🔼አንድ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፌሰር አስማሪው ጋር መናፈሻው ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ፡፡
አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደ ጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው፡፡
ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ፅዶችና ሳሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፤ተማሪው የፅዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ቲቸር ዛሬ አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም? ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል፡፡
አስተማሪውም “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ውስጥ ገንዘብ ከተህበት ና፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡
ተማሪው አስተማሪው እንዳለው ቀስ ብሎ በሰውዬው ጫማ ውስጥ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋር ደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ፡፡ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረዋል ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል፡፡ ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው በኋላ የሁለተኛ እግሩንም ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል፤ ሰውዬው አላመነም!! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ፦
- “ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል? ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳን አውቀህ ነው አይደል? የልጆቼ ዳቦ ማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል? ምስጋና ሲያንስህ ነው ጌታዬ” አለ፡፡ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ከልቡ አዘነ አይኖቹም እንባ አቀረሩ፡፡አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትሪክ ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው፤
ተማሪው እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማሩኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም፤ በህይወቴ የማረሳውን ትምህርት ነው ያስተማሩኝ እውነትም ከመቀበል መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው፡፡
"ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና!! ✔️👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ። 📱ቴሌግራም👉 @Beleqe_boostup
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp
🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/
📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup