የመጽሐፍ መረጃ | Book Mereja


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


​📚 የነፃ PDF መጻሕፍት፣ የመጽሐፍ ማጠቃለያዎች እና የታሪክ ድርሳናት መረጃ።
ለአስተያየትና ጥቆማ: @RealManTadi
Book Daily
https://telega.io/c/BookMereja

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


​"ሰዎች ስለ አንተ ያላቸው አስተያየት ያንተ እውነታ አይደለም።

ትልቁ ነፃነት የሰዎችን ውዳሴ ወይም ነቀፌታ ሳትፈራ፣ የራስህን እውነተኛ ማንነት መኖር ስትጀምር የሚመጣው ሰላም ነው።" 📖✨

​የቀኑን ድካምና አላስፈላጊ ሀሳብ በሮች ላይ ትታችሁ፣ ከራሳችሁ የውስጥ ሰላም ጋር የምትገናኙበት እረፍት ያለው ምሽት ይሁንላችሁ❕

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈




መርሳት... 📖✨

​"የማብድ ቢመስለኝ፣ ድንገት አንቺን ሳጣ
አረቄ ቤት ሔጄ፣ አረቄ ስጠጣ
አንድ ግጥም ሰማሁ...
ፍቅርሽን ከልቤ፣ ነቅሎ የሚያወጣ፡፡
​ያውም 'መንገድ' በሚል...
ለመንገደኛ ሰው፣ ሰካራም የፃፈው
እዛ ጋ ቁጭ ብሎ...
'ከዳችኝ' እያለ፣ የሚለፈልፈው
'መንገድ' የሚል ግጥሙ፣ ጆሮዬን ገረፈው፡፡
​ጆሮዬ ሲገረፍ፣
ጠባሳ ጣለብኝ፣ ግጥሙን እንዳልረሳ
'መንገድ አያደርስም
መንገድ አይመልስም፣ እግር ካልተነሳ❕'
እያለ ይገጥማል...
ደጋግሞ ደጋግሞ፣ ሌላ አይናገርም
እሱም ልክ እንደኔ...
አንዷን በመሔዷ፣ ሳያጣት አይቀርም፡፡
​ብቻ ሰክሪያለሁ...
ለመንገደኛ ሴት፣ የተፃፈ ግጥምን፣ ጆሮዬ ያደሞጣል
መሔድሽን ያየ፣ እንደሌለሽኝ ሲያውቅ፣ ሊኖረኝ ይመጣል
ይህ ነው መንገድ ማለት❕
የሰካራም ግጥምን ሰክሬ ስረዳው
ማፍቀር ሳይሆን ለኔ፣ መርሳት ነው ሚጎዳው❕

በቃ ረስተሽኛል❕" 💔

​እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈


🔔የአስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ

እህታችን አለምን እናድናት👏

⏩ከላይ በፎቶ ላይ ምትመለከቷት እናት የ3 ልጆች እናት ስትሆን እጅግ ጠንካራ ምሳሌ ምቶን ሴት ነበረች ። አሁን ላይ ግን ያ ጥንካሬዋን አታ በአልጋ ላይ ውላ እጅግ በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። ህመሙ ሲጀምራት ደም ግፊት እያለች መድሀኒት ስትጠቀም ቆይታ ነበር ግን ነገሩ እየባሰ ፊትዋን እያጠቆረው ሰውነቷን እያከሳው አቅም እየነሳት ቀስ በቀስ ያደክማት ጀመር ። ከዛም ድንገት ባልታወቀ ሁኔታ አልጋ ላይ አስዋላት። ሀኪም ቤት ስትሄድም የኩላሊት ህመም እንደሆነ እና በአስቸኳይ ንቅለ ተከላ መደረግ እንዳለበት መርዶ ተረዳት። እናም እናንተ ውድ ኢትዮጵያውያን ፊት እንድትረዷት መታለች። ይቺን እናት እናድናት እንድረስላት እኛ እያለን ልጆቿ ያለ እናት መቅረት የለባቸውም ። ነገ የኛን መጨረሻ አናውቀውም እናም ሁላችንም ተባብረን ነግ በኔ እያልን ተባብረን እናትርፋት

