አምባ መፅሐፍ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


🎯 አዲስ እና ጥንታዊ መጻሕፍት በአንድ ቦታ
📥 ሁሉም መጻሕፍት በPDF መልክ
📖 “ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም፤ ወደ ሙሉነት ያደርሳል እንጂ”
👉 Owner: @AmbaSupport
Buy ads ፡
https://telega.io/c/AmbaBooks
🔗 ቅርንጫፎቻችን፦
• @AMBA_PDF_BOOKS
• @AMBA_TREKA
• @YETMHRT_PDF
• @AMBAMUSIC1
🤝 ይቀላቀሉን፣ እውቀትን እናጋራ!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


📚 አእምሮን የሚያበለጽጉ ድንቅ መጻሕፍትን ይፈልጋሉ⁉️

​ታሪክን፣ ፍልስፍናን፣ የስነ-ልቦና ጥበብንና የቋንቋ እውቀትን በአንድ ቦታ ያግኙ❕


አባቴ በ Online እቁብ ተጀመረ ይላል አንተስ ምን ትጠብቃለህ

ከ 22 ተሳታፊዎች ብቻ

1️⃣ኛ እጣ 15 ሺ ብርርርርርር ✅


2️⃣ኛ እጣ 2000 ብርርርር ✅


3️⃣ኛ እጣ 1000 ብርርርር ✅


የእጣው ተሳታፊ ለመሆን
👇👇👇👇
https://t.me/+pa6LeH64C5syMWVk
https://t.me/+pa6LeH64C5syMWVk
https://t.me/+pa6LeH64C5syMWVk

እድል ተቀምጠህ ስለጠበክ አይመጣም ከላይ ባለው group join እያረጋችሁ እድላችሁን ምክሩ
🔥🔥🔥


ከደራሲ የማን አድናቂ ናችሁ ?


#አድስ_መፅሐፍ

"ሀገሬ ፅፈው የሚገልጿት ስለው የሚያሳይዋት ተናግረው የሚያስረዷት ሳትሆን አይተው የሚደነቁባት ድንቅ ተፈጥሮን የያዘች ምድራዊት ገነት ናት።'' ይላል ፶ አቃ አልዓዛር።

📚የመጽሐፍ ርዕስ ፦ ወንድምሽ ልሁን !
📝ደራሲ ፦ ገብሬ ባዬ ደረጀ

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1


#BOOK_NEWS

📔 ይሄንን ድንቅ እና 75 % በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈው #ወንድምሽ_ልሁን የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል !

⚫️በደራሲ ገብሬ ባዬ ደረጃ የተጻፈው መጽሐፍ ፤ በታሪኩ ውስጥ የ፶ አለቃ አልዓዛርን የውትርድርና ፣ የፍቅር ፣ የሕይወት ውጣ ውረድ እና የታማኝነት ፈተናዎችን ያሳያል ።

⚫️ከፓለቲካው ውጥረት እስከ ሀዋሳ ፣ ከአዳማ እስከ ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚዘልቀው ይህ አብሮ የሚያሳፍፍ ታሪክ ልብዎን ይማርካል ።

💡 የመጽሃፉ ዋና ዋና ጭብጦች ፦

🔷የፍቅር እና የእምነት ፈተና ፦ በታሪኩ ውስጥ የሚታየው ልብ የሚነካ የፍቅር እና የሕይወት ጉዞ

🔷ፅናት እና እልህ ፦ በችግር እና በውጣ ውረድ ውሰጥ አልፎ የስኬት ማማ ላይ ለመድረስ ላይ የሚደረግ ተጋድሎ

🔷የህይወት እውነታዎች ፦ እውነት ፣ ታማኝነት እና ሰብአዊነትን የሚመረምረው ድንቅ ሀሳቦች

እመኑኝ ፤ ገዝታችሁ አንብቡት - ታመሰግኑኛላችሁ !

📚የመጽሐፍ ርዕስ ፦ ወንድምሽ ልሁን !
📝ደራሲ ፦ ገብሬ ባዬ ደረጀ

መጽሐፉን አሁኑኑ ለመግዛት እና ለማንበብ እንዲሁም
በብዛት ለምትፈልጉ በዚህ
ስልክ ይዘዙ።😀 +251982686364

ለተጨማሪ ሀሳብ እና ጥያቄ
➡️@AshuVibes

በአዲስአበባ እንዲሁም በክልል ከተሞች እና ክፍለሀገራት በነጻ deliver እናደርጋለን


✨✨ፍቅር ቅብ-20✨✨





ለቅፅበት ሀኒን ከአእምሮዬ የሚያስወጣልኝ ባገኝ ሳልደፋ 'እሺ' እንደምለው አውቃለሁ....

