በሰላም ለሰላም መስራት ለራስም ለወገንም ከእንቁ የከበረ፣ከጊዜው ጋር አብሮ የሚጓዝ የዘመኑ ገድል ነው።
ህዝባችን ሰላም ይሻል፣በጦርነት የጎበጠ ወገቡን በሰላም ቀና ማድረግ ይፈልጋል፣የተሸከመውን ጨካኝ ቀንበር ከትከሻው ማውረድን ይናፍቃል፣በእምባ እና በሀዘን የከረመ ፊቱን ፈገግ ማድረግን አብዝቶ ይመኛል፣በስደት እየተንከራተቱ እግሮቹን፣በልመና እየተሸማቀቁ እጆቹን ማሳረፍ ይፈልጋል።
በገዳይና ሟች ወንድማማቾች፣በአባራሪና ተባራሪ ቤተሰቦች ወላጆች ማልቀስ ሰልችተዋል።በየጊዜው ሰላሜን መልሱልኝ፣ጦርነቱ ይብቃ፣መሰደዴ፣መፈናቀሌ፣መሞት መቁሰሌ፣ከንቱ መከራየ በቃኝ እያለ ተማፅኗል።
አሁን አሁን ግን ተስፋ ሰጭ ጅምሮች እየተከናወኑ ነው። የህዝባችንን ሰላም መመለስ የሚያስችሉ በሰላማዊ መንገድ የእጅ መስጠት በጎ ተግባራት እየተፈፀሙ ነው።
በዚህ ጊዜ እጅ መስጠት ህይወት ከመስጠት የበለጠ ዋጋ አለው።በርካታ የህይወት መስዕዋትነት ተከፍሏል ነገር ግን የተከፈለው ህይወት ዋጋ ሳይሆን ኪሳራ ነው ያመጣው።ትርፋማው መስዕዋትነት ለራስም ለወገንም ሲባል በሰላማዊ መንገድ ወደ ማህበረሰብ በመቀላቀል የራስን ማህበራዊ ሰናይ ተግባር መፈፀም ነው።
ይህም ተግባር በክልላችን የተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜ በርካታ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ናቸው።በየቀኑ ቀላል የማይባሉ ታጣቂዎች ከገቡበት የጦርነት አዙሪት እየወጡ ህይወታቸውንም ማህበረሰባቸውንም እጅ በመስጠት ጥበብ እየታደጉ ነው።
በጎንደር፣በሸዋ፣በወሎ፣በጎጃም ባሉ በርካታ ወረዳዎች እና አካባቢዎች በየዕለቱ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገድ እጅ የሚሰጡ አካላትም ለቀሪ አጋሮቻቸው ሳይቀር ስለተያዘው የትጥቅ ትግል አክሳሪነት ምክረ ሀሳባቸውን ሁሉ በመስጠትና የተሀድሶ ስልጠና በመውሰድ የጫካ ስጋትና መከራቸውን አሰናብተው ከማህበረሰባቸው ጋር የተረጋጋ ህይወትን እየመሩ ይገኛሉ።
በእኛ በኩልም የተጀመሩ የሰላም ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እየተመኘን ህዝባችን ከገጠመው የጦርነት አባዜ ለመውጣት ብቸኛው መፍትሔው ሰላማዊ መንገድ መሆኑን ልብ ማለት ምርጫ ሳይሆን ግደታ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል እንላለን።