ህፃናትን መርዛ የገደለችው የቤት ሰራተኛ ላይ የተሰጠው ፍርድ ፀንቷል።
ይግባኝ በመጠየቅ ከእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የ23 አመት እስራት እንንዲሻሻል የተደረገላት ተከሳሽ በይግባይ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ሆኗል።
ተከሳሽ ስራ ደጀን የተባለችው ግለሰብ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ፍኖተ አካባቢ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራበት ወቅት የአሰሪዋን ሶስት ህፃናት በመመረዝ እንዲሞቱ በማድረጓ የባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነሀሴ 9/2015 ዓ/ም በአስቻለው ችሎት የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት መወሰኑ ይታወቃል።
የልጆቹ አባት አገባሻለሁ ብሎ ስላታለለኝ በንዴት ግለሰቡን ለመበቀል የሶስቱን ልጆች ምግብ መርዥዋለሁ በሚል በወቅቱ ለፍርድ ቤት የእምነት ቃሏን የሰጠችው ተከሳሽ በዚህም ሁለቱ ህፃናት ወዲያውኑ ሲሞቱ አንደኛዋ የዘጠኝ ዓመት ልጅ በሰዎች እርዳታ ለህክምና በቅታ መትረፋን በወቅቱ መዘገባቸን ይታወሳል።
ይሁን እንጅ የህግ ሂደትን ተከትሎ የተከሳሿ ባቀረበችው የፍርድ ይቀነስልኝ ይግባኝ አቤቱታ ሲያከራክር ቆይቶ ስልጣኑ ያለው ፍርድ ቤት እስራቱን ከእድሜ ልክ ወደ 23 ዓመት ፅኑ ቀንሶትም ነበር።
ወንጀሉ ምንም በማያውቁ ህፃናት ላይ ጭካኔ በተሞላበት አረመኔያዊ ተግባር በእቅድ በሙሉ ሀሳብና ድርጊት የተፈፀመ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መቀነስ የለበትም በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብሎ ሲከራከሩ መቆዬታቸውን የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የወንጀል ዓቃቢ ህግ አቶ ደረጀ ቁምላቸው ለዝግጅ ክፍላችን ገልጸዋል።
ከዓቃቢ ህግ የቀረበለትን አቤቱታ በጥልቀት ሲመረምር የቆየው ሰበር ሰሚ ችሎትም ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ/ም ባስቻለው ችሎት 23 ዓመቱን ፍርድ በመሻር በስር ፍርድ ቤት በተከሳሿ ላይ ተወስኖ የነበረው የእድሜ ልክ ጽኑ እስራትን በማፅናት ውሳኔው ተፈጻሚ እንዲሆን የወሰነ መሆኑንን ዓቃቢ ህጉ ተናግረዋል።