እጄ ላይ ያለውን ሹካ አስለቀቀና በሹካው ቦታ እጁ ተገኘ....የእጁን ልስላሴ ነግሬያችኃለሁ አይደል....እሱ ብቻ የሚሰጠኝ ምቾት ይሰማኝ ጀመር.....እጄ ከርዳዳ ስለሆነ ነው መሰለኝ የእጁ ልስላሴ ልቆ ይሰማኛል....

እጄ መከርደድ የጀመረው እናቴ እግሯ ከቤት ከወጣ ማግስት ከአባቴ ሻካራ ጃኬቶች ጋር መታገል ስጀምር ነው....የእናቴ እጅም ከርዳዳ ነበር.....ማታ ማታ ቀኝ እጄን ይዛ ትፀልይ ነበር....ምን እንደምትል ባላውቅም በጣም በቀስታ ታነበንብ ነበር.....እሷ ከሄደች በኃላ እኔም በከርዳዳ እጆቼ የታናሽ እህቴን ቀኝ እጅ ጨብጬ ሳነበንብ ራሴን አገኘሁት.....ያኔ ነው እናቴ ምን ብላ ትፀልይ እንደነበር ለመገመት የበቃሁት.....

ከከረደደ እጅ ጀርባ የከረደደ ትናንት የገገረ ልብ አለ.....ውሀ ቀጠነ ብሎ ባር ባር ከሚለው ሰው ጀርባ ሙሾ የሚያስወርድ ትናንት አለ.....በቀላሉ ማጅራቱ የሚጎብጥ ሰው ጀርባ ማጅራት ገትር የሚያሲዝ ትናንት ያልታወቀለት ቁስል አለ።

ሁላችንም የምንፈርደው የደረስንበት ላይ አይደል....የሌላውን ሸክም እንዳናቀል እኛም ሸክም የከበደን ነን....

የእጄ መጠጠር የጎረበጠው አይመስልም.....ተጠጋኝ.....ይሄ ዮናስ የሚጠጋኝ አይነት መጠጋት....'ዮናስ መክሮት ነው እንዴ' የሚያስብል አይነት መጠጋት.....እጁን ግን ወደሌላ ቦታ አልሰደደም.....ደስ አለኝ.....እጁን እንቁዬ ላይ ሳይጭን ልቤን ቀጥ ያደረጋት የመጀመሪያ ሰው.....መክብብ.....አይኔ ላይ በመቆየት ብቻ ላብ በላብ ያደረገኝ የመጀመሪያው ሰው.....መክብብ....."እወድሀለሁ.....በጣም እወድሀለሁ" አልኩት አይኑን ከአይኔ ሳይነቅል.....አስተያየቱን ፈራሁት.....ከማላብ አልፌ ማቃሰት ሳልጀምር እንኳን እንደምወደው ነገርኩት .....ያን ምትሀት ጥርሱን ገለጥ አረገው.....በጥርሱ ብቻ ብዙ ብዙ ማለት ይችላል.....በአይኑ ብቻ ስሜትን መበርበር ይችላል.....

ከቅድሙ ይበልጥ ተጠግቶኝ አይኖቼን ሳመ.....ወደ አይኖቼ ሲጠጋ ሊስመኝ እንደሆነ ገባኝና አይኖቼን ገርበብ አደረግኩለት....አይኖቼን ወደቦታቸው ሳልመልስ ከንፈሮቼን አንድ በአንድ ሳመ....

ልክ እንደጉንጭ ቀለል አድርጎ ነበር የሳመኝ....ከንፈር በክፍልፋይ እንደሚሳም ባላውቅም ዮናስ ጋር የሌለ የጨዋ አሳሳም ይሆናል ብዬ አለፍኩት....እሳት እንደነካ ሰው ከከንፈሮቼ በፍጥነት ሲላቀቅ ከንፈሮቼ እኔ የማላውቀው አንዳች መለኮታዊ ሀይል ይኖራቸው ይሆናል ብዬ ተውኩት....ከንፈሮቼ ላይ ባይቆይም አይኔ ላይ የቆየው መቆየት በልጦብኝ ልብ ላለማለት ወሰንኩ.....መሳም አቅቶት ሳይሆን ጊዜው ስላልመሰለው አላረዘመው ይሆናል ብዬ ዝም አልኩ.....የሚጠጣ ክትፎ አፍንጫዬ ላይ አስጠግቶ እንደነጠቀኝ አይነት ስሜት ቢሰማኝም መክብብ ስለሆነ ብቻ ዝም ጭጭ ረጭ አልኹ....