መርዳት የምትፈልጉ
📌ንግድ ባንክ፦1000798716461 የኮሚቴ account
✔️አዋሽ ባንክ፦013471004600800 አለም ወጋው
📍ቴሌ ብር፦0981067242


ሰማይነት 📖✨

​"ፀሐይ ነች" ሲሉኝ...
ፀሐይ አይደለችም፣ እያልሁ የምናገር
"ጨረቃ ነች" ሲሉኝ...
ጨረቃ አይደለችም፣ ብዬ ምከራከር
"ኮከብ ነች" ሲሉኝ...
ኮከብ አይደለችም፣ ብዬ ምመሰክር
ሰማይ መሆንሽን፣ ስለማውቅ ነበር፡፡
​"ፀሐይ ነች" የሚሉሽ፣ ፀሐይስ እነሱ
"ጨረቃ ነች" ያሉሽ፣ ጨረቃስ እነሱ
"ኮከብ ነች" የሚሉሽ፣ ኮከብስ እነሱ
ሰማይ ውበትሽ ላይ...
በቀን በጨለማ፣ የሚመላለሱ፡፡

​✍️ በላይ በቀለ ወያ

​ከዋክብትና ጨረቃ በደመቁበት በዚህ ውብ ምሽት፣ እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈


​"ሕሊናን ሸጉጦ
አንደበት አስጊጦ
ከመኖር ዘላለም፤
ለእውነት እየኖሩ 'ዱርዬ' መባልን
የመሰለ የለም
❕" 📖✨

​እውነተኛነታችንን ሳናጣ፣ ለሕሊናችን ታምነን የምንውልበት ሰላማዊ ቀን ይሁንልን❕ 🌸

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈


​"ምናልባት እኔ ፍጹም ወይም ምርጥ አይደለሁም፤ ግን ቢያንስ ለጊዜያዊ መዝናኛ ብቻ ብዬ የሰውን ልብ አልሰብርም። 💔

​ምንም ዓይነት ስሜት የሌላችሁ ሰዎች እባካችሁ ለማፍቀር አትሞክሩ❕ ፍቅር ከውስጥ የሚፈልቅ እንጂ በሰው ሰራሽ ጥረት ወይም ማስመሰል የሚመጣ አይደለም..." 📖✨

​እውነተኛ ፍቅርና የልብ ሰላም የሚሰፍንበት፣ እረፍት ያለው ምሽት ይሁንላችሁ❕ 💤

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈


ወንጀለኛው ዳኛ Book Mereja.pdf
23.9Мб
​📚 የመጽሐፍ ማጋራት / መረጃ 📖✨

​« ወንጀለኛው ዳኛ »
📜⚖️

​"የሕብረተሰብ ማኅበራዊ ሕይወትን፣ የትምህርትና የሥራ ሁኔታዎችን እንዲሁም የወጣቶችን እጣ ፈንታ የታሪክና የልብወለድ ዘይቤን አዋህዶ በጥልቀት የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ..."


📕​የመጽሐፉ መረጃዎች፦

​✍️ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
​📅 የታተመበት ዓመት፦ 1940ዎቹ / የቀደመ ዕትም (1938 ዓ.ም.)
​🏫 የመጽሐፉ ይዘት፦ በመጀመሪያ በትያትር መልክ ተዘጋጅቶ በኋላ በልብወለድ የቀረበ ሲሆን፤ የትምህርት፣ የወጣቶች ሕይወትና የማኅበራዊ ፈተናዎችን በሰፊው ይዳሳል።
​🎯 ዓይነት፦ ልብወለድ / ማኅበራዊና ታሪካዊ ጥናት

​💡 አጭር ማብራሪያ፦
ይህ መጽሐፍ «ወንጀለኛው ዳኛ» በሚል ርዕስ በታዋቂው ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ የተጻፈ ሲሆን፣ በወቅቱ የነበረውን የትምህርትና የማኅበራዊ ሕይወት ምስል በጥበብ የተሞላ ትረካ የሚያቀርብ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ሀብት ነው።


​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗@BookMereja
🔗@BookMereja
🔗@BookMereja


ክብረ ነገስት Book Mereja.pdf
8.4Мб
​📚 የመጽሐፍ ማጋራት / መረጃ 📖✨

​« ክብረ ነገሥት »
📜👑

​"የኢትዮጵያን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ክብር፣ የነገሥታቱን ትውልድ ሐረግ እንዲሁም የጽዮን ታቦት ወደ ኢትዮጵያ አመጣጥን በሰፊው የሚያስረዳ ጥንታዊ ድንቅ መጽሐፍ..."



