ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ልምድ
የቻይና ልማት ባንክ
የቻይና ልማት ባንክ በአገሪቱ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ለውጥ በማምጣት ወሳኝ ድርሻ ያለው ባንክ ነው፡፡ ባንኩ በዋናነት በመሰረት ልማት፣ በአምራች ኢንዱስትሪዎች፣ በክልላዊ ልማት፣ በዓለምአቀፋዊ ድጋፎች፣ በምርምር እና ቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ ዘርፍ ቀጣይነት፣ በማህበራዊ ልማት እና በፖሊሲ ጥናት ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
በዚህም ባንኩ በአገሪቱ የፈጣን መንገድ ግንባታን፣ የባቡር መንገድ፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች እና የከተማ መሠረት ልማት ሥራዎችን ፋይናንስ ያደርጋል፡፡ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የቻይና መንግስት የረጅም ጊዜ የልማት ግቦችን ታሳቢ ያደረገ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎችን ፋይናንስ ያደርጋል፡፡ አገሪቱን በሚያዘምኑ እና የአምራች ኢንዱስትሪውን ከፍ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች በቻይና ልማት ባንክ ይደገፋሉ፡፡
በተጨማሪም የገጠር እና የከተማ ልማት ማስፋፋት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ የሚያደርገው ባንኩ በክልሎች መካከል ያለውን የልማት ልዩነት የማጥበብ ከአገሪቱ ኢኮኖሚ ጋር የማስተሳሰር ሥራ ይሠራል፡፡
የቻይና ልማት ባንክ እንደ ሮድ እና ቤልት ኢንሼቲቮችን ፋይናንስ በማድረግ አገሪቱ የምታደርጋቸውን ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚደግፍ ሲሆን፣ ይህም የአገሪቱን የወደፊት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ባንኩ የፈጣራ ሥራዎችን እና ለኢኮኖሚ እድገቱ ፋይዳ ያላቸውን ጀማሪ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍም ይታወቃል፡፡
የቻይና ልማት ባንክ በጤና፣ ትምህርት እና የቤት ልማት ፕሮጀክቶችንም ፋይናንስ በማድረግ በአጠቃላይ በአገሪቱ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየደገፈ የሚገኝ አንጋፋ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