'የእራት ግብዣ መዝጊያ እራት መብላት ብቻ መሆን አለበት' ትለኝ ነበር ሀኒ በእራት ሰበብ ቁርስ አብልቶ ከሚሸኘኝ ዮናስ ስመለስ.....'እራት ላብላሽ ካለ መብላት የሚፈልገው ነገር አለ' ትለኝም ነበር...... ከምሽቱ ሶስት ሰአት ሲሆን መክብብ ሰአቱን አየት አረገና "ብንሄድ ይሻላል.....እየመሸ ነው....ቤተሰቦችሽም ይጨነቁ ይሆናል" አለኝና አስተናጋጁን ጠርቶ ሂሳብ አስተመነ.......

መኪናው ውስጥ ገባን....አልፎ አልፎ እያየኝ ያን ምትሀት ገለጥ ያደርግልኛል.....ለሀገር የሚበቃ ጥርስ ይዞ እዚ ምንድን ነው ሚሰራው እላለሁ....ግብፅ ስትተብትብን ምናል የመክብብን ጥርስ ይዘውት የግብፅ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ቢሄዱና ቢያደነዝዟቸው.... የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምን ነካው.....የዚን ጥርስ ባለቤት ግብ ጠባቂ ቢያደርጉት ምን አለ....አንዴ ፈገግ ካለ እንኳን ተቃራኒ ቡድን ይቅርና ሊገባ የሚንደረደረው ኳስ እግር አውጥቶ ወደኃላ ያፈገፍግ ነበር....አለማወቅ።

ቤቴ እንደደረስኩኝ ግንባሬን ሳመኝና ከመኪናው ወረድኩ.....ጊቢያችንን ማንኳኳት ስጀምር ሞተሩን አስነሳ.....መኪናው ከአይኔ ሲሰወር  ሀኒ ጭንቅላቴ ላይ ተንሰራፋች።

ቤት ስገባ እህቴ እያጠናች አባቴ ደግሞ ዜና ከሚዘግበው ጋዜጠኛ ፊት ለፊት ተቀምጦ እያንቀላፋ ነበር....

እራት በልተናል ቢሉም  'እድል ስፔሻል' የሚባለውን ምግቤን ሰርቼ ካልበላችሁ ብዬ አስጨነቅኳቸው.....በሉልኝ....."ዛሬ ጫን ያለው ነው ባክሽ....ምን ተገኘ" አለኝ አባቴ....."ደስ ብሎኝ ነው እንዲሁ.....እስቲ መርቀኝ.....".....አልኩትና ጉልበቱ ላይ ተደፋሁ.....

"እድሜ ይስጥሽ....ጤናሽን አይንሳሽ....ልብሽን ይጠብቅልሽ....እመቤቴ በፈረሰው ጎንሽ ትቁም.....".....አለኝና አይኑ ውስጥ የተጠራቀመውን እንባ በጋቢው አደራረቀ....."የፈረሰው ጎንሽ" ያለው ጋር እስኪደርስ ደህና ነበርኩ.....ካጎነበስኩበት ተነስቼ አቀፍኩት....ሳቅፈው ባሰበት....እሱም የሚመርቀው አጥቶ እንጂ የፈረሰበት ጎን እንዳለው ትዝ አለኝ....

እንደ እኔ እንደ እኔ ህይወት ሰፊ ካሬ ያላት መሬት ናት....የፈረሰ ጎናችንን ተወት አርገን ሌላ ማንነት ለመገንባት የሚያስችል ትርፍ ቦታ አላት.....የፈረሰው እስኪጠገን መጠበቅ ሞኝነት ነው.....እሱን የሚጠግነው ጊዜ የተባለ መሀንዲስ ነው.....ሌላው ካሬ ግን የእኛ ሀላፊነት ነው።

"ከትዳር ጋር የተያያዘ ምርቃት የለህም አባዬ.....".....አልኩት ከእቅፉ ሳልወጣ....አንድም ለመመረቅ ደግሞም መላቀሳችንን ረዝሞ ለእህቴ ጥያቄዎች አሳልፌ እንዳልሰጥ......

ከት ብሎ ሳቀና "ኧረ ሞልቶ".....አለና አዥጎደጎደው....ጉልበቱን ስሜ ተነሳሁ.....ቡና ካላፈላሁ ሞቼ እገኛለሁ ስለው 5 ሰአት እያለፈ ነበር......

"ውቃቢ እንዳለበት ሰው በጠራራ ለሊት....?".....አለ ከላዩ የወደቀውን የጋቢ ክፍል ወደቦታው እየመለሰ....

"መች ስድስት ሰአት ሆነ አባዬ ደሞ" ብዬ እንደማኩረፍ ስል እንዳፈላ ተፈቀደልኝ.....

"ፊትሽ ሁላ ፈካ....የሰጠሽን የሰጠሽ አምላክ ይመስገን.....".....አለኝ አቦል ቡናውን እየተጎነጨ።

*
አተኛኘቴ የሬሳ ነበር.....የእህቴ አቀሳቀስ ደግሞ ሬሳ የሚያስሮጥ ነበር....