📒​የመጽሐፉ መረጃዎች፦

​🏢 አሳታሚ፦ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)
​📅 የታተመበት ዓመት፦ መስከረም 1994 ዓ.ም.
​🏫 የመጽሐፉ ይዘት፦ መጽሐፉ የግዕዝ እና የአማርኛ ቅጅን ጎን ለጎን አያይዞ የሚያቀርብ ሲሆን፤ ከንግሥተ ሳባና ከንጉሥ ሰሎሞን ጀምሮ ያለውን የታሪክ አወቃቀር፣ የንግሥናን ክብር እና የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊቶችን በጥልቀት ይተነትናል።
​🎯 ዓይነት፦ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ባህል


​💡 አጭር ማብራሪያ፦
«ክብረ ነገሥት» የኢትዮጵያን የሺዎች ዓመታት የንግሥና እና የሃይማኖት ታሪክ አያይዞ የሚተርክ፣ የሀገሪቱን መንፈሳዊና ባህላዊ መሠረት ለመረዳት እጅግ አስፈላጊ የሆነ ታሪካዊ ሰነድ ነው።



​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗@BookMereja
🔗@BookMereja
🔗@BookMereja


የሽቶ ጠረን... 📖✨

​በአዲሱ ሰፈራችን ከጎረቤታችን ማሪቱ ቤት የገባው የመጀመሪያው ጉርስ በእንጀራ ላይ የተነሰነሰ ሽቶ የሚሸት ነበር።

አባቴ «የቆርቆሮውን አጥር በግንብ እንስራ» ሲል እናቴ «ከጎረቤት ጋር መቆራረጥ የለብንም» ብላ ተቃወመች።

አባቴም የቆርቆሮውን አጥር በእጁ ጠገነው።
​ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እናቴ በግንብ እንዲታጠር አባቴን በእንባ ተሞልታ መለመን ጀመረች። አባቴ ግን «ምን አጣሁ ብለሽ ነው የምታማርሪው?» ሲል ተቆጣት።

​እናቴም በሆዷ፦ "ጠረንህን ነዋ ያጣሁት..." አለች።
​አባቴ ማታ ማታ በቆርቆሮው አጥር ስር ሾልኮ ወደ ጎረቤት ግቢ ሲገባ እናቴ አውቃ ነበር።

እሷ የእሱን እቅፍና ፍቅር ስትናፍቅ፣ እሱ ግን የማሪቱን ሽቶ ስቦ አርፎ ነበር... ከዛች ቀን በኋላ እናቴ ስታንጎራጉር ሰምቼያት አላውቅም።
​

አንዳንድ ጊዜ በሰዎች መካከል ያለው ግንኙነት የሚሸረሸረውና የሚፈርሰው ከውጭ በሚመጣ አካላዊ መሰናክል ሳይሆን፣ በውስጥ በሚፈጠር የታማኝነትና የፍቅር ማጣት ነው።
የቅርብ ሰዎቻችንን ትኩረትና እውነተኛ ፍቅር እንዳናጣ እንጠንቀቅ።

​ብሩህና ሰላማዊ አዲስ ቀን ይሁንላችሁ❕

​ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈




​"በሕይወታችን ውስጥ ትልቁ ነፃነት የሚጀመረው ሌሎች ስለ እኛ የሚያስቡትን ነገር የመጨነቅ ፍላጎታችን ሲቆም ነው።

የራሳችንን እውነት መኖር ስንጀምር፣ የውስጥ ሰላማችንን ማንም ሊነጥቀን አይችልም።" 📖✨

​የቀኑን ውጣ ውረድና ጭንቀት በሮች ላይ ትታችሁ፣ በውስጣችሁ ካለው እውነተኛ ሰላም ጋር የምትገናኙበት እረፍት ያለው ምሽት ይሁንላችሁ❕

