የመጀመሪያው ፍቅር ያዘኝ።የመጀመሪያው ፍቅር፤የእናትና የልጅ ፍቅር ነው።ከእናቴ ፍቅር ያዘኝ።ብን.....! አልኩ፥ እፍፍፍ...!በየደቂቃው ራሴን ፍለጋ ዐይን ዐይኗን ማየት ሆነ፨በፍቅር አበድኩላት።ፍቅር ማለት ለካስ ራስን በሌላው ውስጥ ማየት ነው።ሳድግ ለምን እንዲህ ውስብስብ መሰለኝ!? እሷም እንዲሁ ዐይኔ ዐይኔን ስለምታየኝ ፍቅር ሳይዛት አልቀረም!መተያየት በመተያየት ሆንን።
አንዳንድ ጊዜ እናቴ ዐይን ዐይኔን ስታየኝ ትቆይና በዚያው እ..ል..ም ትላለች።ብጠብቅ አትመለስም፥ብጠብቅ...፤እቁነጠነጣለሁ..ምንም መልስ የለም።አተኩሬ ዐይኗን ሳይ፤እኔም ዐይኗ ውስጥ የለሁም።የት እየሄደች ነው? እላለሁ።በብዙ ጉትጎታና መቁነጥነጥ ትመለሳለች።ስትመለስ ታዲያ የዐይኗ ነጭ፤ቀይ ደመና ያረግዛል።ትንሽ ቆይቶም ከዐይኗ ደመና፤ከፊያ ዝናብ መንጠባጠብ ይጀምራል።እኔ እረበሻለሁ።ደስ አይለኝም።ለምን እና ለማን እንደሆነ ሳላውቅ አጅባታለሁ።እናት ስታለቅስ ታሳዝናለች።ለቅሶዋ መቼም ቢሆን ስለ ራሷ አይደለም።
📓ርዕስ፦አለማወቅ
✍️ደራሲ፦ዳዊት ወንድምአገኝ
✈️ @Bemnet_Library