የተጣጠፈ ወረቀት በእጄ ሰጠችኝ እና እያለከለከች ማውራት ጀመረች......"እድል የሆነች ተለቅ ያለች ሴትዮ ናት ለእህትሽ ስጫት ብላ የሰጠችኝ....ነጠላ ለብሳ ነበር....አጠር ያለች.....".....እንዳለችኝ ከአልጋዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ.....አባታችን ቤት አልነበረም.....እጇን እየጎተትኩ ይዣት ወጣሁ....."በየት በኩል ነው የሄደችው ታስታውሻለሽ....እእእ" አልኳት በተጣደፈ ሰው ድምፅ....."ሰጥታኝ ታጠፈች....".....ባለችኝ መንገድ ታጠፍኩና ከአራት መንታ መንገድ ጋር ተፋጠጥኩ.....አንቺ በዚኛው ሂጂ እኔ ደግሞ በዚህ ብዬ ከአራት መንታው ሁለቱን መንገድ መረጥኩ.....በህይወቴ እንደዚህ የሮጥኩበትን ቀን አላስታውስም.....ልቤ ልትፈነዳ አንድ ሀሙስ እስኪቀራት ድረስ ሮጥኩ.....ከእንባ ጋር ሮጥኩ....ከትናንቴ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዤ ሮጥኩ.....

አላገኘኃትም።


"ምንም አይነት ነገር ቢመጣ ከዚህ የሚከብድ አይመስለኝም....ከዛን ቀን በላይ ከባድ ምሽት የሚኖረኝ አይመስለኝም...እጃችሁን ይዤ እያለቀስኩኝ ነበር...በተኛችሁበት ይቅርታ እየጠየቅኳችሁ ነበር....በብርሀን አይናችሁን እያየሁ ማድረግ አልቻልኩም...."ጥያቹ ልሄድ ነው" ለሚል መርዶ የሚሆን ይቅርታ ይኖራል...?....."ካሁን በኃላ አይኔን ስለማታዩት ይቅር በሉኝ..."....ይባላል...?

ለረጅም ሰአት እያየኃችሁ ነበር ....ስትተኙ ደግሞ ይበልጥ ታሳሱ ነበር.....እንቅልፋችሁ ላይ እምነት ነበረ....ስትነቁ ሁሉም ነገር እንደሚቀጥል የሚነግራችሁ እምነት....

"ለምን እውነቱን አልነገርኳቸውም...?"....የምልበት ቀን አበዛዙን አታውቂም እድሏ.....የሆንኩትን አታውቂም እድሏ....ስንት ቀን እግሬን አንስቼ እንደመለስኩት አታውቂም ልጄ.....አንዴ አቅፌያችሁ ለመመለስ የፀለይኩትን ፀሎት አታውቂም ልጄ....ለልደታችሁ ሻማ እንደማበራ....ፎቶአችሁን በትልቁ እንደሰቀልኩ... የብቻ ቤቴ አድባር እናንተ እንደሆናችሁ አታውቂም የኔ ልጅ....

ከአመታት በኃላ ተመልሼ ልመጣ ሻንጣዬን ሸክፌ ነበር....እንዳትጎዱብኝ ብዬ ተውኩት እንጂ......ይቅር በሉኝ ልጆቼ....ይቅር በሉኝ....አልመጣም አትጠብቁኝ....እወዳችኃለሁ።".....ብሎ የሚዘጋ ደብዳቤ አንብቤ ለእህቴ ሰጠኃት....ስለ እናቷ የማወቅ መብቷን ከዚህ በላይ ልጋፋ አልፈለግኩም.....

'መምጣቴ ይጎዳችኃል' ነው ያለችው አይደል....! ...አሁን ማን ይሙት ለዘመናት ከእናት መለየት ቆዳ ተልጦ ጨው እንደተነሰነሰበት ሰውነት እንደሚለበልብ ጠፍቷት ነው....?...እንደዚህ ይደረጋል....?....አልመጣም ለማለት ይሄ ሁሉ ጊዜ ይጠበቃል.....

**
እውነቱ ግን ራስ ወዳድ መሆኗ ላይ ነው...የልጆቿን እምባ እና ድንጋጤ በአይኗ ማየት የሚፈጥርባትን ከባድ ስሜት ለማምለጥ ነው...ሁላችንም እንዲህ አይደል የምናደርገው....እኛ ሳናይ ስለሚወርዱት ዘላዎች ማሰብ አንፈልግም....ብቻ ማምለጥ....ብቻ መፈርጠጥ...

ብናምንም ባናምንም ሁላችንም ስለሚጎዳው ስሜታችን ስናስብ እንደደነበረ በሬ የሚያስፈረጥጥ ራስ ወዳድነት አለብን...

