የምስራቅ ጎጃም ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የ6 ወር የሰላም ማስከበር ስራን በደጀን ወረዳ መገምገም ጀመረ።
መምሪያው ባለፉት 6 ወራት የፀጥታ ተቋማትን በማደራጀትና በማጠናከር በዞኑ በሚገኙ አካባቢዎች አጋጥሞ የነበረውን የፀጥታ ችግር በመቆጣጠር የህብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን ማከናወን መቻሉ ተገልጿል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አበባው በለጠ በውይይት መድረኩ መግቢያ ላይ እንደተናገሩት በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኘው የፀጥታ ኃይል በሙሉ ፍላጎትና ወኔ ራሱን አደራጅቶ በመንቀሳቀስ ከቁጥጥር ውጭ ሆነው የነበሩ አካባቢዎችን መልሶ በመቆጣጠርና አስተዳደር በመመስረት የህዝቡን ሰላም በማረጋገጥ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሰራው ስራ ለሌሎች አካባቢዎች አርዕያ ነበር ብለዋል።
የፀጥታ ኃይሉ ባለፉት 6 ወራት የነበሩ ጥንካሬዎችን የበለጠ በማጠናከርና የነበሩ ክፍተቶችን ለይቶ በመስራት ዞኑን የተረጋጋ ሰላም የሰፈነበት ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉም አቶ አበባው አጽንኦት ሰጥተዋል ሲል የምስራቅ ጎጃም ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።