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕

👉 @BookMereja 👈


ግራጫ ቃጭሎች Book Mereja.pdf
70.4Мб
📚 የመጽሐፍ ማጋራት / መረጃ 📖✨

​« ግራጫ ቃጫዎች »
📝

​"በተለየ የሥነ-ጽሑፍ አቀራረብና ጥበብ የተሞላ፣ የማኅበራዊ ሕይወት ምልከታዎችንና ልዩ ልዩ ገጠመኞችን አቃፊ ድንቅ መጽሐፍ..."



📒​የመጽሐፉ መረጃዎች፦

​✍️ ደራሲ፦ አዳም ረታ
​📅 የታተመበት ዓመት፦ 1990ዎቹ / የቆየ ዕትም
​🏫 የመጽሐፉ ይዘት፦ መጽሐፉ በደራሲው ልዩ የፈጠራ ዘይቤ የተጻፉ የተለያዩ አጫጭር ታሪኮችንና የሕይወት ምልከታዎችን ያካተተ ስብስብ ነው።
​🎯 ዓይነት፦ ልብወለድ / አጫጭር ታሪኮች


​💡 አጭር ማብራሪያ፦
ይህ መጽሐፍ «ግራጫ ቃጫዎች» በሚል ርዕስ በታዋቂው ደራሲ አዳም ረታ የተጻፈ ሲሆን፣ በውስጡ ባቀፋቸው ማረፊያ ባላቸው ታሪኮችና በተለየ የትረካ ዘይቤው በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ድንቅ ሥራ ነው።



​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me


የንቃት ፀሀይ Book Mereja.pdf
19.3Мб
📚 የመጽሐፍ ማጋራት / መረጃ 📖✨

​« የንቃት ፀሐይ »
📜☀️

​"የሰው ልጅ የውስጥ እውነተኛ ሀይል፣ መንፈሳዊ ንቃትና የአእምሮ ነፃነት ላይ ያተኮረ ድንቅ ፍልስፍናዊ መጽሐፍ..."


🏫​የመጽሐፉ መረጃዎች፦

​✍️ ደራሲ፦ ኦሾ (ትርጉም፦ መርሻ በነበሩ)
​📅 የታተመበት ዓመት፦ 2009 ዓ.ም.
​🏫 የመጽሐፉ ይዘት፦ መጽሐፉ የሰው ልጅ በውስጡ የተቀበረውን እውነተኛ ማወቅ፣ አእምሮአዊ እንቅፋቶችን ማስወገድና ወደ ከፍተኛ የመንፈስ ንቃት መሸጋገር የሚችልበትን መንገድ ያብራራል።
​🎯 ዓይነት፦ የስነ-ልቦና፣ የፍልስፍናና የመንፈሳዊ ንቃት

​💡 አጭር ማብራሪያ፦

ይህ መጽሐፍ «የንቃት ፀሐይ» በሚል ርዕስ በመርሻ በነበሩ የተተረጎመ የኦሾ ሥራ ሲሆን፣ የሰውን ልጅ ውስጣዊ እውቀትና ንቃተ-ሕሊና ከፍ የሚያደርግ አሳቢ መጽሐፍ ነው።



​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me


ፈውስ የራቀው ሰው... 📖✨

​አለን ኤስ በአንድ ትልቅ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ድርጅት ውስጥ የመስክ ተወካይ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ ሰው ባለቤትና አራት ልጆች ያሉት ቢሆንም ከሌላ ሴት ጋር ድብቅ የፍቅር ግንኙነት መስርቷል።

​ወደ እኔ ሲመጣ ፊቱ ላይ ፍርሃት ይነበብበት ነበር፤ ቁጣ ቁጣም ይለዋል።
የእንቅልፍ እንክብል ካልወሰደ እንቅልፍ በዓይኑ አይዞርም።
ከፍተኛ የደም ግፊት እና ሐኪሙ ያላወቀለት ሌሎች የውስጥ ሕመሞች ነበሩበት።
በዚያ ላይ ከልክ በላይ ይጠጣል።