✍ሸዊት

ቀጣይ የመጨረሻው ክፍል ✨

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1




ደማቆቹ.pdf
15.7Мб
📚ደማቆቹ 📚

📝ደራሲ :-ሌሊሳ ግርማ
📜ዘውግ:- biographies
📖የገፅ ብዛት ፦ 343
🗓 ዓ.ም :- 172
⬇️size :- 15. 7MB
🖨አታሚ :--_-_-
🪝Type :-
#pdf #biographies
🔔 ቻናል :- @AmbaBooks|📚

⚫️" ደማቆቹ " የተሰኘው የሌሊሳ ግርማ መጽሐፍ ::  

✅ ይህ " ደማቆቹ  " የተሰኘው መጽሐፉ  ይዘቱ አጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ሆኖ የትርጉም ሥራ ነው ::  በመጽሐፉ ውስጥ ድርሰቶቻቸው ለትርጉም የበቁላቸው አስራ አራት የዓለማችን ምርጥ ደራሲያን ናቸው ::

✅ ሶመርሴት ሞም
✅ ሼርውድ አንደርሰን
✅ ፍራንክ አር አስቶክሰን
✅ ሳኪ
✅ ናጂብ ማህፉዝ
✅ አንቷን ቼኮቭ
✅አየ ራንድ
✅ፍራንክ ካፍካ
✅ኧርነስት ሄሚንግዌይ
✅ ገብርኤል ጋርሻ ማርኩዌዝ
✅ ማርጋሬት አትውድ
✅ዊሊያም ሳሮያን
✅ ሲ . ቢ ጊልፎርድ
✅ሮበርት ሻራክ

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1


📚ደማቆቹ 📚

📝ደራሲ :-የሌሊሳ ግርማ
📜ዘውግ:- biographies
📖የገፅ ብዛት ፦ 343
🗓 ዓ.ም :- 172
⬇️size :- 15. 7MB
🖨አታሚ :--_-_-
🪝Type :-
#pdf #biographies
🔔 ቻናል :- @AmbaBooks|📚

✅በዓለም የታወቁ የአጫጭር ልብወለድ ስብስብ

✅"መንፈስና ሥጋ" ከሚለው ክፍል የተቀነጨበ

✅የኬትት አስዊፍት የመስኮት መጋረጃ ሲገለጥ በሰበረው ቀዳዳ አሻግሮ ማየት ቻለ፡፡ ግን እሷን አልጋዋ ላይ አልነበረችም። እሷም ለመንጎራደድ ወደ ጎዳናው ወጥታለች ማለት ነው። መጋረጃውን የገለጠችው ወይዘሮ ኤሊዛቤት እስዊፍት ነበረች።

✅አገልጋዩ  በመስኮት ከሚያስጮልቀው የሥጋ ፈተናው ለዛች ቅፅበት ስላመለጠ በደስታ ሊያለቅስ ምንም አልቀረውም። ወደ ራሱ ቤት አምላኩን እያመሰገነ በዛ የተረገመ ቅጽበት በመስታወቱ ላይ የተሰበረውን የመስኮቱን ቀዳዳ መድፈን ዘነጋ።

✅የተሰበረው የመስኮቱ ሸራፊ ጠርዝ ላይ ነው፤ የልጁ ምስል በባዶ ተረከዙ ከቆመበት ትንሽ ዝቅ ብሎ። ልጁ ያለ እንቅስቃሴ ግስጥ ብሎ የክርስቶስን ፊት ተመጦ እያየ ቆሞ ባለበት።

✅ክርቲስ ሀርትማን በዛ የእሑድ ማለዳ ስለ ስብከቱ ከናካቴው ረሳው። ለተሰበሰቡት ምዕመናን ተናገራቸው። በንግግሩ፣ ሰዎች ስለ ፓስተራቸው ተፈጥሮ እንክን አልባ መሆን እና የተለየ ሰው አድርገው ማሰባቸው ትከክል አለመሆኑን ገለጸላቸው።

✅"ከራሴው ተሞከሮ በመነሣት. እኛ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋዮችም እናንተ በምትፈነበት ኃጢአት የምንፈተን ነን" ብሎ ተናገራቸው። “በኃጢአት ተፈትኜ ወድቄ አውቃለሁ። የእግዚአብሄር እጅ ከእኔ እራስ በላይ ሆኖ ነው ከውድቀቴ ያነሣኝ። እኔን እንዳነሣኝ እናንተንም ደግሞ ያነሣችኋል። ተስፋ እትቁረጡ በኃጢአት በወደቃችሁ ጊዜ ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ... እናም ደጋግማችሁ እና ደጋግማችሁ ትድናላችሁ"

