🆕የትሮይ ፈረስ
የትሮይ ፈረስ ታሪክ በጥንታዊት ግሪክ ትሮይ በተባለች ከተማ ካጋጠመው አሳዛኝ ታሪክ የተወሰደ ነው። ታሪኩም እንደዚህ ነው።
የትሮይ ልዑል በእንግድነት ወደ ስፓርታ ይሄዳል። አጋጣሚ ሆኖ ከስፓርታው ንጉሥ ሚስት ጋር በፍቅር በመውደቁ ይዟት ወደ አገሩ፣ ወደ ትሮይ ኮበለለ (የእሷም ፍላጎት ታክሎበት)።
የስፓርታ ንጉሥም ንግሥቲቷን ለማስመለስ ሠራዊቱን በብዙ የጦር መርከቦች ጭኖ ወደ ትሮይ ገሠገሠ። ይሁን እንጂ የትሮይ ከተማ በጣም ጠንካራ በሆነ ግንብ የታጠረች በመሆኗና የትሮይ ሠዎችም ግንቡን በምሽግነት በመጠቀም ሊያስጠጓቸው ስለአልቻሉ ስፓርታውያን ሌላ ብልሃት መፍጠር አስፈለጋቸው።
በዚህ ጊዜ ልዩ ልዩ እንጨቶችን በመገጣጠም በጣም የሚያምር ትልቅ የፈረስ ቅርጽ ሠርተው በሌሊት ከአጥሩ አጠገብ አስቀምጠውት ይሄዳሉ። የትሮይ ሠዎችም የፈረሱን ምስል ጠዋት ሲያዩት በደስታ ፈነደቁ፤ "ጠላቶቻችን ሸሹ። አምላካችን ደግሞ የድላችንን ገፀ በረከት ላከልን" ብለው እየጨፈሩ ወደ ውስጥ አስገቡት።
ከዚህ በኋላ በከተማይቱ ታይቶ የማይታወቅ ፈንጠንዝያና ድግስ ሆነ። ሲመሽ ሁሉም በጭፈራና በስካር ደክሞት ስለነበር ባለበት ተኛ። በራቸውን ከፍተው ባስገቡት የፈረስ ሀውልት ውስጥ ግን የስፓርታ ወታደሮች ተደብቀው ገብተዋል።
ሁሉም ሰው እንቅልፍ ውስጥ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ወደ ውጭ በመውጣት ከውጭ ሆኖ በተጠንቀቅ ይጠብቅ የነበረውን የስፓርታን ጦር በሩን ከፍተው ወደ ውስጥ እንዲዘልቅ አደረጉት።
ወዲያው እንደገቡ የትሮይ ሰዎች እንቅልፍ ላይ እንዳሉ እሳት ለቀቁባቸው። ከዚያ በኋላ ከቃጠሎው እየሮጠ ለማምለጥ የሚሞክረውን ሁሉ እየተከታተሉ ፈጁት፡፡ አንድም እንኳ አላስተረፉም፡፡ ከተማዋም ለዘላለም ዳግም እንዳትገነባ ሆና ወደመች።
━━━━━━ 📌በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።
📱ቴሌግራም👉 @Beleqe_boostup
📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp
📱ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/📱📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup