✨✨ፍቅር ቅብ-20✨✨
ለቅፅበት ሀኒን ከአእምሮዬ የሚያስወጣልኝ ባገኝ ሳልደፋ 'እሺ' እንደምለው አውቃለሁ....
እጄ ላይ ያለውን ሹካ አስለቀቀና በሹካው ቦታ እጁ ተገኘ....የእጁን ልስላሴ ነግሬያችኃለሁ አይደል....እሱ ብቻ የሚሰጠኝ ምቾት ይሰማኝ ጀመር.....እጄ ከርዳዳ ስለሆነ ነው መሰለኝ የእጁ ልስላሴ ልቆ ይሰማኛል....
እጄ መከርደድ የጀመረው እናቴ እግሯ ከቤት ከወጣ ማግስት ከአባቴ ሻካራ ጃኬቶች ጋር መታገል ስጀምር ነው....የእናቴ እጅም ከርዳዳ ነበር.....ማታ ማታ ቀኝ እጄን ይዛ ትፀልይ ነበር....ምን እንደምትል ባላውቅም በጣም በቀስታ ታነበንብ ነበር.....እሷ ከሄደች በኃላ እኔም በከርዳዳ እጆቼ የታናሽ እህቴን ቀኝ እጅ ጨብጬ ሳነበንብ ራሴን አገኘሁት.....ያኔ ነው እናቴ ምን ብላ ትፀልይ እንደነበር ለመገመት የበቃሁት.....
ከከረደደ እጅ ጀርባ የከረደደ ትናንት የገገረ ልብ አለ.....ውሀ ቀጠነ ብሎ ባር ባር ከሚለው ሰው ጀርባ ሙሾ የሚያስወርድ ትናንት አለ.....በቀላሉ ማጅራቱ የሚጎብጥ ሰው ጀርባ ማጅራት ገትር የሚያሲዝ ትናንት ያልታወቀለት ቁስል አለ።
ሁላችንም የምንፈርደው የደረስንበት ላይ አይደል....የሌላውን ሸክም እንዳናቀል እኛም ሸክም የከበደን ነን....
የእጄ መጠጠር የጎረበጠው አይመስልም.....ተጠጋኝ.....ይሄ ዮናስ የሚጠጋኝ አይነት መጠጋት....'ዮናስ መክሮት ነው እንዴ' የሚያስብል አይነት መጠጋት.....እጁን ግን ወደሌላ ቦታ አልሰደደም.....ደስ አለኝ.....እጁን እንቁዬ ላይ ሳይጭን ልቤን ቀጥ ያደረጋት የመጀመሪያ ሰው.....መክብብ.....አይኔ ላይ በመቆየት ብቻ ላብ በላብ ያደረገኝ የመጀመሪያው ሰው.....መክብብ....."እወድሀለሁ.....በጣም እወድሀለሁ" አልኩት አይኑን ከአይኔ ሳይነቅል.....አስተያየቱን ፈራሁት.....ከማላብ አልፌ ማቃሰት ሳልጀምር እንኳን እንደምወደው ነገርኩት .....ያን ምትሀት ጥርሱን ገለጥ አረገው.....በጥርሱ ብቻ ብዙ ብዙ ማለት ይችላል.....በአይኑ ብቻ ስሜትን መበርበር ይችላል.....
ከቅድሙ ይበልጥ ተጠግቶኝ አይኖቼን ሳመ.....ወደ አይኖቼ ሲጠጋ ሊስመኝ እንደሆነ ገባኝና አይኖቼን ገርበብ አደረግኩለት....አይኖቼን ወደቦታቸው ሳልመልስ ከንፈሮቼን አንድ በአንድ ሳመ....
ልክ እንደጉንጭ ቀለል አድርጎ ነበር የሳመኝ....ከንፈር በክፍልፋይ እንደሚሳም ባላውቅም ዮናስ ጋር የሌለ የጨዋ አሳሳም ይሆናል ብዬ አለፍኩት....እሳት እንደነካ ሰው ከከንፈሮቼ በፍጥነት ሲላቀቅ ከንፈሮቼ እኔ የማላውቀው አንዳች መለኮታዊ ሀይል ይኖራቸው ይሆናል ብዬ ተውኩት....ከንፈሮቼ ላይ ባይቆይም አይኔ ላይ የቆየው መቆየት በልጦብኝ ልብ ላለማለት ወሰንኩ.....መሳም አቅቶት ሳይሆን ጊዜው ስላልመሰለው አላረዘመው ይሆናል ብዬ ዝም አልኩ.....የሚጠጣ ክትፎ አፍንጫዬ ላይ አስጠግቶ እንደነጠቀኝ አይነት ስሜት ቢሰማኝም መክብብ ስለሆነ ብቻ ዝም ጭጭ ረጭ አልኹ....
'የእራት ግብዣ መዝጊያ እራት መብላት ብቻ መሆን አለበት' ትለኝ ነበር ሀኒ በእራት ሰበብ ቁርስ አብልቶ ከሚሸኘኝ ዮናስ ስመለስ.....'እራት ላብላሽ ካለ መብላት የሚፈልገው ነገር አለ' ትለኝም ነበር...... ከምሽቱ ሶስት ሰአት ሲሆን መክብብ ሰአቱን አየት አረገና "ብንሄድ ይሻላል.....እየመሸ ነው....ቤተሰቦችሽም ይጨነቁ ይሆናል" አለኝና አስተናጋጁን ጠርቶ ሂሳብ አስተመነ.......
