላይ ናቸው በሚል ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2023 የቀረበባቸው ይህ ክስ በቦስተን የሚገኙ የቻይና ኮሚኒቲ አባላትንና ቡድኖችን እንዲሁም የመንግስት ተቃዋሚዎችን የግል መረጃ ለቻይና ባለስልጣናት እየሰጡ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡ በክሱ ላይ የቻይና መንግስት በውጭ አገር የሚገኙ ተቺዎቹን ድምፅ ዝም ለማስባል በሚያደርገው እንቅስቃሴ እኚህ ቻይናዊ በድብቅ ለአገራቸው መንግስት እየሰለሉ መሆናቸው ተገልፆ ነበር፡፡

በቻይና የተወለዱትና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው እኚህ ቻይናዊ ክሱ እንደቀረበባቸው የተባለውን ድርጊት እንዳልፈፀሙ ገልፀው ታዋቂውን ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሙያ አቶ ደረጀ ደምሴን ጠበቃቸው አድርገው ሲሟገቱ ቆይተዋል፡፡ ጉዳዩ ትላንት በጁሪ ከታየ በኋላ ተከሳሹ ነፃ መሆናቸው ተገልፆላቸዋል፡፡

ይህ ውሳኔ ከተሰማ በኋላ የአሜሪካ መንግስት አቃቤ ህግ በመሆን ሲሟገቱ የቆዩት ሊህ ፎሊ ‹‹የጁሪውን ውሳኔ እናከብራለን፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ክሳችንን አቋርጠናል›› ብለዋል፡፡ የተከሳሹ ጠበቃ አቶ ደረጄ ደምሴ እንደገለፁት ይህ ክስ የቀረበባቸው ቻይናዊ በቦስተን የሚገኘው የአሜሪካዊ ቻይናዊያን ኮሚኒቲ አስተባባሪና አክቲቪስት ናቸው፡፡

ብዙውን ጊዜ የቻይናን አንድነት ማለትም የታይዋንን መጠቃለል የተመለከቱ አስተያየቶችን እንደሚሰጡ የጠቀሱት አቶ ደረጄ ይህ ሀሳብ ከቻይና መንግስት አቋም ጋር ስለሚመሳል ብቻ የቻይና ሰላይ ተብለው መከሰሳቸውን አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም ይህ ክስ የሰዎችን የመናገር ነፃነትን የሚገድብና ሌሎች ሰዎችን ለማስፈራራት ሲባል የቀረበ መሆኑን በመግለፅም ተከራክረዋል፡፡

ክርክሩን የተመለከቱት የጁሪ አባላትም የአቶ ደምሴን ሙግት ተቀብለው ተከሳሹ ላይ የቀረበው ክስ ውቅድ መሆን እንዳለበት ውሳኔ ካሳለፉ በኋላ ቻይናዊው ተከሳሽ ‹‹ትክክለኛ ፍትህ ዛሬ አግኝቻለሁ›› በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
(ዘ-ሐበሻ ዜና)
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ግዴታ ሆኗል‼️

በአካል ኢትዮጵያ ውስጥ የማይገኙ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደ ዩናይት ዶት ኢቲ ያሉ አማራጮችን ተጠቅመው ፋይዳን ሳይዙ የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ ተገልጿል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደ ቅደመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ብሔራዊ ባንክ አቅጣጫ ማስቀመጡን ያስታወሰው መረጃው ይህው አሰራርም በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን እንዲያካትት መደረጉን ነው የተናገረው።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የውጪ ሀገር ዜጎችንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያጠቃልል መሆኑ ጭምር የተገለፀ ሲሆን መመሪያው በብሔራዊ ባንክ መውጣቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ መሥሪያ ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
#ኢትዮ-መረጃ


የብድር ውል ይፍረስልኝ በሚል ከሚቀርብ ክስ ጋር በተያያዘ የተወሰነ አስተማሪ ጠቃሚ የሰበር ውሳኔ
በጋብቻ መካከል አንደኛው ተጋቢ የውል ግደታ ሲገባ በስምምነት ተሳታፊ ያልሆነ ተጋቢ ውል ይፍረስልኝ ክስ ሊያቀርብ በሚያስችል ልክ ስለውሉ መኖር የተሟላ እዉቀት ሊኖረው ስለሚገባ በአንደኘው ተጋቢ የተደረገ የብድር ውል መኖሩን ሌላኛው ተጋቢ አወቀ ሊባል የሚችለው ቢያንስ የገንዘብ ብድር ዉሉ ከማን ጋር እንደተደረገ፣ የምን ያህል ገንዘብ ብድር ውል እንደሆነ፣ መቼ የተደረገ ውል እንደሆነ ማወቅ ሲችል ነው፡፡በሌላ በኩል በፌደራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 68/መ እና 69/1 መሰረት የገንዘብ ብድር ውል ሲደረግ ያልተሳተፈ ተጋቢ እንድፈርስ በመጠየቅ ምክንያት ሊያደርግ የሚገባው እና ውሉ እንዲፈርስ ከመወሰኑ በፊት በፍሬ ነገር ደረጃ ሊረጋገጥ የሚገባው በገንዘብ ብድር ውል ግደታው በተዋናይነት አለመሳተፉ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ የብድር ውል ይፍረስልኝ በሚል ከሚቀርብ ክስ ጋር በተያያዘ በብድር ተገኘ የተባለው ገንዘብ ለትዳር ጥቅም ውሏል ወይስ አልዋለም በሚል ጭብጥ ላይ በማከራከርነወ ውሳኔ መስጠት አይቻልም፡፡ ይህ አይነት ክርክር ሊቀርብ የሚገባው የጋብቻ ፍች ተከትሎ በሚደረግ የባል እና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም ፍረድ ቤቶች የብድር ውል ይፍረስልኝ ተብሎ በቀረበ ክስ ክርክር ላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነው በብድር የተገኘው ገንዘብ ለትዳር ጥቅም ውሏል ወይስ አልዋለም የሚለውን ጭብጥ ላይ አከራክረው መወሰናቸው ሊታረም የሚገባው የክርክር አመራር ጉድለት ነው ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 26 በመ/ቁ 208197
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alehig.com @Alehig


230493 (2).pdf
881.9Кб
የተከራየ መኪና ተከራይ እጅ እያለ በሌላ ሰዉ ንብረት ላይ ጉዳት ካዳረሰ ለደረሰዉ ጉዳት ተጠያቂዉ ተከራይ ብቻ ነዉ።
ስ/መ/ቁ 230493


ከሳሽ ስለሚያሲይዘው የወጪና ኪሳራ ዋስትና ሰ/መ/ቁ. 218235
በፍርድ ቤት ክስ ያቀረበ ከሳሽ በክሱ ተረቺ ቢሆን ለተከሳሽ ወጪና ኪሳራ ለመክፈል ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል በሚል ዋስትና እንዲያስይዝ ሊጠየቅ አይገባም። 
የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 200(1) ለመክፈል አቅም ማጣትን አስመልክቶ የተደነገገ በመሆኑ ለመክፈል አቅሙ ካለ ፍ/ቤቱ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ፍርዱን የሚያስፈፅም በመሆኑ ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆን ከመነሻውም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 200(1) ዋስትና ለማስጠራት በቂ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰድ አይሆንም።
#daniel fikadu



Показано 14 последних публикаций.