​ብዙም ሳይቆይ ለመረዳት እንደቻልኩት፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤው በውስጡ ያለ ስር የሰደደ የኃጢያተኝነት ስሜት ነው።

ያደገበትን ሃይማኖቱን እጅግ በጣም ያከብራል፣ ይፈራል።
በዚህ የተነሳ የጋብቻ ቃል-ኪዳኑን በማፍረሱ ውስጡ በወንጀለኛነት ስሜት እየተለበለበ ነበር።

​ይህንን የአዕምሮ ቁስል እንዲጠግግ እና ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ብሎ አዘውትሮ የሚወስደው መጠጥ ችግሩን ከማባባስ በቀር የፌደለት ነገር አልነበረም።
ነገሩ እሳትን በቤንዚን ለማጥፋት እንደመሞከር ነው።

​ይህ ሰው ለምን ፈውስ ራቀው⚡️
​አለን ስለ አዕምሮአችን ገለፃ ሳደርግለት በሚገባ አዳመጠኝ።

ችግሩንም ረጋ ብሎ አሰበው።
በመጨረሻ ድብቅ ግንኙነቱን ለማቆም ውሳኔ ላይ ደረሰ።
የመጠጥ ሱሱም ቢሆን ሳይረዳ ከራሱ ለመሸሽ ያደረገው ሙከራ እንደሆነ ተረዳ።

ድብቅ አዕምሮው ውስጥ የተሰነቀረው ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ተመንግሎ እስካልወጣ ድረስ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያገኝ ሲገነዘብ፣ በውስጡ የመተማመን መንፈስ ፈጠረለት።
​በመጨረሻም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ለመላቀቅ ቻለ።

​💡 ከጽሑፉ የምንወስደው ትምህርት፦
​ከተጠናወተን ጎጂ ልማድ ለመላቀቅ ጥልቅ ፍላጎት ካለን፣ 51% ፈውስ እንዳገኘን ይቆጠራል።
ይህን ጎጂ ልማድ ለማቆም ያለን ፍላጎት ለመቀጠል ካለን ፍላጎት የበለጠ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ መላቀቅ አይከብደንም።

​በአዕምሯችን መላልሰን የምናስበው ነገር የመጉላት ባህርይ አለው፤ በመሆኑም፦
• ከጎጂ ልማድ የመላቀቅን ነፃነትና የአዕምሮ ሰላምን መላልሰን እናስብ።
• አትኩሮታችንን ሁልጊዜ በዚህ አዲስ አቅጣጫ እናድርግ።
• ይህን ስናደርግ ቀስ በቀስ የነፃነትና የሰላም ስሜት በመላ አካላችን እየተሰማን ይመጣል።

​✍️ ጆሴፍ ማርፊ (Joseph Murphy)

📖"አእምሮን በብቃት በመጠቀም መልካም ሕይወትን የመምራት ቁልፍ ምስጢራት" (ትርጉም፦ እስክንድር ስዩም)

​ብሩህና የአእምሮ ሰላም የሞላበት አዲስ ቀን ይሁንላችሁ❕ 🌸

​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me


​"መኖር የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው❕

​በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው፤ ረሀብ የለም።
በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው፤ ብርድ የለም።

ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም፤ ምቾት፣ መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሀ ውስጥ መንሳፈፍ ነው።
ግን ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድክበት ቅፅበትየፍርሀታችን ይለወጣል።

​መተንፈስ ግድ ይላል❕ ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን፤ አለበለዚያ መኖር የለም❕ መታፈን፣ በረሀብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሀታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ።

በእናታችን ማህፀን ውስጥ የምናውቀው መኖርን ብቻ ነው።

መወለድ ግን አለመኖርን አመላካች ነው❕" 📖✨

​✍️ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ
📖 "አለመኖር"

​እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕ 💤

​ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕

👉 @BookMereja 👈


​"በዓላት የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታና የአንድነት መግለጫዎች ናቸው።

