ሰማይነት 📖✨
"ፀሐይ ነች" ሲሉኝ...
ፀሐይ አይደለችም፣ እያልሁ የምናገር
"ጨረቃ ነች" ሲሉኝ...
ጨረቃ አይደለችም፣ ብዬ ምከራከር
"ኮከብ ነች" ሲሉኝ...
ኮከብ አይደለችም፣ ብዬ ምመሰክር
ሰማይ መሆንሽን፣ ስለማውቅ ነበር፡፡
"ፀሐይ ነች" የሚሉሽ፣ ፀሐይስ እነሱ
"ጨረቃ ነች" ያሉሽ፣ ጨረቃስ እነሱ
"ኮከብ ነች" የሚሉሽ፣ ኮከብስ እነሱ
ሰማይ ውበትሽ ላይ...
በቀን በጨለማ፣ የሚመላለሱ፡፡
✍️ በላይ በቀለ ወያ
ከዋክብትና ጨረቃ በደመቁበት በዚህ ውብ ምሽት፣ እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕
ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈
"ፀሐይ ነች" ሲሉኝ...
ፀሐይ አይደለችም፣ እያልሁ የምናገር
"ጨረቃ ነች" ሲሉኝ...
ጨረቃ አይደለችም፣ ብዬ ምከራከር
"ኮከብ ነች" ሲሉኝ...
ኮከብ አይደለችም፣ ብዬ ምመሰክር
ሰማይ መሆንሽን፣ ስለማውቅ ነበር፡፡
"ፀሐይ ነች" የሚሉሽ፣ ፀሐይስ እነሱ
"ጨረቃ ነች" ያሉሽ፣ ጨረቃስ እነሱ
"ኮከብ ነች" የሚሉሽ፣ ኮከብስ እነሱ
ሰማይ ውበትሽ ላይ...
በቀን በጨለማ፣ የሚመላለሱ፡፡
✍️ በላይ በቀለ ወያ
ከዋክብትና ጨረቃ በደመቁበት በዚህ ውብ ምሽት፣ እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕
ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