Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ለረጅም ጊዜ በዝምታ መቆየት ትችላለህ? የስነ-አእምሮ ጠበብት እንደሚሉን ከሆነ ለሶስት ሳምንታት ዝም ብለህ ከቆየህ፣ከዚያ ከራስህ ጋር ማውራት ትጀምራለህ።ያን ጊዜ ሁለት ቦታ ትከፈላለህ ማለት ነው።ተናጋሪም አድማጩም አንተ ትሆናለህ።በዝምታህ ፀንተህ ሶስት ወር ከቆየህ ደግሞ፤የእብዶች ሆስፒታል በር ወለል ብሎ ይከፈትልሀል።ምክንያቱም አሁን ሰው አጠገብህ ኖረ አልኖረ ግዴ የለህም።ታወራለህ፤ማውራት ብቻም አይደለም፤መልስም ትሰጣለህ።አሁን ምሉዕ ሆነሀል፣የሌላ ሰው ጥገኛ አይደለህም።እብድ ማለት ትርጉሙ በቀላሉ ይሄው ነው
እብድ ማለት መላውን አለም በራሱ ውስጥ ማግኘት የሚችል ማለት ነው።ተናጋሪ እሱ ነው፤አድማጭ እሱ ነው፤ተዋናዮ እሱ ነው፤ተመልካቹ እሱ ነው።በቃ ሁሉም እሱ ነው፤አለምን ሁሉ በውስጡ ያገኛታል።ራሱን ብዙ ቦታ ከፋፍሎታል።በዚህ የተነሳ ሁሉም ነገር ሽርፍራፊ ሆኗል።ሰዎች ዝምታን የሚፈሩት ለዚህ ነው፤ሳያስቡት ሊለፈልፉ እንደሚችሉ ይታወቃቸዋል።
📚ርዕስ፦ራስን ማግኘት
✍️ደራሲ፦ኦሾ
✈️ @Bemnet_Library