እብዱ ዮሐና
....................ምዕራፍ ስምንት(13)
«አቤቱ ኢየሱስ! እነዚህ ሰዎች ለስምህ ክብር ሲሉ ሳይሆን ለራሳቸው ክብር ሲሉ ቤተ-መቅደሶችንና ፅላቶችን ሰርተዋል፡፡
እነዚህን መታሰቢያዎችህን በሀር በተሰሩ አልባሳትና በቀለጠ ወርቅ አንቆጥቁጠዋቸዋል፡፡ የአንተ ድሆች ብጣቂ ለብሰው ወይም ዕርቃናቸውን በምሽት ብርድ ሲንዘፈዘፉ አይተዋቸው እንዳላዩ ሆነው ያልፋሉ፡፡
እነሱ አየሩን በዕጣን ጢስና በሻማዎች መብራት እየሞሉ፣ እነዚያ እውነተኛ አማኞች ግን የዕለት ጉርሳቸውን ተነጥቀዋል ........
. «አቤቱ ክርስቶስ! አንተን በዜማ ለማሞገስ ድምጻቸውን ከፍ ቢያደርጉትም፣ የውዳሴ መዝሙሮቻቸውንና ቅዳሴዎቻቸውን የገደል ማሚቱ በየቦታው ቢያስተጋባም፣ ባሎቻቸውን የሞቱባቸውን ሴቶችና የወላጅ አልባ ህፃናትን ሙሾ የሚሰማ ጆሮ የላቸውም.....
«አቤቱ ኢየሱስ ሆይ! እንግዲያውስ ለሁለተኛ ጊዜ መጥተህ ቤተ መቅደስን የተንኮለኛ ብልህ እፉኝቶች ጐጆ ያደረጉትን፣ በሀይማኖት ስም የሚነግዱትን ትዕቢተኞችና ውሸታሞችን አስወጥተህ አባርራቸው፡፡
ጠንካራና ከልብ የመነጩ የዮሐና ቃላት የሚያጉረመርሙ የድጋፍ ድምጾች አገኙ፡፡ የአስተዳዳሪዎቹ መምጣትም አላስፈራውም፡፡ እንዲያውም ድፍረት ጨምሮ በሀይለኛ ድምፅ መናገሩን ቀጠለ፡- .....
«ኦ ኢየሱስ! ናና ከደካሞች ላይ የደካሞችን፣ ከእግዚኣብሄር ላይ የእግዚአብሄርን የሚነጥቁትን ቄሳሮች ዋጋቸውን ስጣቸው፡፡ አንተ በቀኝ እጅህ የተከልከው የወይን ተክል በስግብግብ ትሎች ተበልቶ ግንዱም ተረጋግጧል፡፡ የሰላም ልጆች ተለያይተው አርስ በርስ እየተዋጉ ባሉበት በዚህ ሰዐት፣ እነዚህ አስመሳዮች በድግስና በበዓላት ቀናት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ እያሉ ለይምሰል ይፀልያሉ፡፡
የሰማዩ አባትህስ በነዚህ በሀጢአት በተሞሉ ክንፈሮችና ከቀጣፊ ምላሶች በሚወጡ ቃላት ለይምሰል ሲወደስ ደስ ይለዋልን? ጨቋኝና ተጨቋኝ በሞሉባት በዚህች ምድርስ ደስታና ሰላም ይኖራል ብለህ ታስባለህ? እነዚህ የገዢዎችን ከርስ ለመሙላት እንደ ባሪያ የሚለፉ ድሆችስ . ሰላም መጥቶ ከድህነት አረንቋ ሊያወጣቸው ይችላልን?...
«ኧረ ለመሆነ _ ሰላም _ ምንድነው? የሚገኘውስ ከወዴት ነው? በቅዝቃዜና በጨለማ በተዋጡ ደሳሳ ጐጆዎች ውስጥ የእናታቸውን የደረቁ ጡቶች በሚምጉ ህፃናት ዘንድ ነውን? ወይስ በረሀብ እየተጠበሱ በሚቆረቁር የድንጋይ መደብ ላይ ተኝተው፣ ለወፋፍራም አሳሞቻቸው ከሚወረውሩላቸው ምግብ የተራረፈውን ያህል እንኳን ባገኘን ብለው በሚመኙና እርዳታን በሚሹ ሚስኪኖች ጉስቁል ኣካል ውስጥ ይሆን ሰላም
ያለው?
..........ይቀጥላል............
👍👍👍👍👍👍👍👍
https://t.me/Asresee