መኪናው ውስጥ ገባን....አልፎ አልፎ እያየኝ ያን ምትሀት ገለጥ ያደርግልኛል.....ለሀገር የሚበቃ ጥርስ ይዞ እዚ ምንድን ነው ሚሰራው እላለሁ....ግብፅ ስትተብትብን ምናል የመክብብን ጥርስ ይዘውት የግብፅ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ቢሄዱና ቢያደነዝዟቸው.... የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምን ነካው.....የዚን ጥርስ ባለቤት ግብ ጠባቂ ቢያደርጉት ምን አለ....አንዴ ፈገግ ካለ እንኳን ተቃራኒ ቡድን ይቅርና ሊገባ የሚንደረደረው ኳስ እግር አውጥቶ ወደኃላ ያፈገፍግ ነበር....አለማወቅ።
ቤቴ እንደደረስኩኝ ግንባሬን ሳመኝና ከመኪናው ወረድኩ.....ጊቢያችንን ማንኳኳት ስጀምር ሞተሩን አስነሳ.....መኪናው ከአይኔ ሲሰወር ሀኒ ጭንቅላቴ ላይ ተንሰራፋች።
ቤት ስገባ እህቴ እያጠናች አባቴ ደግሞ ዜና ከሚዘግበው ጋዜጠኛ ፊት ለፊት ተቀምጦ እያንቀላፋ ነበር....
እራት በልተናል ቢሉም 'እድል ስፔሻል' የሚባለውን ምግቤን ሰርቼ ካልበላችሁ ብዬ አስጨነቅኳቸው.....በሉልኝ....."ዛሬ ጫን ያለው ነው ባክሽ....ምን ተገኘ" አለኝ አባቴ....."ደስ ብሎኝ ነው እንዲሁ.....እስቲ መርቀኝ.....".....አልኩትና ጉልበቱ ላይ ተደፋሁ.....
"እድሜ ይስጥሽ....ጤናሽን አይንሳሽ....ልብሽን ይጠብቅልሽ....እመቤቴ በፈረሰው ጎንሽ ትቁም.....".....አለኝና አይኑ ውስጥ የተጠራቀመውን እንባ በጋቢው አደራረቀ....."የፈረሰው ጎንሽ" ያለው ጋር እስኪደርስ ደህና ነበርኩ.....ካጎነበስኩበት ተነስቼ አቀፍኩት....ሳቅፈው ባሰበት....እሱም የሚመርቀው አጥቶ እንጂ የፈረሰበት ጎን እንዳለው ትዝ አለኝ....
እንደ እኔ እንደ እኔ ህይወት ሰፊ ካሬ ያላት መሬት ናት....የፈረሰ ጎናችንን ተወት አርገን ሌላ ማንነት ለመገንባት የሚያስችል ትርፍ ቦታ አላት.....የፈረሰው እስኪጠገን መጠበቅ ሞኝነት ነው.....እሱን የሚጠግነው ጊዜ የተባለ መሀንዲስ ነው.....ሌላው ካሬ ግን የእኛ ሀላፊነት ነው።
"ከትዳር ጋር የተያያዘ ምርቃት የለህም አባዬ.....".....አልኩት ከእቅፉ ሳልወጣ....አንድም ለመመረቅ ደግሞም መላቀሳችንን ረዝሞ ለእህቴ ጥያቄዎች አሳልፌ እንዳልሰጥ......
ከት ብሎ ሳቀና "ኧረ ሞልቶ".....አለና አዥጎደጎደው....ጉልበቱን ስሜ ተነሳሁ.....ቡና ካላፈላሁ ሞቼ እገኛለሁ ስለው 5 ሰአት እያለፈ ነበር......
"ውቃቢ እንዳለበት ሰው በጠራራ ለሊት....?".....አለ ከላዩ የወደቀውን የጋቢ ክፍል ወደቦታው እየመለሰ....
"መች ስድስት ሰአት ሆነ አባዬ ደሞ" ብዬ እንደማኩረፍ ስል እንዳፈላ ተፈቀደልኝ.....
"ፊትሽ ሁላ ፈካ....የሰጠሽን የሰጠሽ አምላክ ይመስገን.....".....አለኝ አቦል ቡናውን እየተጎነጨ።
*
አተኛኘቴ የሬሳ ነበር.....የእህቴ አቀሳቀስ ደግሞ ሬሳ የሚያስሮጥ ነበር....
የተጣጠፈ ወረቀት በእጄ ሰጠችኝ እና እያለከለከች ማውራት ጀመረች......"እድል የሆነች ተለቅ ያለች ሴትዮ ናት ለእህትሽ ስጫት ብላ የሰጠችኝ....ነጠላ ለብሳ ነበር....አጠር ያለች.....".....እንዳለችኝ ከአልጋዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ.....አባታችን ቤት አልነበረም.....እጇን እየጎተትኩ ይዣት ወጣሁ....."በየት በኩል ነው የሄደችው ታስታውሻለሽ....እእእ" አልኳት በተጣደፈ ሰው ድምፅ....."ሰጥታኝ ታጠፈች....".....ባለችኝ መንገድ ታጠፍኩና ከአራት መንታ መንገድ ጋር ተፋጠጥኩ.....አንቺ በዚኛው ሂጂ እኔ ደግሞ በዚህ ብዬ ከአራት መንታው ሁለቱን መንገድ መረጥኩ.....በህይወቴ እንደዚህ የሮጥኩበትን ቀን አላስታውስም.....ልቤ ልትፈነዳ አንድ ሀሙስ እስኪቀራት ድረስ ሮጥኩ.....ከእንባ ጋር ሮጥኩ....ከትናንቴ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዤ ሮጥኩ.....
አላገኘኃትም።