በሆስፒታል ውስጥ አስታማሚ መስሎ ሞባይል የሰረቀው በእስራት ተቀጣ።
በአዊ ብሄረሰብ አሰተዳደር ቻግኒ ከተማ ህዳር 14/2017 ዓ/ም ከንጋቱ 11:40 ሠዓት ሢሆን የግል ተበዳይ ወንድሙን ቻግኒ ከተማ 02 ቀበሌ ቻግኒ 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና የመጣውን በማስታመም ላይ እያለ አንድ ሞባይል ቻርጅ ካደረገበት ላይ ተጠርጣሪ መሀመድ አህመድ ሀሠን በሀሠት አስታማሚ መስሎ ሆስፒታል በመግባት ሞባይሉን ቻርጅ ከተደረገበት ስፍራ ሠርቆ ከወሰደበት የሆስፒታሉ ጥበቃዎች ተከታትለው ከእነ ኤግዚቪቱ በመያዝ ለፖሊስ አስረክበዋል።
የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ፖሊስም ፈጥኖ በመድረስ ተጠርጣሪውን እና ምስክሮችን አያይዞ በመውሠድ ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ ወንጀል ተይዞ ምርመራውን በማጣራት ምርመራ መዝገቡን ለሚመለከተው ዐ/ህግ ተልዕኮ ምርመራ መዝገቡ የቀረበለት የጓንጓ ወረዳ ፍ/ቤትም በቀን ህዳር 17/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሣሽ መሀመድ አህመድ ሀሠን የተባለውን ግለሰብ 2 ዓመት ከ6 ወር ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን የቻግኒ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ኅላፊ ኮማንደር አድገህ ልመነህ ገልፀዋል። ኅላፊው አያይዘውም የጉዳዩ ማነስና መግዘፍ ሳይታይ ተቋማት የውስጥ የቁጥጥርና ክትትል ስርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
መረጃው፦ የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ነው።