ይህ የምሽት እረፍት በልባችን ውስጥ አዲስ ተስፋንና ደስታን የሚጭር፣ አእምሮን የሚያሳርፍ የተባረከ ምሽት ይሁንልን።" 📖✨

​እረፍት ያለውና ሰላማዊ ምሽት ይሁንላችሁ❕💤

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አትርሱ❕
👉 @BookMereja 👈


ግዮናዊነት Book Mereja.pdf
3.9Мб
​📚 የመጽሐፍ ማጋራት / መረጃ 📖✨

​« ግዮናዊነት፡ የአማራ መነሻ እና መድረሻ »
📜⚔️

​"የአማራን ሕዝብ ታሪካዊ መነሻ፣ የብሔረሰቡን ትግል፣ ያጋጠሙትን ወቅታዊ ፈተናዎችና የቀጣይ መንገድ አቅጣጫን በምርምርና በፖለቲካዊ እይታ በጥልቀት የሚያስረዳ መጽሐፍ..."


🏫​የመጽሐፉ መረጃዎች፦

​✍️ ደራሲ፦ ምስጋናው አንዱዓለም (መልክ ሐራ)
​📅 የታተመበት ዓመት፦ 3ኛ ዕትም - ጥር 2010 ዓ.ም.
​🏫 የመጽሐፉ ይዘት፦ መጽሐፉ የአማራን ታሪክ፣ የብሔርተኝነት እድገት፣ ወቅታዊ የፖለቲካ ፈተናዎችን፣ የአንድነትና የስብስብ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የቀጣይ ትግል መድረሻዎችን በ10 ምዕራፎች ከፍሎ ያቀርባል::
​🎯 ዓይነት፦ ታሪክ፣ ፖለቲካና ማኅበራዊ ጥናት

​💡አጭር ማብራሪያ፦
ይህ መጽሐፍ «ግዮናዊነት» በሚል ርዕስ በምስጋናው አንዱዓለም የተጻፈ ሲሆን፣ የአማራን ህዝብ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ጉዞ ከጥንት እስከ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በመተንተን ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥ ጥናታዊ መጽሐፍ ነው::



​📚ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ⚡️ 🏫✨

​📚ተጨማሪ መጻሕፍትን ለማግኘት ይቀላቀሉ፡
         👇👇👇
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me
🔗 BookMereja.t.me


​"አንድ መጽሐፍ ስታነብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት፣ ልምድና ዕውቀት በአንድ ጊዜ ትኖረዋለህ።" 📖✨

​እያንዳንዱ አዲስ ጥዋት ያልተከፈተ አዲስ የመጽሐፍ ገጽ ነው፤ ዛሬ በሚጠበቅባችሁ አዲስ ገጽ ላይ መልካም ነገር ብቻ እንድታስፍሩ እንመኛለን❕

​ስኬታማና በዕውቀት የተሞላ ቀን ይሁንላችሁ❕🌸

ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አይርሱ❕
👉 @BookMereja 👈


​"እንደማይመጣ አምና ታውቃለች፤ ግን አሁንም ትጠብቀዋለች... ለምን⚡️
ምክንያቱም ታፈቅረዋለች።


በገዛ ውሸቷ፣ 'ይመጣል' በሚል መካከለኛ ተስፋ ልቧን እየሸነገለች በፅናት ትጠብቀዋለች።

​ምክንያቱም ስናፈቅር እንደማይቀየር እርግጠኛ የሆንንበትን ነገር ሳይቀር 'ሊቀየር ይችላል' ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

አዎ፣ ስናፈቅር 'አብቅቷል፣ በቃ አለቀ፣ አከተመ' ባልነው ጉዳይ ላይ እንኳን በምናልባት ስስ ተስፋ እናሳድራለን።

እናም ይህ አጉል ምኞታችን የወለደው ባዶ ተስፋ ቀን በቀን ውስጣችንን እየገደለ ሲሄድ እንኳን ልብ እስከማንል ድረስ በፍቅር እንታወራለን..." 📖✨

​እረፍት ያለውና አእምሮን የሚያሳርፍ መልካም ምሽት ይሁንላችሁ⚡️ 💤

​ለወዳጆቻችሁ ሼር ማድረጉን አይርሱ⚡️
👉 @BookMereja 👈

Показано 20 последних публикаций.