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅


📔ስንቶቻችሁ ይህንን መፅሐፍ አንብባችሁታል❓

አንብቤዋለሁ ❤️ ፣ አላነበብኩትም 🤝 ፣ ጀምሬው ነበር
👍


✅.«ሕይወት ጠመዝማዛ የአቀበት መንገድ ነው፡፡ ያለፉበትን ድንግዝግዝ አቀበቶች አቅርቅሮ ለማየት ከመሞከር ይልቅ፣ ጉዞው ሽቅብ እንደ መሆኑ፣ ቀጣዮቹን ተመሳሳይ መሰል አቀበቶች ገና ከወዲሁ ለመገንዘብ አንጋጦ መቃኘት ይሻላል።››

Speak 💬፦ አንድሬ ጊዴ

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅


✨✨ፍቅር ቅብ-19✨✨




"ሰርፕራይዙን አበላሸሁት አይደል......".....አለቺኝ ስልኩን ከዘጋች በኃላ......

ግራ ገባኝ.....እሱን አግኝቼ እሷን ላጣት ነው....?...አንዱን አጥቶ ሌላ ማግኘት ህይወት ሊባል ይችላል....?.....ብሎልኝ ልቤን የሞላው ሰው ባሌ ከሆነ የሰርጌ እለት በግራ ባሌን አድርጌ በቀኝ የማደርጋት ስር ሚዜዬ ሀኒ ላትሆን ነው......?.....አጥንት የሚሰረስር ህመም ውስጥ ሆና ታጅበኝ ይሆን.....በሙሉ ልቧ "ይዟት በረረ....".....እያለች ትሸኘኝ ይሆን.....

ምን አለ እንዲህ ባታደርግ.....ምን አለ እንደመጀመሪያው ቀኗ ብትሆን.....ምን አለ ዛሬም እንደትናንቱ እንድታዘባት ብታደርግ.....በ"እድለኛ" ነሽ ፈንታ "መሰሪ ነሽ" ብትለኝ.....ምናል እንዲህ ባታደርግ.....አንገቷን ሰበር አድርጋ ባታለቅስ ምን አለበት.....ምናል እምባዋ እልህ ቢኖረው....ምናል አንድ ሁለት ስድብ ብትሰድበኝ...."ማን ስለሆንሽ ነው" ብትለኝስ.....

"አደራሽን ደግሞ እንዳላወቀ ሁኚ....ብዙም አትዘንጪ.....".....አለችኝ ስንሰነባበት.....ሳቅ ነገር ብትልልኝም ለፈገግታዋ መልስ አልሰጠሁም......ጭንቅላቴ ተወጥሯል....እያሰብኩ ነው.....ይሄ ነው የማልለው ከባድ ስሜት እየተጫወተብኝ ነው.....

"ስለ ባሌ የማወራው ለሀኒ እና ለንሰሀ አባቴ ብቻ ነው" የሚል መንግስት ያላፀደቀልኝ ህግ ነበረኝ....አሁን ስለመክብብ ምንድነው የምነግራት....ሌላው ቀርቶ የዛሬውን ቀን አብረን መፈንደቅ አልነበረብንም....ግማሽ ሳቅ ግማሽ ሳግ ይዤ ነው የፍቅር ጥያቄውን የምቀበለው....?

መታደልም አለመታደልም ነው ይሄ..... ዱባ እና ክትፎ ቀላቅሎ እንደመብላት ያለ ነው ይሄ....የፆም ቋንጣ እንደመስቀል ነው ይሄ.....ባንድ እግር ቤተስኪያን ቆሞ እንደማስቀደስ ባንዱ ደግሞ መሸታ ቤት ቡጊ ቡጊ እንደመጨፈር ግራ የገባው ነገር ነው.....በአንድ አይን የደስታ እምባ ባንዱ ደግሞ ዋይታ ነው ይሄ....

እሺም እምቢም ብለው ደስታ አለው....የቱ ደስታ ይበልጣል....?

***
አመሻሽ ላይ ስልኬ ጠራ.......መክብብ።

"ሄለው እድሏ......"......አለኝ ፍቅር ባለበት ድምፅ....... እድሏ ብሎኝ አያውቅም.....እድሏ  የምትለኝ እናቴ ብቻ ነበረች።

"አ....አቤት.....".....እንደእስከዛሬው ወዬ ማለት ሀኒን መክዳት መሰለኝ....

"የት ነሽ...."......አለኝ ወዬ አለማለቴን ከቁብ ሳይቆጥር......

"ቤት" አልኩት....ቤቴ ነበርኩ.....በቴሌቭጅን መስኮት ላይ በማያቸው በሚስቁ ሴቶች እየተደመምኩ....ይስቃሉ.....በጣም ይስቃሉ.....ይዝናናሉ.....ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ውስጥ ገብተው እንደ ንግስት ይስተናገዳሉ....'ለአንድ ቀን ኖሬው ብሞትም አይቆጨኝ' የሚያስብል ኑሮ ለአንድ ቀን ይኖራሉ።

"እራት እንብላ"....አለኝ....ድምፁ ላይ መሳቀቅ ነበር......እንዳልገባው ሆኜ "ብሉ" ልለው ነበር.....ውስጤን ደስ አላለውም.... እሱ ያጠፋው አንድም ጥፋት አለመኖሩን ለማሰብ ሞከርኩ.....ስመኘው የነበረው ነገር እንደነበር አስታወስኩ.....ሰውየው መክብብ እንደሆነ አስታወስኩ...."መክብብ የወራት ክስተት ነው.....ሀኒ ግን የዘመናት......".....አለኝ ስሙን የማላውቀው የጭንቅላቴ ክፍል.....

በደስታዬ መደሰት አለመቻሌ አብከነከነኝ.....

"እና ምን አልሽኝ.....".....ጥያቄውን አስታወሰኝ።

"እሺ".....አልኩትና ወደሚያናውዘኝ ጭንቅላቴ ተመለስኩ።

***

"ወድጄሻለሁ...."......አለኝና ኮፍያውን አውልቆ በራው ላይ ችፍ ያለውን ላብ በሶፍት አደራረቀ.....ፊት ለፊታችን ያስቀመጥነውን ምግብ ቆልለን.....ብዙ ዝባዝባዝንኬ እንደማልወድ የነገረችው ሀኒ መሆን አለባት....መግቢያም መንደርደሪያም የሌለው እንቅጭ ነው የነገረኝ....

የእጁን ርግብግቢት ያስተዋልኩት በእጁ የያዘው ሹካ አየር ላይ ሲውለበለብ ነበር....

"እድል" አለኝ ዝምታዬ ሲረዝምበት.....

"ወዬ".....አልኩትና አይኑ እንዳያገኘኝ ሳህኔ ላይ አፈጠጥኩ....

"ወድጄሻለሁ.....በጣም ወድጄሻለሁ....'ምን ታስቢያለሽ' ብዬ አልጠይቅሽም....ምንም ብታስቢ....ምንም ብትዪኝ እኔ ጋር የሚለወጥ ስሜት የለም....ድንገት እንደሆነብሽ እና እንዳስደነገጠሽ ይገባኛል....ምን አልባት ይሄን ለማለትም ፈጥኜ ይሆናል....ግን እድሏ ልቤ አላስቀምጥ አለኝ....መጀመሪያ ላይ እንዲሁ obsession መስሎኝ ነበር....ጭራሽ ጊዜ ሳይመርጥ ቀን እና ማታውን የማስበው ስላንቺ ሆኖ ሲያርፍ ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ....

ከልክ በላይ አሰብኩሽ....አንድ ሁለት ቀን ስለመስሪያ ቤት ሴቶች ለማሰብና አይኔ ላይ የምትጠገኚብኝን ነገር ለማደብዘዝ ሞከርኩ.....በውኔም በህልሜም በዚህ መንገድ አስቤያት ስለማላውቀው ሀኒ እራሱ ሳስብ ነበር.....ከማንም ላወዳድርሽ አልቻልኩም....አንቺን የማወቅ....አንቺን የመቅረብ ምኞቴ ከቀን ወደ ቀን እየጋለ ሄደ....".....አለኝና ፊት ለፊቱ ከተቀመጠው ውሀ አንድ ጉንጭ ጠጣለት።

"አይኔን የሳምከኝ እለት የሆንኩትን መሆን አስታውሳለሁ.... እረፍትም ፍርሀትም....ሳቅም ደስታም....ለቅፅበት የመኖር ፍላጎቴ ሲንር ይታወቀኝ ነበር....ላውቅህ እፈልጋለሁ.....በደንብ ላውቅህ....ሁልጊዜ እንባ ያቦዘዛቸውን አይኖቼን እንድትስም እፈልጋለሁ.....ባንተ መታቀፍ አለም ነው.....ስታዳምጠኝ ልብህን እስከ ጥግ ከፍተህ ነው....አንተን አለመውደድ አይቻልም"......ያለው ልቤ ነው......

ጎንበስ ብዬ ሳህኔ ላይ ያለችውን የሞተች ዶሮ ሬሳዋን በሹካ እየወጋሁ አላስተኛ እያልኳት ነው.....ላቤ ጀርባዬ ላይ ይንቆረቆራል....እንደ እሱ በራ ብሆን አናቴ ላይ ያለው ላብ ጎርፍ ሆኖ ይወስደው እና እኔም ከዚ አጣብቂኝ እገላገል ነበር......

"እድሏ......".....ጠራኝና 'መልስሽን እየጠበቅኩ' ነው አስተያየት አየኝ።

አላለቀም.....

✍️ሸዊት

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅




📔አደፍርስ የአማርኛ ስነ - ፅሁፍ ማስተርፒስ ተደርገው ከሚወሰዱ መፅሀፍት አንዱ ሲሆን የአማርኛ ቋንቋን ጉልበት ያሳየ ታላቅ ስራ ነው

✅አንዳንድ አንባቢዎች "አደፍርስ" ሴራ የለውም ብለው ይከራከራሉ። በእርግጥ አደፍርስ ለየት ያለ ልብወለድ ነው። በእንግሊዝኛ experimental ብለን እንደምንጠራቸው ያለ ነው። አቀራረቡ እንደ ተውኔት ሆኖ የገፀባህሪያቱ ምልልስ ቃለ―ተውኔት ይመስላል። ዳኛቸው ወርቁ "Ulysses" የተባለውን የጀምስ ጆይስን ዝነኛ ልብወለድ ዘዬ የተከተለ ይመስላል። ሴራው በአጭሩ ይሄን ይመስላል፦

💎እንግዶቹ ወደ አርማኒያ ከመሄዳቸው በፊት በሶስት ወጣት ገፀባህሪያት መካከል ደብረሲና ውስጥ የፍቅር ግንኙነት ይፈጠራል። አጣሁ ወሮታ ለእመቤቷ እንደነገረቻቸው ከሆነ አቶ ክብረት ለፍሬዋ የጋብቻ ጥያቄ አቅርቧል። ፍሬዋ ጅረቱ አጠገብ ሆና ከምታነበው ደብዳቤ የአቶ ወልዱ ልጅ በላይም ከእሷ ፍቅር ይዞታል።

💎ይህ የፍቅር ትሪያንግል አደፍርስ ወደ አርማኒያ ሲደርስ ከሚገጥመው የተወሳሰበ ግንኙነት የቀደመና በንጽጽር ቀላል ነው። ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው።

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅


📖 ካነበባችሁት መጻህፍት 1ኛ የተመቻችሁ ምንድን ነው ? እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ ቤተሰብ 😁🙏

👇👇👇


አደፍርስ.pdf
24.4Мб
📚አደፍርስ 📚

📝ደራሲ:- ዳኛቸው ወርቁ
📜ይዘት:- ልቦለድ
📖የገፅ ብዛት:- 332
🗓 ዓ.ም :- 1962
⬇️size :- 32 MB
🖨አታሚ :-ንግድ ማተሚያ ቤት
🪝Type :- #pdf #ልቦለድ
🔔 ቻናል :- @AmbaBooks|📚

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅


📚 አደፍርስ 📚

📝ደራሲ:- ዳኛቸው ወርቁ
📜ይዘት:- ልቦለድ
📖የገፅ ብዛት:- 332
🗓 ዓ.ም :- 1962
⬇️size :- 32 MB
🖨አታሚ :-ንግድ ማተሚያ ቤት
🪝Type :- #pdf #ልቦለድ
🔔 ቻናል :- @AmbaBooks|📚

📢ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅


❓የመሪነት መርህ  ‼️

እስኪ እንወያይ፤ ጎበዝ መሪ ሊኖረው የሚገባው  ዋና መርሆች ምን ምን ናቸው?🤔

ከእናንተ ልምድና እይታ እንስማ። 👇

5k 0 1 12 11

📚ከእናንተ ለእናንተ

የቻናል ቤተሰብ ፦
CHAYNEH W/GEBRIEL«አንዳንድ የሶፍት ኮፒ መጽሐፍትን
ማጋራት እፈልጋለሁ፣ ፈቃደኛ ከሆንክ።»


እኛም ፦
AmbaSupport >🙏


📚የተላኩልን መፅሀፍት

📏 አደፍርስ
📏 ገመና
📏 ደማቆቹ
📏ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ
📏ወዳጄ ልቤ እና ሌሎችም
📏ጎረቤት ፈልጊ ነበር
📏የአንድ ሺ ከአንድ ለሊት አስደናቂ ታሪክ

እነዚህ መፅሐፍ post  እንድናደርግ በ React ....ፍላጎታችሁን አሳዩን ።

እንዲሁም ልክ እንደ ወንድማችን #CHAYNEH_W/GEBRIEL በኛ  ቻናል ማጋራት የምትፈልጉት መፅሐፍ የፍቅር ታሪክ እና አስተማሪ ታሪኮች  እጃችሁ ላይ ካለ አጋሩን መልሰን ለእናንተ እንጋራለን 🙏

ሌሎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📔ማቆያ ➤ @Amba_Pdf_Books✅
🎭 ትረካ ➤ @Amba_Treka✅
🎓ትምህርት➤@Yetmhrt_Pdf✅
🎵 ሙዚቃ ➤ @AmbaMusic1✅

Показано 20 последних публикаций.